የ አማራ የበላይነት ነበረን?

የ አማራ የበላይነት ነበረን?
🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
የአማራ የበላይነት አልነበረም የምንለው በዘመኑ የትኛውም ስልጣን ላይ የነበረ ሀይል በዘር ተደራጅቶ አማራውን በተለየ መልኩ ልጥቀም ብሎ ስላልሰራ ነው። ከአፄ ዮሀንስ ጀምሮ የነበሩት ነገስታት አማርኛን የስራ ቋንቋ በማድረግ ስልጣናቸውን ያደላደሉበት መንገድ የአማራ የበላይነት ነበር ሚያሰኝ ምንም ነገር የለውም።

ለአማራውም ምንም የተለየ ነገር ያደረጉለት የለም። የትግራይ የበላይነት አለ ስንል ግን ህወሃት በዘር ተደራጅቶ ኢኮኖሚውን፥ፖለቲካውን ፡ደህንነቱን፥ ወታደሩን ተቆጣጥሮ የብሄሩን ተወላጆችና ክልሉን በተለየ መልኩ ለመጥቀም ያለሰለሰ ጥረት በማደረጉ ነው።

የአማራው የበላይነት ነበር በሚል የአማራውን ማህበረሰብ አንገት ለማስደፋት የሚደረገው ሙከራ በአዲሱ ትውልድ ተቀባይነት የለውም። ከዚህ በሁዋላ የአማራ የበላይነት ነበር የሚል የፖለቲካ ፕርግራም ማሟሻ በማድረግ እንደ ወያኔ አማራውን ለማሸማቀቅ መሞከር በእሳት እንደ መጫወት ነው።Semahagn Gashu Abebe

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *