ዛሬ ይህ ሰው በሰው እጅ ላይ ወድቆ ይገኛል።እንዲህ እሆናለሁ ብሎ አስቦም አያውቅም።ተሽከርካሪ ወንበር እንጂ ዊልቼር ያጋጥመኛል ብሎም አላሰበም።የሰራውን እኩይ ስራ ግን እሱ ቢረሳው ፈጣሪ አይረሳውም።

ይህን ሰው ያውቁታል ?

የት እንዳለስ ያውቃሉ ?

ከአሜሪካ አገር ታክሲ ነጂነት ወደ ኢፌዴሪ አፈጉባኤነት በሹመት ሲያገለግል የነበረው ዳዊት ዮሃንስ የእነ ገነት ዘውዴ ዘመድ ሲሆን ከታናሽ ወንድሟ ከዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ ጋር በአንድ ቤት ያደገ ነው።

ይህ ግለሰብ በስልጣን ዘመኑ ያለ አግባብ የአንድ የተከበሩ ኢትዮጵያዊ ቤትን በስልጣን ጉልበት ቀምቶ ለራሱ መኖሪያ ያደረገ ሰው ነው ።

ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ ከገነይም ሆነ ከዚህ እርኩስ ሰው በተለየ ስርዓቱን የሚቃወሙና በዚህ አቋማቸውም ከአአዩ የፍልስፍና መምህርነት በግፍ እንዲባረሩ የተደረጉ ፅኑ አገር ወዳድ ናቸው።

ዶ/ር ዳኝኛቸው ዛሬም ኢትዮጵያዊነት እንዲያብብና የአንድነት መንፈስም እንዲናኝ በየመድረኩ ጉልህ ሚና እያበረከቱ ያሉ ምሁር ናቸው።

አብሮ አደጋቸው ዳዊት ዮሃንስ ግን በአንድ ወቅት የአድዋ በዓል ሲከበር የምኒልክ ሃውልት ስር የአበባ ጉንጉን ካስቀመጠ በኋላ “ኢትዮጵያ በታሪኳ የቱንም ጦርነት አሸንፋ አታውቅም።”ብሎ እነ መለስ በላኩት መሰረት ሃፍረት ሳይሰማው የተናገረ ሰው ነው።

ለመሆኑ ዳዊት ዮሃንስ ምነው ጠፋ ?

በሰው ላይ ግፍ የሚሰራ ድሮም የዘራትን ማጨዱ የማይካድ ሃቅ ነው።በእምዬ ኢትዮጵያ ላይ ያላገጠም እራሱ መላገጫ ከመሆን እንደማያመልጥም እሙን ነው።

እናም የቀድሞው አፈ ጉባኤ የዊልቸር ጉባኤ ከሆነ ዘመናትን አስቆጠረ።

እያንዳንዱ የስርዓቱ ሹምና አሽቃባጭም ከዚህ የባሰ እንጂ ያነሰ ነገር እንደማይገጥመው እሙን ነው።

በቆፈሩት ጉድጓድ መቀበር የማይቀር ነው።

ክፉን የዘራ ክፋትን ያጭዳል።

ዛሬ ይህ ሰው በሰው እጅ ላይ ወድቆ ይገኛል።እንዲህ እሆናለሁ ብሎ አስቦም አያውቅም።ተሽከርካሪ ወንበር እንጂ ዊልቼር ያጋጥመኛል ብሎም አላሰበም።የሰራውን እኩይ ስራ ግን እሱ ቢረሳው ፈጣሪ አይረሳውም።

ለማንኛውም ብዙ ዘመን ማቋልና ቀሪ ዘመኑ የንስሃና የምህረት እንዲሆንለት ምኞቴ ነው።

ዮሴፍ ይጥና

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *