የ አማራ ወጣቶች በ አማራነታቸው የሚደርስባቸው ግፍ እና በደል አንገፍግፏቸው ወደ ትግሉ በ አስገራሚ ሁኔታ ተቀላቅለዋል!!!!

ሞረሽ ! ….ጠንካራ የ አማራ መሪ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
የ አማራ ወጣቶች በ አማራነታቸው የሚደርስባቸው ግፍ እና በደል አንገፍግፏቸው ወደ ትግሉ በ አስገራሚ ሁኔታ ተቀላቅለዋል ይህ በ ኮ/ል ደመቀ ዘውዴ አስደናቂ ገድል አብሪነት የተቀጣጠለው ነጎድጏዳዊ ቁጣ ላለፉት ትቂት አመታት አድማሱን አስፍቶ የ አማራ ወጣቶችን በ አንድ ሳንባ እንዲተነፍሱ ያደረገ የትግል ቋያ ነው!

የ አማራው ፋኖ እንዲህ በመሰለ አስገምጋሚ ወኔ ለትግል ቢሰለፍም ግለቱን ጠብቆ የሚመራው ጠንካራ መሪ ባለማግኘቱ ምክኒያት በተፈለገው መጠን ማድግ ሳይችል ቆይቷል !

ስንት እና ስንት ሙሁራንን ያፈራ አማራ የመሪ መካን የሆነ ይመስል የ አማራ ሙሁራን ለወጣቶች ጥሪ ጀሮ ዳባ ልበስ በማለታቸው እነዚህ ወጣቶች ሁነኛ አቅጣጫ ሳይኖራቸው
ሲደክሙ ማየት ልብ ይሰብራል!

ከምንም በላይ ደግሞ ትንንሽ መርህ አልባ ጩኽት የሚጮሁ በ አማራ ወጣቶች ምሬት ጀርባ ቁብ ብለው የግላቸውን ዝና እና ክብር ለማስፈን የሚጥሩ ወረበሎችን ማየት ያማል! አማራ ሳይሆኑ አማራ ሁነው ወይም ሌላ ስውር ተልኮ አንግበው ወጣቱ ፈላፃውን ወደ ዋናው ጠላቱ መወርወር ሲገባው አላስፈላጊ የጎንዮሽ ውጊያ ላይ ተጥዶ እንዲውል ለፈረዱበት ክፉወች ልብ ግዙ ማለት ግድ ይላል!

አማራው ግዙፍ ቁጥር ያለው ከ 60% በላይ አዲስ አበባን ያቀፈ በሌሎችም ከተማች በብዙ ፐርሰንቴጅ የሚጠቀስ ነው! በ ውጭ ሀገር አብዛኛው የ ሀበሻ ነዋሪ አማራ ነው! ከ ዛም አልፎ በ እስራኤል ሀገር በ መቶ ሺወች የሚቆጠር ቤተ እስራኤላዊ አማራ ነው !

ይህ ግዙፍ ቁጥር ያለው አማራ ጠንካራ መሪ አላገኘም ! አማራው በ ንግግርም ሆነ በምግባር ሁሉም ኢትዮጵያውያን የሚአከብሩት ጠንካራ መሪ ከምንጊዜም በላይ ይሻል! አሁን ላይ ብዙ በ አማራ ስም የሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች አሉ መልካም ነው ! ሁሉም የሚችሉትን ሰርተው በተግባር ደጋፊ ለማፍራት መጣር ይጠበቅባቸዋል!

አሁን ደግሞ የ አማራ ወጣቶች ህብረት በተለየ መዋቅር እና ስትራቴጂ ተደራጅቶ አማራውን ለመታደግ ተነስቷል ይህ ደስ የሚአሰኝ ነገር ነው! እኔም ሆንኩ ብዙወች እንደ እኔ አይነት የ አንድነት ደጋፊ የ አማራ ልጆች ጠንካራ የ አማራ መሪ ማየት እንሻለን!

አኛ የመረረን እና ያንገፈገፈን ቢኖር ይህ የጎንዮሽ ሽኩቻ እንጂ ግንቦት 7 ንም ሆነ የ አማራውን ድርጅት ለመደገፍ አልተሳነንም ! እናንተ የ አማራ ድርጅቶች በመርህ የለሹን የጎንዮሽ ፍትጊያችሁን ተውልን እንጅ እኛ የምንችለውን ያህል እንደግፋችሗለሁ! እኔን ምሰሉ አልበለዚያ አጠፋችሗለሁ የሚል አዝማሚያ ያለው መርህ አልባ ጩኽት የሚጎዳው መከረኛውን አማራ ነው!

ሌላው ኢሳት ላይ ያላችሁ ነገር ነው! ኢሳት ለ እኔ እና ለ ብዙ የ አማራ ልጆች ጥሩ ሚዲያ ሁኖ ቆይቷል እኛም ድጋፋችን ይቀጥላል የ አማራው ጠንካራ ሚዲያ ከተመሰረተም እንደግፋለን በ ወር 20 ብር ለ ኢሳት 20 ብር ለ አማራ ሚዲያ መስጠት እኛን ይጎረብጠናል አላልናችሁ ኢሳትን ለቀቅ አድርጋችሁ ጠንካራ ሚዲያ ብታቋቁሙ ምናለበት!? ኢሳትን ለ እኛ ተውልን !

ግንቦት 7 ቢሆን በተመሳሳይ መልኩ ለ እኛ ተውልን እና ጠንካራ በመርህ ላይ የተመሰረተ ድርጅት ፍጠሩ ግንቦት 7ንም የ አማራውን ድርጅትንም ለመርዳት ታከተን መች አልናችሁ ? እናንተ ብቻ ግንቦት 7ን አትንቆሩብን እንጂ ድጋፋችን አይለያችሁም ! ነገር ግን የ ምደግፈውን ንቅናቄ ሌት ተቀን ስትጠለሹብን እየዋላችሁ እንዴት እንድደግፋችሁ ትጠብቃላችሁ? ግድ የለም እስከ ችግሩ ግንቦት 7 ለ እኛ ተውልን ! ዜሮ ነው የለም ካላችሁም እኛን ይጭነቀን እናንተ በ እኛ ኪስ ምን አገባችሁ እና በ አማራው እየተረዳ ምናምን የ ሚል መርህ አልባ ጩኽት ታሰማላችሁ?

ሽግግር መንግስት አማራውን ትተው ተሰበሰቡ እያሉ ከማለቃቀስ እና ሲናቆሩ ከመዋል በተግባር ጠንካራ መሪ እና ድርጅት መመስረት ግድ ይላል ! በርቱ ተደራጁ ጠንክሩ የጎንዮሽ መርህ አልባ ጩኽት አቁሙ እኛም ከጎናቸሁ ነን !

ማሳሰቢያ
🔥🔥🔥
በነገራችሁ ላይ ሞረሽ የሚለው ቃል ወጣቶች ተራራ ላይ ወጥተው ድምፃቸውን ከፍ አድረገው የሚአሰሙት ጩኽት ነው! ሞረሽ….እገሌ አበሉን አላያችሁም አይነት ነገር! አደራ ከ ሞረሽ ወገኔ የ አማራ ድርጅት ጋር እንዳታገናኙብኝ …ሞረሽ የሚለውን ቃል የተጠቀምኩት ጥሪየ በ ታላቅ ድምፅ መሆኑን ለማመልከት ብቻ ነው።    ከዳዊት ሰለሞን

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *