አልተገናኝቶም -ለ አቶ አበበ ቦጋለ 🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥

አልተገናኝቶም -ለ አቶ አበበ ቦጋለ
🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥

በቅድሚያ የ ብዙወቻችን ቅሬታ ተቃውሞ ሰተው ለማብራራት በመቅረብወት ያለኝን ከልብ የመነጨ ምስጋና ለመግለፅ እወዳለሁ! እንደዚህ መደማመጥ መኖሩ መልካም እና የሚበረታታ ነው::

ይህ በ እንዲህ እንዳለ እኔም ሆንኩ ብዙው የንቅናቄው ደጋፊም ሆነ ሌላው ኢትዮጵያዊ ያቀረበውን ቅሬታ ኢሳት በ አግባቡ አቀነባብሮ ስላቀረበውም ለ ኢሳት እንደ ተቋም በ እረፍት ጊዜው ይህን የ ህዝብን ቅሬታ ይዞ መድረክ ላይ ያቀረበው ምንይላቸው ስማቸውንም ማመስገን እወዳለሁ::

አቶ አበበ ቦጋለ እውነቱን ለመናገር የ ድርጅት ጉዳይ ሀላፊ ሁነው ለ ድርጅቱ አባላት ማብራሪያ ለመስጠት የሞከሩ እንጂ ለመላው የ ሀገሪቱ ህዝብ የሚአገናኝ የ ህዝብ ግንኝነት ስራ ለ መስራት የመጡ አልመሰለኝም! ተግሳፅ እና ቁጣ የተቀላቀለበት ለምን እኛ የ ፃፍነውን ሳይሆን ለማለት የፈለግነውን አልተረዳችሁም የሚል አይነት ወቀሳ አውርደውብን ሄዱ! ሆድ ለባሰው ማጭድ አታውሰው አሉ አቨው! ሆ!

ፅሁፉ በግልፅ ያለውን ብሏል ! ፅሁፉ ግድፈት አለበት ለማለት የፈለግነውን አላንፀባረቀም ለማለት የፈለግነው ይህ ነው ብለው ቢመጡ አፉ ብለናል ወደፊት ሀሳባችሁን በደንብ የሚገልፅ ፅሁፉ ለመፃፍ ሞክሩ ብለን እናልፈው ነበር::ግን በ ተቃራኒው ሌላ መግለጫ አውጥተው ጥያቄወቹን በቀኝ ጀሮ ሰምተው በግራ አፍስሰው የ ተሰጠውን የ አየር ጊዜ አጠናቀዋል:: እውነቱን ለመናገር አቶ አበበ ቦጋለ ምንግዜም ሲቀርቡ ለ መከላከል ተዘጋጅተው እንጂ ለማብራራት እና የንቅናቄውን ሀሳብ ለመሸጥ ጥረት አድርገው አያውቁም::

የ አቶ አበበ ቦጋለን ሀሳብ አንድ በ አንድ እያነሳሁ መከራከር ወይም መደገፍ አስፈላጊነቱ አልታየኝም ሌላ ማስተባበያ ወይም መግለጫ ንቅናቄው እንዲያወጣ አልጠብቅም ከዛ ይልቅ ምንይላቸው ያቀረባቸው ጥያቄወችን በንቅናቄው አመራር በደንብ ታይቶ እና ተመርምሮ የ ስትራቴጅም ሆነ የ ስልት ማስቱካከያ እንዲአደርግ ነው::

ፓለቲካ የ አሸናፊነት ስልት እንጂ የ ፅድቅ ጎዳና አይደለም በመሆኑም ዘመኑን የዋጀ የ አዲሱን ትውልድ ስነልቦና እና የንቃተ ህሌና ያገናዘበ:: ጠላቱን ሊመታበት የሚችለውን ጉልበት እና አቅም የሚፈጥርበትን አካባቢ እና ማህበረሰብ ያገናዘበ ስልት ቢከተል ለ ዚህች መከረኛ ሀገር አለኝታ መሆን ይችላል:: ነገር ግን የቆጡን ለማውረድ በመሞከር የብብትን መልቀቅ ለ ሀገሪቱም ብብቱ ውስጥ ላለው ህዝብም መከራ ከማብዛት ውጭ ጥቅም የለውም::

አንድ ወዳጄ በ ውስጥ መስመር እቺን ትዝብቱን አካፈለኝ !

“ይህን መግለጫ ስሰማ አንድ ያነበብኩት ቅኔ ትዝ አለኝ። እንዲህ ይላል፦ “ጽንሓ ለእሳት ከዊነ ብርዓ”(የአማርኛ ትርጓሜውም ፦ እሳትን ገለባ ሆነህ ጠብቀው ማለት ነው)
ቅኔው ሲመሰጠር፦ G7 አማራውን በሚመለከት እየነደደበት ለነበረው የCrediability እሳት፤ በዚህ መግለጫ እራሱን ገለባ አርጎ ጠበቀው በደንብ አቃጥሎ እንዲታጠፋው።

ከዳዊት ሰለሞን

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *