ኢሳት ዜና ህዳር 27 ቀን 2010ዓም) ኢትዮጵያ ለጂቡቲ በነፃ የምትሰጠው የንፁህ ውኃ አቅርቦት ግንባታው ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ሊጀምር ነው

(ኢሳት ዜና ህዳር 27 ቀን 2010ዓም) ኢትዮጵያ ለጂቡቲ በነፃ የምትሰጠው የንፁህ ውኃ አቅርቦት ግንባታው ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ሊጀምር ነው

በተለያዩ የአገሪቱ ከተሞችና በገጠሪቱ የአገሪቱ ክፍሎች ያለው የንጹህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ችግር ተባብሶ በቀጠለበት በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያ ለጂቡቲ በነፃ የምትሰጠው የንፁህ ውሃ አቅርቦት ግንባታው ተጠናቆ በሦስት ወራት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ለጂቡቲያውያን መዳረስ እንደሚጀምር የገዥው ፓርቲ ልሳናት አስታወቁ።
ለመጪዎቹ መቶ ዓመታት የጂቡቲን የውሃ አቅርቦት ለማሟላት የሚያግዘው ፕሮጀክት በ350 ሚሊዮን ዶላር ወጪ የተሰራ ሲሆን ግንባታውን የጂቡቲ መንግሥት ሲያካሂድ የኢትዮጵያ መንግሥት በበኩሉ ውሃውን በነፃ ያቀርባል፡፡ በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የጂቡቲ ከተሞች በመጠኑ የውኃ ሥርጭቱ መጀመሩም በጂቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሻሜቦ ፊታሞ እና የትራንስፖርት ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ ለጋዜጠኞች አስታውቀዋል።
በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል በሽንሌ ዞን በኩሊ ሸለቆ ልዩ ስሙ ዋሮፍ በተባለ ቦታ ላይ በቻይና ኩባንያ ለጅቡቲ መንግስት የሚቀርበውን የውሃ መጠጥ የከርሰ ምድር ውሃ ቁፋሮ ረቂቅ አዋጅ በፓርላማው ሳያፀድቀው የውሃ ቁፋሮው ተጠናቋል። በወቅቱ ኢትዮጵያ በሽንሌ ዞን ለጅቡቲ የውሃ ማሰራጫ 20 ሔክታር መሬት በነፃ የሰጠች ሲሆን የውሃ ልማቱ ለሚካሄድበት ተጨማሪ አራት ሺህ ሔክታር መሬት እንደምትከልል በስምምነቱ ላይ ሰፍሯል።
በመዲናዋ አዲስ አበባ፣ አዳማ፣ መቀሌ፣ ጎንደር፣ ሃረር፣ ድሬዳዋ፣ ባህርዳር፣ ጅጅጋ፣ ሃዋሳን የመሳሰሉ ብዙ ሕዝብ የሰፈረባቸው ታላላቅ ከተሞች በንጹህ ውሃ እጥረት ችግር ለዘመናት ተጎጁ ከሆኑት ውስጥ በቀዳሚነት ይጠቀሳሉ። የኮተቤ አካባቢ ነዋሪዎች ለዓመታት በውሃ እጥረት በመቸገራቸው የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን በቦቴ ውሃ እያቀረበ መሆኑን ሸገር ኤፍ ኤም መዘገቡ ይታወሳል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *