ከሀሳዊ “አባቶች” ተጠበቁ

ከሀሳዊ “አባቶች” ተጠበቁ
🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥

ይህን ፅሁፍ ያሰፈረው ብቸኛው የ ወገኑ ተቆርቋሪ ሙሁር የ እኝው ወንድም ታዋቂው ሙሁር ዶር ሰማኽኝ ነው! ይህ ወንድማችን ያለውን ሰአት አጣቦ የወገኑን ህመም እየታመመ እኛን የሚአወያዩ ፅሁፎችን ይልካል ዛሬ ምሬቱን የገለፀው የ ሀይማኖት ጭንብል ያጠለቁ ሀሳዊ የሀይማኖት አባቶች ላይ ነው! እንደ ዶር ሰማኽኝ ያሉ ሙሁራን ብዙ ቢሆኑ መከራችንም ይቀል ነበር!Semahagn Gashu Abebe

“ሰላም ለሁሉም ነገር እጅግ አስፈላጊ ነገር ነው። ስለ ሰላም መስበክ ግን በራሱ ሰላምን አያመጣም። ሰላም የሚመጣው ለሰላም መታጣት ምክንያት የሆኑትን ግፍንና ጭቆናን መቃወምና መታገል ሲቻል ነው። የእኛ አገር የሃይማኖት መሪዎች ግን ግፍ ሲደረግ አይኔን ግንባር ያድርገው ብለው ይቆዩና የተገፉት የግፍ ቀንበራቸውን ለመጣል በአልሞት ባይ ተጋዳይነት ሲታገሉ የሰላም ተቆርቋሪዎች ሆነው ብቅ ይላሉ።

እነዚህ ሰዎች ግፍን ሳያወግዙ ስለ ሰላም ሚናገሩ ከሆነ ህዝቡን ባርነትን ተቀብላችሁ ኑሩ ማለታቸው እንደሆነ ሊረዱት ይገባል። ይባስ ብሎ ደግሞ አንዳንድ ነብያት ነን ባዮች የሰዎች ስልክ ቁጥር ተገለጠልን እያሉ ገንዘብ እየዘረፉ ስለ አገራዊ ጉዳይ የሚመጣላቸው ራእይ የለም። የአገራችን ውድቀት አንዱ ምክንያት ለእውነት የቆሙ የሀይማኖት መሪዎች አለመኖርም ነው። መፅሃፍ እንደሚል እንዲህ አይነት የሀይማኖት መሪዎች በነፋስ የተወሰዱ ውኃ የሌለባቸው ደመናዎች፥ ፍሬ የማያፈሩ ሁለት ጊዜ የሞቱ ከነሥራቸው የተነቀሉ በበጋ የደረቁ ዛፎች ናቸው።”

በዚህ ፅሁፍ ስር እህታችን የ ሰው ልጅ መብት ተቆርቋሪዋ የ ቤተክርስትያን አገልጋይ ስዋሰው ጆንሰን ይህን ብላለች!Sewasew Johannessen

“😭😭😭😭😭ለኢትዮጵያ መልካም እረኛ የሆነ የሐይማኖት መሪ በስንት ጭንቅ ቢገኝ :እነርሱም በአገር ውስጥም አለያም በውጭም ስደት ላይ ናቸው::
“ መልካም እረኛ እኔ ነኝ“ ያለው ጌታችንን እና መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደሙ የዋጃት ቤተክርስቲያን: የጌታዋን ጥምቀት ለማስታወስ በዓሉዋን ስታከብር: ትውልድ እንደ ቅጠል ረገፈባት::
“ በቀል የኔ ነው“ ያለው አምላካችን እግዚአብሔር የትውልዱን ደም ከፀባዖት ይበቀል!
የበግ ለምድ ለብሰው በየቤተክርስቲያኑ የተሰገሰጉትንና በስሙ የሚነግዱ ተኩላዎችን: የቤተክርስቲያን ራስ የሆነው ክርስቶስ ዋጋው በእጁ አለና: ዋጋቸውን ይክፈላቸው!
በየዕለቱ በመላ አገሪቱ ስደት: ጦርነት: መከራና ረሐብ ሲፈራረቁባት ማየትም መስማትም እጅግ ልብን ይሰብራል::
“ እግዚአብሔር የለም“ ብሎ ትውልዱን ሲግት የነበረ ነፍሰ በላ ድርጅት: ቄሶችንና ሰባኪያንን የሚፈልጋቸው እንደ እሳት አደጋ መከላከያና: ትውልድ በድንዛዜ ትምህርት ልቦናው እንዲጨልም ለማድረግ ብቻ ነውና: ይህን አዙሪት እግዚአብሔር በታላቅ ክንዱ ይስበረው!”

ዳዊት ሰለሞን

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *