እነ ገዱ አጋዚ በኦራል ተጭኖ ሲገባ በደንብ ያውቃሉ::

# Ethiopia :-ገዱ አንዳርጋቸው “አጋዚ ወልድያ ከተማ እንዲገባ ትእዛዝ አልሰጠሁም” ብሎአል እየተባለ እየተወራ ነው :: መራር ቀልድ ነው:: በሃዘናችን ላይ ሃዘን የሚጨምር አስቀያሚ ቀልድ:: ከሳምንት በፊት አጋዚ ወደከተማው በብዛት ሲገባ ህዝቡ “ለምን?” የሚል ጥያቄ አንስቶ ነበር:: የሚሰማው ግን አልነበረም:: ብዙዎች ግጭት እንደሚነሳ እርግጠኞች ነበሩ:: ወታደሮች ሆን ብለው ያልተገቡ ድርጊቶችን በማሳየት ህዝቡን ያበሳጩት ነበር:: አንዱ ወዳጄ “ወልድያን ስናይፐር የታጠቁ ወታደሮች እያስፈራሩዋት ነው፣ ወጣቱ በድርጊታቸው በጣም ተቆጥቷል፣ የከተራ ቀን ግጭት እንደሚነሳ እርግጠኛ ነኝ፣ ወታደሩን በብዛት ማስገባታቸው ህዝቡን እልህ ውስጥ እየከተተው ነው” የሚል መልዕክት ሰዶልኝን ነበር:: እነ ገዱ አጋዚ በኦራል ተጭኖ ሲገባ በደንብ ያውቃሉ:: የከተማው ሹም እንኳን ባይነግራቸው ኢሳት ነግሮአቸዋል፣ የኢሳትን ዘገባ ማየት ይቻላል :: ከብአዴን ደህና ነገር መጠበቅ፣ ህወሃት ለሰው ነፍስ ዋጋ ይሰጣል ብሎ እንደ መጠበቅ ነው:: ህወሃት ጸረ-ህይወት ነው:: ማንነቱ የተገነባው በመግደል ነው:: ብአዴን ደግሞ የህወሃት የባህሪ ልጅ ነው፥ ሁለቱም በግብር አንድ ናቸው:: ህወሃት 60 ሺ የትግራይ ወጣቶችን ገብሮ ስልጣን እንደያዘ ይናገራል:: አሁን የሚፈጽመው ግድያ የእነዛን የሟቾቹን ደም ለመበቀልም ይመስላል፣ ያስ ቢሆን 26 አመት ሙሉ የገደለው፣ባድሜን ሳይጨምር፣ 60 ሺ አልደረሰም ብላችሁ ነው? ካልደረሰስ ስንት ይቀራል?

በወልድያ የተካሄደው ጭፍጨፋ ሆን ተብሎ የተቀነባበረና ለበቀል ተብሎ የተዘጋጀ ነው::

ወልድያዎች ለመብታችሁ በምትከፍሉት ዋጋ የፍትህ አምላክ ብድራችሁን ይክፈላችሁ፣ የወልድያ እናቶችና አባቶች መጽናናቱን ይስጣችሁ::
Fasil Yenealem ( Esat )

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *