ትዉልዱም ነክሶ የማያኝከውን አዉሬ ሊጋፈጠዉ ተዘጋጅቷል።

የህወኣት አርማጌዶን – መኮንን ሀብተጊዮርጊስ ብሩ (ዶ/ር)

መኮንን ሀብተጊዮርጊስ ብሩ (ዶ/ር)

“በደንብ መዝነቡ አይቀርም”። አለ ትኩር ብሎ እየተመለከተኝ።  በዚህ ሁኔታ ሳየዉና ሳዳምጠዉ ሁሌም ዉስጤ ይደነግጣል። ብዙ ጊዜ ትንቢት ከሚመስለዉ ምልከታዉ ጋር የሚያስፈራና እልፎ አልፎም የሚያሳዝነዉ ሳቤላዊ  የንግግር ቃናዉ በቀላሉ ትኩረት ይስባል። ሰለሞን ንግግሩን ቀጠለ “ነጎድጓዱ በአራቱም አቅጣጫ እየተሰማ ነዉ። ንፋሱም ተራዉን ሳይጠብቅ እዚህም እዚያም ሽዉ እያለ ነዉ። ሰዉና እንሰሳቱም አምሳያቸዉን እየፈለጉና እነርሱን ከሚመስላቸዉ ጋር በመጠጋት  ሊመጣ ያለዉን ዉሽንፍር በጋራ ለመጋፍጥ ወዲህ ወዲያ ሲሉ እየታየ ነዉ። መጪዉ ማህበልና ጎርፍ የስንቱን ሕይወት እንደሚያጠፋ ማወቅና መገመት ቢያስቸግርም በርካታ እናቶች ግን በልጆቻቸዉ በድን ላይ ተቀምጠዉ ደግመዉ ደጋግመዉ እንዲያለቅሱ የተፈረደባቸዉ ይመስላል። ብዙ ስቃይና መከራም ይሆናል” አለ ሰለሞን በሁለት ጣቶቹ ግንባሩን በስሱ እያሻሸ።

ምንም ነገር ተናግሬ ላቋርጠዉ ስላልፈለኩ በዝምታ ዓይን ዓይኑን መመልከቴን ቀጠልኩ። እሱም አሳቤ የገባዉ ይመስል ንግግሩን ቀጠለ “የሚያስፈራ ዘመን ነው። እናት የልጇን ሬሳ መቅበር አትችልም፤ አባትም ለሚስትና ለልጆቹ መከታ መሆን ላይችል አቅም ያጣል፤ ባልንጀሮችም እንደባላንጣ ይተያያሉ፤ ሕፃን አዛዉንቱ የሚሰማቸዉ ላይኖር የስቃይ ጣራቸዉን ያሰማሉ። መጪዉ ዘመን አስፈሪ ነዉ። ትዉልዱ ከማያዉቁት መልሃክ የሚያዉቁት ሴይጣን ከሚለዉ ብሄል ርቆ ብዙ ተጉዟል። በለዉጥ እርግዝናና ምጥ ዉስጥ ባለ ትዉልድ ዙሪያ እርኩስ መንፈስ የሕፃኑን ጉሮሮ ሊደፍን አቆብቁቧል። ስለዚህ ትዉልዱም ነክሶ የማያኝከውን አዉሬ ሊጋፈጠዉ ተዘጋጅቷል።” አለ

አሁንም መልስ አልሰጠሁትም። ይልቁንም እያስፈራዉ ያለዉ ነገር እኔንም ያስፈራኝ ጀመር።

ሰለሞንም መናገሩን ቀጠለ “እየመጣ ባለ ዉሽንፍር ዉስጥ አብሮ ሊመጣ የሚችል እንግዳ መልሃክ ብቻ ሳይሆን ሴይጣንም ቢሆን እንኳ ይህ ሕዝብ ሊቀበለዉ የተዘጋጀ ይመስላል። ቤት የሕግዚሃብሔር መባሉ ሊቀር ተቃርቧል። አስፈሪ ዘመን ነዉ። ቤተ ክርስትያን በዲያቢሎስ ሰንሰለት ተጠፍራ አርማጌዶንን የምትናፍቅ ሆናለች። የልጆቹን እንባ ከማበስ ይልቅ ቤተ መቅደስ ሆዳቸዉ ቀንድ በሆነባቸዉ ጋኔኖች ተሞልታለች። የሕግዚሃብሔር መንፈስ የታሰረ ይመስል እርኩስ መንፈስ በየቦታዉ መልከስከስ ብቻ ሳይሆን ለመጨረሻዉ አርማጌዶን ዝግጅት ዘጠኝ ቀዳዳ መጫሚያዉን  እየወለወለ ይገኛል። ይህም ሆኖ ተዓምራት በዝቷል። አላዛር ብቻዉን ላይሆን ሌሎችም ከሞት ተነስተዋል የሚል የጠንቋይ ወሬ በከተማይቱ ይሰማል። መንፈስ ከራሱ ጋር አይጣላምና ሴሰኞችና ቀማኞች የከተማይቱን ቤተ መቅደስ ይፈነጬበታል። በልጇ ሬሳ ላይ ተቀምጣ በምታነባ ሴት መንደር ብዙ ቅዱሳንና ነቢያት እንደ ባሕር አሳ ተበራክተዋል። የቆሰለዉን አዉሬ መገሰፅን ባይፈቅዱም ትንቢትን አብዝተዋል ” አለና ሽቅብ በደመና የጠቆረዉን ጨፍጋጋ ሰማይ ከተመለከተ በሃላ “ጉድጓድ የሚምስ ይወድቅበታል፥ ቅትርንም የሚያፈርስን እባብ ትነድፈዋለች” ሲል  ሁሌም እየደጋገመ የሚለዉን የመክብብን ቅዱስ ቃል አነበነበ።

እኔም ከንግግሩ በላይ የፊቱ ገፅታ ላይ እያነበብኩ ያለሁት ሐዘን የበለጠ አስፈራኝ። ያኔ ልጅ ሆኜ አዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት በፍቃዱ ተክለማርያም ኪናዊ አንደበት የሰማሁትን የቴዎድሮስ የሚያስፈራ ድልና ሽንፈት፡ ማግኘችትና ማጣት እርግማንና ንዴት  እንዲሁም የሞት አፋፍ ጣርና ቁጭት ስሰማ የፈራሁትን ያህል ፈራሁ።

ተስፋ ባጣ ምድረ በዳ
የአንድ ዕምነት ይሆናል ዕዳ
እናም ትንፋሼ አለሆነሽም …..ሆኜብሽ መራር መካሪ
እሩቅ አሳቢ ቅርብ አዳሪ።
እዉነት ላንቺ መች ተስፋ ናት ጉስቁል ልሳንሽን ነክሳሽ
ክንድሽን ካዛለ ቅርስሽ መጠላለፍ ሲሆን ዕጣሽ…

አዎን! በልጅነቴ የፈራሁትን ያህል አሁንም ምራቅ ዉጬ በሰሎሞን ቁጭት ፈራሁ። ጀግንነትን ሰዉ በማዳን ሳይሆን የንፁሐንን ሬሳ ብዛት አልያም ምርኮኛን በማዋረድ  በሚተረጉሙ መዓይማን እርኩስ መንፈስ ሕዝቤ መከበቡ ሲታወቀኝ ንግግሩ ይበልጥ አስፈራኝ።  በዚህች ሰዓት በጣር የሚቃትተዉ የህወኣት እርኩስ መንፈስ የመጨረሻዉን መርዙን ሊተፋ በአዲስ አበባና መቀሌ እየተወራጨ መሆኑም አሳሰበኝ ።  በቅርቡ ‘ጥቂት መስዋህትነት መክፈል ይኖርብናል’ ያለው  ደብረ ‘ሴይጣን’ ያኔ አዉዜን ላይ በቅርቡም ሶማሌና ኦሮሚያ ላይ ያደረገዉን አይነት የንፁሐን ደም ማፍሰስ መዘጋጀቱን ሳስብ በአጭሩ ሊቀጭ የተዘጋጀዉ የሕፃን አዛዉንቱ መንፈስ ጩኸት ዳግም ከመቅደላ የሚሰማ መሰለኝ።

መልመጥመጡ መሽቆጥቆጡ መስሎሽ ድንገት የሚያዋጣሽ
የእኔ እዉነት ሆነብሽ እዳሽ።
ወራሪም ፈጣሪን ላያቅ
የጣለዉም በስሏል እንጂ ወድቋል ብሎ ግፉ ላያልቅ
መች ትተርፊያለሽ ኢትዮጲያ ህዋስሽ አብሮኝ ካልሰራ….
አንገትሽ ብቻ መቅደላ አፋፍ ወጥታ ብታበራ
የቀረዉ ሰራ አካላትሽ በየጥሻዉ ተዘርሮ
ካባት በወረሽዉ ንፍገት ነፍዞ ደንዝዞ ተቀብሮ…..በአጉል ወጌሻ ታጅሎ
እኔን ለጥንባሳ ጥሎ…

ሰለሞን ንግግሩን ቀጠለ “ቢሆንም ተስፋ ይታየኛል። መሪዉን ለጥንባሳ የመጣያዉ ጊዜ አብቅቷል። ይህንንም ጥንባሳዉም ተረድቶታል። በመሆኑም መጪዉ አርማጌዶን ይሆናል ። ሁላችንም ማወቅ ያለብን እዉነት ደግሞ በመጨረሻ ሁልጊዜ አሸናፊ የሚሆነዉ የተቀደሰ መንፈስ ነዉ። ያ ባይሆን ኖር የሰዉ ልጅ ፍጥረት ከንቱ ይሆን ነበር። አርማጌዶንም የዚህ ዕውነት ምሳሌና መገለጫ ነዉ። ጥያቄ መሆን ያለበት ግን የእያንዳንዳችን ዉሳኔ ነዉ። ወደድንም ጠላንም ዉስጣችን ካለ መንፈስ ተመሳሳይ መንፈስ ጋር እናብራለን። ስለዚህ እራሳችንን እንመረምር ።” አለና በድንገት እጄን ይዞ  ” ዛሬ ሰኞ ነዉ። ሕሁድም ትንሳኤ ይሆናል ። በዕለተ ዓርብ ግን ስቃይና መከራ ይከፋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *