የብአዴን ካድሬወች አሳፋሪ ናቸው አሁን የቀራቸው ወፍጮ ቤት ገብተው መሰብሰብ ብቻ ነው !!!

በተለይ ወደ ታች ያለው የብአዴን ካድሬ በእህል አምልኮ የተለከፈ ይመስላል።ሁልጊዜ ስብሰባ ላይ ፍራፍሬ ፣ድፎዳቦ ፣እሸት ፣አነባበሮ ፣ድንች ፣ጥቅል ገመን ፣ቲማቲምና ቃሪያ …..ኧረ ስንቱ ይጠራል ?

እናም የምግብ ኤግዚቢሽን….የጓሮ አትክልት ኤግዚቢሽን ነው የሚመስለው ።

ምርት ለማሳየትም ከሆነ ከአዳራሽ ውጭጪ ዳስ ነገር አዘጋጅቶ በጠረጴዛ ላይ ማሳየት ይቻላል እኮ።እነርሱ ግን መድረኩ ላይ….ጠረጴዛው ላይ ….አይን አይኑን እያዩ ካልሆነ ትንፍሽ አይሉም።ቃላት አይመጣላቸውም።ሙዳቸው ይከነታል።

እኔማ የጉዳዩ መደጋገምና መብዛን ስመለከት በቀጣይ ደግሞ የቤት እንስሳትን ዶሮ ፣በግ ፣ፍየል ፣ላም ፣በሬ ፣አህያ ፣ፈረስ ወዘተ በዙሪያቸው እየኮለኮሉ እዩ ምርታችንን ።ውጤታችንን ብለው እንዳያቅራሩ ስሰጋ ነበር።

እሱን እንግዲህ በቀጣይ እንጠብቃለን።

አሁን ይሄን ብጥሌ ዳቦ ጠረጴዛ ላይ አድርጎ ስብሰባ መቀመጥ የጎጃምን ህዝብ መናቅ አይሆንም ?

ኧረ ህዝቡ ይታዘባችኋል።እንደው ካድሬነትን ወፍጮ ቤት አይም እህል መጋዘን ውስጥ ነው እንዴ የሰለጠናችሁት ?

ከዮሴፍ ይጥና !!!!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *