አምርረን ከታገልን፣ አይደለም እስረኞችን ማስፈታት፣ የፖለቲካ እስረኛ የሚባል ነገር በኢትዮጵያ ምድር እንዳይኖር ማድረግ እንችላለን

Fasil Yenealem፦ አምርረን ከታገልን፣ አይደለም እስረኞችን ማስፈታት፣ የፖለቲካ እስረኛ የሚባል ነገር በኢትዮጵያ ምድር እንዳይኖር ማድረግ እንችላለን። የዶ/ር መረራ መፈታት ነጻነት በእጃችን ላይ ያለ መሆኑን አሳይቶናል። ነጻነት የሚገኘው በስጦታ ሳይሆን በትግል ነው። የሰው ልጅ ያለፈና መጪው ታሪኩ ከትግል ጋር የተያያዘ ነው። ትግል የሌለበት የሰው ልጅ ታሪክ የሚገኘው አዳምና ሂዋን ከገነት ከመባረራቸው በፊት ይመስለኛል፤ ከዚያ በሁዋላ ያለው ታሪክ በሙሉ የመውደቅና የመነሳት ( የትግል) ታሪክ ነው። እና በአጭሩ ቀበቷችንን ( መቀነታችንን) ጠበቅ አድርገን ትግላችንን ከቀጠልን፣ አገራችንን የነጻነት ምድር ማድረግ እንችላለን። ይህ ትውልድ አገሩን ነጻ አድርጎ ማለፍ ከቻለ፣ ለሺ አመታት የሚነገር ታሪክ እንደሰራ ይቁጠረው።
ዶ/ር መረራ እንኳን ከዚያ አስከፊ እስር ቤት በሰላም ወጣህ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *