መከላከያ ሰራዊቱ ያደረገውን ጭፍጨፋ ህግን እና ስርአትን ለማስከበር መሆኑን በመግለፅ ያመሰገነው መግለጫው ወደፊትም ይህን እርምጃ አጥብቆ ያለርህራሄ መፈፀም እንደሚገባው ይገልፃል …

የኢሀዴግ ስራ አስፈፃሚ መግለጫ
ሲፈተሽ
🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥

የ ኢህአዴግ የ ስራ አስፈፃሚ ስብሰባ መግለጫ ብዙወቻችን የጠበቅነውን የ ህውሀት የበላይነት በማረጋገጥ ተጠናቋል! የ ግንባሩን በቃላት ድርደራ የታጨቀ ዝባዝንኬ መግለጫ አንብቦ ለመጨረስ ጉልበት ይጠይቃል…ወላዲት አምላክን በጣም እያቅለሸለኝ በመከራ ነው ያነበብኩት …ውይይይ ምሬቱ አሁንም አፌ ላይ አለ …

እየመረረኝም ቢሆንም ገለባውን ከፍሬው አጣርቼ ለመረዳት እንደቻልኩት በ መግለጫው የ ህውሀት አጀንዳወች በበላይነት አሸንፈው የወጡበት ሀሳብ ተንፀባርቋል! እርግጥ ውሳኔውን ማን ደገፈ ማን ተቃወመ የሚለው መረጃ ባይኖረንም በስሌት ደረጃ የ ለማ እና የገዱ ቲም በቁጥር ያንሲልና እና ውሳኔውም የህውሀትን የበላይነት ያንፀባረቀ እንደሚሆን የተጠበቀ ነው የሆነውም ይህ ነው!

መግለጫው አፅንኦት የሰጠባቸውን ጉዳዮች ለመግለፅ ልሞክር ነውና ተከታተሉኝ!

🛑 መርህ አልባው ቡድናዊ ትስስር
🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
ይህ በ ሸውራራውም ሆነ በ አድዋው ቅኔ ለመግለፅ የተሞከረው ኦሮማራ መሆኑን ለማወቅ የ ሮኬት ሳይንቲስት መሆን አይጠበቅም! መግለጫው የ አማራ እና የ ኦሮሞን ግንኝነት መርህ አልባ ብሎታል …መርህ አልባ የሚለው ንግግር ምንም ስሜት የሌለው ተራ አገላለፅ ቢሆንም በመሰረታዊ ነገሩ የ ኦሮማራ ማበብ እና መጎልበት የ ህውሀት ውድቀት ስለሆነ በዚህ መግለጫ ተውግዟል ከዚህ በሗላም ኦሮማራን ለማስቆም ወስኗል!

🛑 የትግራይ የበላይነት የለም

መግለጫው ባለፈው 25 አመት እኩልነት እንጅ የበላይ እና የበታች የማይታይበት ስርአት ገንብተናል ይልና ይህም በስራ አስፈፃሚው መረጋገጡን ይነግረናል…ስንተረጉመው የ ሚነገረው የ ትግሬ የበላይነት ትረክት የ አያጅቦ መስፈራሪያ እንጅ እውነት አይደለም አንደማለት ነው…

🛑 የበላይ አመራሮች ላይ እርምጃ ይወሰድ

ኢህአዴግ ግንባር ስለሆነ በ አባላት ላይ እርምጃ መውሰድ አይችልም በመሆኑም ብሄራዊ ድርጅቶች በግልፅ ቋንቋ ኦህዴድ እና ብአዴን የበላይ አመራሮችን በጥልቅ ገምግመው እርምጃ እንዲወስድ ተወስኗል! እዚህ ላይ ነው ችግሩ እንደ ህውሀት ፍላጎት እነሱ የማስተካከያ እርምጃ ስለወሰዱ ኦህዴድ እና ብአዴን በ ነ ለማ ዶር አብይ እና ገዱ ላይ እርምጃ እንዲወስድ ታዘዋል! ኦህዴድ ያደርገዋል ብየ አላምንም ብአዴን ግን ገዱ ላይ እርምጃ እንዲወሰድበት ታዘዋልና ያደርጉታል ለዚህም እንዲረዳ በረከት ስምኦን ተጨምሮላቸዋል…
ገዱ ሆይ ለፈፀምከው ተጋድሎ ሳላመሰግንህ አላልፍም …

🛑 መከላከያ እርምጃ እንዲወስድ ታዟል

መከላከያ ሰራዊቱ ያደረገውን ጭፍጨፋ ህግን እና ስርአትን ለማስከበር መሆኑን በመግለፅ ያመሰገነው መግለጫው ወደፊትም ይህን እርምጃ አጥብቆ ያለርህራሄ መፈፀም እንደሚገባው ይገልፃል …መንገድ በመዝጋትም ሆነ በሌላ መልኩ የሚገለፅን ተቃውሞ ያለርህራሄ እርምጃ በመውሰድ ማስቆም እንዳለበት ይገልፃል …

ሌሎቹ ሀሳቦች የተለመዱ ዲስኩሮች በመሆናቸው እናንተን ውድ አንባቢወችን በ ወያኔ ዲስኩር አላደርቅም …ክቡራን አንባቢወቼ መልካም አዲስ አመት ! በዚህ አመት ስላስያችሁኝ ያልተቋረጠ ድጋፍ አመሰግናለሁ ! እስከ ድል ድረስ ተያይዘን ወደፊት እንጏዝ!
💚💛❤️
ኦሮማራ ያብባል! ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር
💚💛❤️ከዳዊት ሰለሞን

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *