የወያኔ የዝንጀሮ ፓርላማ ተቋረጠ!!!!!!!

ሰበር ዜና ……….
የፓርላማው ስብሰባ ተቋረጠ
የኦሮሚያን ልዩ ጥቅም ላይ ለመወያየት የተሰበሰበው የፓርላማ ስብሰባ በመበጥበጡ ምክንያት በግድ ለሻይ እረፍት ተወጥቷል
አቶ አዲሱ አረጋ
1. 600 ሺ የኦሮሞ ተወላጆች በመከራና በየመጠለያው አስቀምጠን
2. ሕዝቡን እስከታች ወርደን ሳናወያየው እና የጋራ መግባባት ላይ ሳንደርስ ለብዙ ዓመት የቆየን አዋጅ ለማጽደቅ በዚህ ወቅት በዚህ አጀንዳ ላይ ለመነጋገር የምንጣደፍበት ምክንያት የለም ….. ስለዚህ ለመወያየት ዝግጁ ባለመሆናችን ውይይቱ እንዲበተን እጠይቃለሁ ሲሉ በሙሉ ጭብጨባ ድጋፍ አግኝተዋል
አቶ ሽመልስ የተባሉ ከኦህዴድ የመጡ አመራር ለውይይቱ ዝግጁ አይደለንም….. ህዝቡ ሳይወያይበት ዛሬ አጽድቀነው ነገ እንዴት ልንተገብረው ነው? ምክር ቤቱስ ሕዝቡ ያልተወያየበትን ለማጽደቅ እኛን ብቻ የሚጠራው ከምን አንጻር ነው? ስለዚህ እንደ ክልላችን ውይይቱ በሌላ ጊዜ ማድረግ ስለምንችል ስብሰባውን እንዲበተን እጠይቃለሁ ሲሉ ሌላ ጭብጨባ አጅቧቸዋል
የተከበሩ አቶ ግርማ መኮንን /ዶ.ር/ በምክር ቤቱ የአባላትን የአሰራር ደንብ ላይ ሕዝቡ የራሱን አስተያየት ሳይሰጥበት እዚህ መጥቶ መወያየቱ ለምን አስፈረገ? ቋሚ ኮሚቴው ይህን ስራ ሳይሰራ ይህን ውይይት መጥራቱ ለምን አስፈለገ? የምን ሱሪ በአንገት ነው? ሲሉ ተጨብጭቦላቸዋል
አቶ አባዱላ ገመዳ ውይይቱ ቢደረግ ጥሩ ነው ምንም ክፋት የለውም ሲሉ ተሰብሳቢዎቹ በአንድ ድምጽ በግድ ነው እንዴ? የደርግ ስርዓት ነው የምታራምዱት? ብሎ በጩኸት አቋርጣቸዋል ……አቶ አጽብሃ አረጋዊም ስብሰባው ቢደረግ ይሻላል ሲሉ ተሰብሳቢው በሙሉ አናደርግም ካልን አናደርግም ነው ብሎ ጥሏቸው ሲነሳ ባልታሰበ ሰዓት የሻይ ሰዓት ተብሎ ተሰብሳቢው ያለፍላጎቱ ቀጣዩን ሰዓት እንዲቆይ ተደርጓል
ከሻይ ሰዓት በኃላ ምን እንደሚሆን አልታወቀም ………………………………………………………………………………………………………….ከሻይ በኃላ ….አቶ አስመላሽ ወልደስላሴም አስተያየት ልስጥ ብለው ማስቀጠል ስላልቻሉ
በመጨረሻ የኦሮሚያን ልዩ ጥቅም ለማስጠበቅ የተጠራው የፓርላማ ስብሰባ ተቋርጧል
@Alamin Nuri

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *