የ “ኮሶ ሻጭ ልጅ”….አፄ ቲወድሮስ

የ “ኮሶ ሻጭ ልጅ”….አፄ ቲወድሮስ
💚💛❤️🌹🌹🌹🌹💚💛❤️

ከዳዊት ሰለሞን

ደምቢያ ከ ጎንደር ከተማ በ ቅርብ እርቀት ወደ ጣና ሀይቅ ረገድ የሚገኝ እና ከ ሀይቁ የሚዋሰን ወለል ያለ ሰፊ ሜዳ ያለበት በሰሜን እና በምዕራብ ተራራ የተንተራሰ ለም መሬት ነው!

ዓፄ ቲወድሮስ የተወለዱትም ደንቢያ ነው! ካሳ ሀይሉ ደንቢያ መወለድ ብቻ አይደለም ከ ደጃች ጎሹ ጋር ተዋግተው የመጀመሪያውን አንፃባራቂ ድል ያገኙትም ደንቢያ ውስጥ ከምትገኝ ጉራንባ ላይ ነው!

ከ ዚህ ላይ ቋረኛው ካሳ እየተባለ የምናውቀውን ታሪክ እንዴት ወደ ደንቢያ ወሰድከው የሚለኝ ቢኖር እንዲህ አስረዳለሁ!

ደንቢያን ያቀናት ደጃች ማሩ የሚባል ጀግና የጦር አዋቂ ነው! ደጃች ማሩ በጌምድርን ሰሜንን እና የጁን አስገብሮ የሚኖር በተደጋጋ ሚ የመጣውን የቱርክን ጦር በምዕራብ በኩል ድል ያደረገ ዓፄ ቴወድሮስ የተካነበትን ሽምጥ ጋልቦ የ ጠላትን ጦር የማተረማመስን እና መሪውን የመምታትን ስልት የፈለሰፈው ሀያል ብርቱ ጀግና ነው! ማሩ ቀመስ ደንቢያ የሚለው አባባል የተገኘው ከዛ ነው!

ደጃች ማሩ በዘመኑ ያስቸግሩት የነበሩትን ቋረኞች ለመያዝ በማሳብ የቋራውን ባላባት ልጅ ሀይሉን ( የቴወድሮስ አባት) ለ እህቱ ይድርና ልጅ ሀይሉን ደንቢያ ጉራንባ እንዲኖር ያደርገዋል! ልጅ ሀይሉ የ ቴወድሮስ ወንድም ክንፉን ይወልዳል ! ከ ዘመናት በሗላ ደጃች ማሩ እህታቸውን አፋተው ለ አማራ ሳይንቱ ባላባት ይድሯታል!

ልጅ ሀይሉ በግዞት ሲኖር እንደ ወቅቱ አገላለፅ ኮሶ የምታጠጣው ሚስት እናጋባው የሚል ምልጃ ወደ ደጃች ማሩ ይመጣል! ኮሶ የሚባል ጥሬ ስጋ በመብላት ምክኒያት የሚመጣን ኮሳ የሚባል ጥገኛ የ አንጀት ትል ( tape worm )የሚያጠፋ ፍቱን መድሀኒት ነው! መድሀኒቱ ሀይለኛ ስለሆነ ደሮ ወጥ ተዘጋጅቶ ከምግብ ጋ ይወሰዳል! ስለዚህ ኮሶ የምታጠጣ የሚለው የዘመኑ አገላለፅ ሚስት ማለት ነው…በግዞት ያለን ሰው ይዳር ሚስት ያግባ የሚለው አባባል ቅንጦት ስለሚያስመስል ነገሩን የሚአሳዝን መልክ አላብሶ ከደጃች ማሩ ፍቃድ የማግኛ ለስለስ ያለ አገላለፅ ነው!

የ እነ ፈሲል ዘር የሆነች የ ጎንደር ከተማ ተወላጅ ሴት ዘመድ ጥየቃ ወደ ደንቢያ ዘልቃ ስለነበር ለ ልጅ ሀይሉ ታጨች እና ተጋብተው አብረው ሲኖሩ! አንድ ብላቴና ጥር 6 ቀን 1811 ዓ/ም ተወለደ!

ደጃች ማሩ አንተን የሚተካህ ጀግና ካሳ ይባላል የሚል ንግርት ስለነበረ ይህን ብላቴና ለማስገደል አሰቡ! ተልኮውን ለማስፀም የተሰማራው የ ደጃች ማሩ አሽከር ሀሳቡን ቀይሮ በበቅሎ ሸኝቶ ልጅ ሀይሉን ወደ ሀገሩ ቋራ ሸኘው !

እናቱም ወደ ዘመዶቿ ጎንደር ከተማ ቤተክርስትያንን ገብታ ተማፀነች ከ ደጃች ማሩ ጋር በ ጎንደር ካህናት በታቦት የታጀበ ምልጃ ተረፈች ብላቴናውም አደገ! ቸንከር ተክመሀይማኖት ትምህርቱን ተከታተለ!

ደጃች ማሩ ከ የጁወች ጋ ሲዋጉ ተሰው በ እህታቸው ልጅ በቴወድሮስ ወንድም ደጃች ክንፉ ተተኩ! ደጃች ክንፉ ከ ቱርኮች ጋ ሲዋጋ ብላቴናው ካሳ ተገኝቶ እንደነበር እና ድንቅ የጦር ስልት አፍልቆ የጋርድ ጦር ድል እንዲቀዳጅ ስላደረገ እረኞች እና አዝማሪወች የ ካሳን ስም እየጠሩ መዝፈናቸው
ያልተድእሰተው ደጃች ክንፉ ጦር ወርውሮ ወንድሙን ሳተው! ብላቴናው ካሳ ወደ ጎጃም ተሰዶ ከ ደጃች ጎሹ ቤት ደጃች ክንፉ እስኪሞት ድረስ ኖረ!

ካሳ ሀይሉ ወደቋራ ወርዶ ተከታዮቹን አፍርቶ የ ራስ ዓሊ ተቀናቃኝ በሆነ ጊዜ ካሳን ለ ራስ ዓሊ ልጅ ተዋበች ዓሊን አጋብተው ወደ ጎንደር አስመጡት! ደጃች የሚል ማዕረግ አገኘ! በዘመኑ ተዋበችን ይፈልግ የነበር ደጃች ወንድ ይራድ በከተማው ሁሉ ኮሶ የምታጠጣው ሴት የሚለውን የ ደጃች ማሩ አማላጆች ቃል ጠምዝዞ እናቱ ኮሶ ሻጭ ናት ብሎ ስላስወራ በወቅቱ የነበሩ የውጭ ሀገር ዲፕሎማትም ስለሰሙት በጎንደር ከተማ ሲወራ ስለነበረ! ነገሩ በብዙ ተባዛ!

ስለዚህ ዓፄ ቴወድሮስ “የኮሶ ሻጭ ልጅ ” አይደለም በ እናቱ የ ፈሲል የነገስታት ዘር በ አባቱ የ ቋራ ባላባት ልጅ መሆኑን ለመግለፅ እና ልደቱን ለማስታወስ ይህን ፃፍኩ!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *