ወያኔ ከጥንሱ ጀምሮ ይህን ትግል ጠምዶ የያዘው የመሪወችን ቆራጥነት እና የማያወላዳ የትግል ፅናትን በመገንዘብ እንጅ በሰራዊቱ ብዛት ወይም ባለው የመሳርያ ክምችት አይደለም!

Dawit Solomon
ብርሀኑ ነጋ እና ግንቦት 7 ይታማሉ!
🔥🔥🔥🔥💚💛❤️🔥🔥🔥

ሰሞኑን በ ብርሀኑ ነጋ እና በሚመሩት ንቅናቄ ላይ ብዙ ሀሜት ስድብ እና ፍርጃ የፌስ ቡክ መንደር እያስተናገደ ነው! ለምን በዚህ ወያኔ አፍንጫዋ ተይዛ ነፍስ ውጭ ነብስ ግቢ በምትልበት የ ቃውጢ ወቅት ? ለምን የ ጥንት የወያኔ አሽከሮች ለጌቶቻችን አንገዛም ባሉበት ወቅት ? መልሱን ለ እናንተ ትቸዋለሁ!
እኔ በተደጋጋሚ እንደምለው ወያኔን የሚቃወም እና የሚታገልን ማንኛውንም ሀይል እደግፋለሁ ለ እኔ ጠላቴ ወያኔ ብቻ ነው! አንድ አንድ የሚአቅለሸልሽ ስብዕና ያላቸው ሰወች እንዳሉ ሳልደብቅ! ጎበዝ የያዝነው እኮ ትግል ነው ! የ ሰው ህይወት የሚከፈልበት ትግል! ይህ ትግል ብዙ ወገኖችን አስገብሮናል! የቅርቦችን ለማስታወስ ያክል መሳፍንት ጥጋቡ (ገብርየ) አበራ ጎባው …ሌሎች በስም የማናውቃቸው ታጋዮች ተሰውተውበታል!

አንዳርጋቸው ፅጌን ጨምሮ ስንት እና ስንት ሰወች ጥፍራቸውን እየተነቀሉ! በዘይት የተቀቅሉበት የውስጥ ገላቸው እስኪገለበጥ የተገረፉበት ትግል ነው! ይህ ትግል መራራ እጅግ መራራ ነው!!! ስለዚህ ይህ መራራ እልህ አስጨራሽ ትግል ሚሊዮኖች በፀሎት በገንዘብ በህይወት የሚደግፉት የህዝብ ትግል ነው!

ወያኔ ከጥንሱ ጀምሮ ይህን ትግል ጠምዶ የያዘው የመሪወችን ቆራጥነት እና የማያወላዳ የትግል ፅናትን በመገንዘብ እንጅ በሰራዊቱ ብዛት ወይም ባለው የመሳርያ ክምችት አይደለም!

ብርሀኑ ነጋ !ይቅርታ ማዕረጉን እየደረደርኩ አላሰለቻችሁም ብየ እንጅ አርበኛ ታጋይ ብርሀኑ ነጋ የሚለውን ማዕረግ አላምንበት ሁኘ አይደለም!! ይህ ሰው በተፈጥሮ ደመ መራር ይመስለኛል ብዙ ቀንደኛ ጠላቶች በግለሰብ ደረጃ አፍርቷል ! ከ እነኝህ መካከል ልደቱ አያሌው ዋነኛው ሲሆን ሌሎችም ብዙ አሉ! እነዚህ ጠላቶቹ በየግዜው የሚፈበርኩት ስም እና ጥላሸት ብዙ ነው! ዋና ዋናወችን በዚህ ፅሁፌ ልዳስሳቸው!

1. ፀረ አማራ !
🔥🔥🔥🔥
መቼም በ እሱ ደረጃ ከልጅነቱ ጀምሮ እስከ አሁኑ እድሜው ድረስ ለነፃነት ያቀነቀነ! እህቶቹ በልጅነታቸው በመስዋዕትነት ሲወድቁ የታዘበ ታጋይ ለአንድ እሱ ሲታገልላት ለኖረችው ሀገር መሰረት የሆነን የህብረተሰብ ክፍል ይጠላል ብሎ ማሰብ ከባድ ነው! እስኪ እሱ ላይ የተለጠፈውን ጥላቻ ለጊዜው ተውት እና እንደሰው ልጅ አስቡት ከሰማንያ በመቶ በላይ አማራ የሆኑበትን ንቅናቄ እየመራ እነ ገብርየን የመሰሉ የ አማራ ልጆች ለህይወታቸው ሳይሳሱ እየወደቁ ያየ ሰው እንዴት እነ ገብርየ የወጡበትን ማህበረሰብ ይጠላል! ?

እነ አንዳርጋቸው እነ ነአምን እነ ገበየሁ አባጎራው እነ አሰፋ ማሩ የወጡበትን ማህበረሰብ እንዴት ይጠላል ተብሎስ ይታሰባል ? ይህ ሰው የተለየ ፍጡር ካልሆነ በስተቀር አማራን የሚጠላበት ምንም ምክኒያት የለውም! የወጣበት የጉራጌ ማህበረሰብም ሳይቀር የ አማራ ተለጣፊ ይባላል እንጅ አማራን የሚጠላ አይደልም ስለዚህ ፀረ አማራነትን ከየት ያመጣዋል?

2. በ ህዝቡ ገንዘብ ይነግዳል!
🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
ሲያሙት ያማል ይላል አባቴ እንዲህ አይነት ያልሆነ ሀሜት ሲገጥመው! እስኪ ማን ይሙት በሙሉ ፕሮፌሰር ማዕረግ ዩኒቨርስቲ የሚአስተምር ! ባለቤቱ የራሷ የህክምና ማዕከል ያላት ዘር አዛርቱ የሞላው የተረፈው ባለፀጋ ስንት ጉሮሮ ደርቆ የሚገኝ ብር በልጦበት በህዝብ ገንዘብ ሲነግድ? ይህ ሰው እኮ ወደ ትግሉ በመግባቱ ምክኒያት የተዘረፈበት ንብረት ብቻ እኛ እስካሁን ካዋጣነው ገንዘብ የብዙ እጥፍ ይሆናል!

ሰሞኑን የ ወያኔው ፍርድ ቤት በሀራጅ የ ፕ/ር ብርሀኑን እና የ አንዳርጋቸው ፅጌን ንብረት ወርሶ በሀራጅ በብዙ ሚሊየን እንደሸጠው የሰማነው ሀቅ ነው! እስኪ በ አንድ አመት የተዋጡትን አስልታችሁ አቅርቡ ! በ አሜሪካ ትልቅ የሚባል ገቢ የተሳባሰበው ስያትል ነው ካልተሳሳትኩ ወደ ሰባ ሺህ ይመስለኛል ! የሁሉንም ደምረን ቀንሰን ብናሰላ 300 ሺህ ይሞላል ? ከዚህ ውስጥ በርሀ ላሉ አርበኞች ምግብ :መጠጥ :አልባሳት ትጥቅ ተርፎ ለግላቸው ጥቅም ሲውል እስኪ አስቡት ? በሌላ አንፃር የፕ/ር ብርሀኑ እና የ ኤፍሬም የአመት የ አመት ገቢ ሲደመር ከ ሶስት መቶ ሺ በላይ እንደሆነ አውቃለሁ!

3. የ አርበኞ ግንቦት 7 ውስጥ የ አማራ ተወላጆች አናሳ ናቸው/የሉም

ለዚህ ጥያቄ ፕ/ር ብርሀኑ በአምስተርዳም በተካሄደው የአርበኞች ግንቦት 7 የተናገረውን ከደረጀ ሀብተውልድ ገፅ እንዳለ ወስጀዋለሁ!”ሲጀመር አርበኞች ግንቦት 7 ኀብረ ብሔራዊና መሰረቱን በዜግነት እንጂ በብሔር ላይ ያዋቀረ ድርጅት አይደለም። አንድ ሰው የድርጅቱ አባልም ሆነ አመራር ለመሆን ብሔሩ ከየትም ይሁን ከየት፣ኢትዮጵያዊ መሆኑ ብቻ በቂ ነው …..”
“….ይህ እንዳለ ሆኖ ፣ይህ መሰረታዊው ነገር እንዳለ ሆኖ፣ በብሔር ተዋጽዖ እናስላ ቢባል እ ….. ለምሳሌ የአማራ ሕዝብ ከአጠቃላይ የኢትዮጵያ ሕዝብ 30 በመቶውን ይሆናል ቢባል ፣ በአንድ ኀብረ -ብሔራዊ ድርጅት ውስጥ ካሉት አመራሮች 30 በመቶዎቹ አማራዎች መሆን አለባቸው። ሆኖም የተሰባሰብነው በኢትዮጵያዊነት አምነን እንጅ በብሔር ተመራርጠን ባይሆንም፣ከአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ 13 ሥራ አስፈፃሚዎች መካከል 8 ቱ አማራዎች ናቸው። ይህ ማለት ከአመራሩ የሚበልጡት ፣ማለትም ከግማሽ በላይ ወደ 60 በመቶ የሚሆኑት አማራዎች ናቸው ማለት ነው።ሀቁ ይህ በሆነበት ሁኔታ በአርበኞች ግንቦት 7 አመራር ውስጥ አማራዎች የሉም የሚለውን ሥርና ጫፍ የሌለውን አሉባልታ እነማን እንደሚያሰራጩት፣ከምን ተነስተው እንደሚያሰራጬትና ለምን ዓላማ እንደሚያሰራጩት አይገባኝም። የሚገርመኝ ግን ውሸት መወራቱ ሳይሆን ከዚህ ከማህበራዊ ሚዲያው መስፋፋት ጋር ተያይዞ በብዙዎቻችን ዘንድ የአንድን ወሬ ውሸትነትና እውነትነት የማረጋገጥ ባህል ጭራሽ መጥፋቱና አንዱ ከሜዳ ተነስቶ የሆነ ነገር ሲል ያንኑ ተቀብሎ ማስተጋባቱ ልማድ እየሆነ መምጣቱ ነው። እና የሚባለው ነገር ፍጹም ውሸት ነው።”

❤️💛💚
ወዳጆቼ ለመዳሰስ የሞከርኩት እነዚህን ነው !ሌሎችን እናንተ በጭዋ ደንብ ጠይቁ ተቹ ግን እባካችሁ በሀሰት እና በተንኮል ልብ አይሁን!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *