አሁን ለዚህስ ግፍ ተጠያቂው ማነው ? ወዴትስ አቤት ይባላል ?

አሁን ለዚህስ ግፍ ተጠያቂው ማነው ?
ወዴትስ አቤት ይባላል ?
*★★★*

¶ የህወሓት [ #የከፍታው_ዘመን ] ይልኽሃል ይሄ ነው ። እድገታችን 11% አልፎ ወተት መድፋት ጀምረናል ። ጎበዝ መጪው ጊዜ #ከኢህአዴግ ጋር ብሩህ ነው.! እንበል እንዴ.?

¶ ወተት አልበውና ከገበሬው ገዝተው እንዲደፉት የተፈረደባቸው የዚህ ፋብሪካ ባለቤቶች ብሔራቸው ከነገደ #ዐማራ ወይም ከነገደ #ኦሮሞ ይሆን እንዴ ? መቼም በዚህ ዘመን ሁለቱ ብሔሮች ናቸው የፈረደባቸው ፤ አድማጭም የሌላቸው ።

¶ የኢትዮጵያው መንግሥት ይኽን የመሰለ ዘግናኝ ግፍ በቴሌቭዥን መስኮት እያሳየ ዘወትር ከኢትዮጵያ ውጪ የምትኖሩ ባለሃብቶች ኑ በሀገራችሁ ገብታች ኢንቨስት አድርጉ እያለ ላንቃው እስኪሰነጠቅ ይለፈፍልኛላ ። ወይ አለ ማፈር ።

¶ ደግሞ ይኼን ግፍ የፈጸመው ግንቦት 7 ፣ ኦነግ ፣ ሻአቢያ ፣ አልሸባብ ፣ ግብጽ ፣ ፀረ ልማት ኃይሎች ፣ ፀረ ተባይ ኃይሎች ፣ ኒዮ ሊበራሊስቶች ፣ የአቶ ለማ መገርሳና የአቶ ገዱ አንዳርጋቸው አመራሮች ፣ ቄሮ ፣ ፋኖዎች ናቸው በሉ አሏችሁ ። ምድረ በጥራቃ ሁላ !

#ETHIOPIA | #አዲስ_አበባ ¶ ዘገባው የሬድዮ ፋና ነው ¶ ለጨጓራችሁ እያሰባችሁ በተለይ ቪድዮውን በጥሞና ደጋግማችሁ ትመለከቱት ዘንድ ጋበዝኳችሁ ።

ታህሳስ 12፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) የጀነሲስ ፋርም እና የኢትዮጵያ የምግብ የመድሃኒት እና የጤና ክብካቤ አስተዳደር እና ቁጥጥር ባለስልጣን መካከል የተፈጠረው ውዝግብ በየዕለቱ 3 ሺህ ሊትር ወተት እንዲደፋ ምክንያት ሆኗል።

የጀነሲስ ፋርም የወተት ማቀነባበሪያ በተቋማት የምርመራ ውጤት ውዝግብ ምክንያት በየቀኑ 3 ሺህ ሊትር ወተት ለመድፋት ተገዷል።

★ እስካሁንም ከ129 ሺህ በላይ ሊትር ወተት በባዮ ጋዝ ውስጥ ማመንጫ ውስጥ ተጨምራል።

★ የተደፋው ወተት በገንዘብ ሲተመን ከ3 ሚሊየን ብር በላይ ዋጋ አለው።

ባለስልጣኑ ነሃሴ 25 ቀን 2009 ዓ.ም በጻፈው የቁጥጥር ሪፖርት በጀነሲስ ፋርም የወተት ምርት ላይ ከተቀመጠው መጠን በላይ የሆነ አፍላቶክሲን አግኝቻለሁ፤ የወተት አመራረት ስርዓቱም ጥራት ላይ ጫና የሚያሳድር ነው ብሏል።

ባለስልጣኑ ይህንን ካሳወቀ ሁለት ወር ከሁለት ቀን በኋላ የጀነሲስ ፋርምን የወተት ማቀነባበሪያን ጥቅምት 28 ቀን 2010 ዓ.ም አሸገ።

የኢትዮጵያ የምግብ፣ መድሃኒት እና የጤና ክብካቤ እና አስተዳደር ቁጥጥር ባለስልጣን ከገበያ ናሙና ወስጄ ባደረኩት ምርመራ በጀነሲስ ፋርም የወተት ምርት ላይ ከፍተኛ የአፍላቶክሲን መጠን አግኝቻለሁ ይላል።

የወተት ማቀነባበሪያ ድርጅቱ ደግሞ የባለስልጣኑን ውጤት በሰማ ማግስት የወተት ምርቱን አስመርምሮ ሙሉ በሙሉ ከአፍላቶክሲን ነፃ ነው መሆኑን በምርመራ ያረጋገጠበትን ሰነድ ያቀርባል።

በዚህ መካከል ግን የማቀነባበሪያ ድርጅቱ የታሸገ ሲሆን፤ አሁን ላይ ከላሞች የሚታለበው እና ከአቅራቢዎች የሚገዛው ወተት እየተደፋ ይገኛል።

በድርጅቱ ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች እያለቀሱ የወተቱ መደፋት እንዳሳዘባቸው እነሱም የስራ ማጣት እንደተጋረጠባቸው ይናገራሉ።

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ባረጋገጠው መረጃ ስለወተት ማቀነባበሪያው መከፈት እና ስላሸገው አካል ማንነትም በሁለት የመንግስት ተቋማት መካከል ውዝግብ አለ።

በማሸጊያ ወረቀቱ ላይ ማህተሙን ያሳረፈው የኢትዮጵያ የምግብ መድሃኒት እና የጤና ክብካቤ እና አስተዳደር ቁጥጥር ባለስልጣን ብቻዬን ስላላሸግኩ ብቻየን መክፈት አልችልም የሚል አቋም አለው።

በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ምርመራ ቢሮ የንግድ እና የሸማቾች ዳይሬክቶሬት ደግሞ እኔ በማሸጉ እጄ የለበትም፤ ያሸገው ባለስልጣኑ ነው ሲል የቃል ምላሽ ሰጥቶናል።

የባለስልጣኑ የስራ ሃላፊዎች ስለማቀነባበሪያው የመታሸግ ምክንያት፣ እስከመቼ ታሽጎ ይቆያል በሚለው ጥያቄ እና አገኘን ስለሚሉት የአፍላቶክሲን የምርመራ ውጤት ሲጠየቁ ዝርዝር መረጃውን በዚህ ሳምንት መስጠት አንችልም ብለዋል።

አ ከ ተ መ ።

እኔ ግን ስጠረጥር ፣ መጠርጠር ነው ያልኩት እንዲያው ስጠረጥር የሆነ ሰው የዚህ ድርጅት አይነት ተመሳሳይ ድርጅት እየከፈተ ይሆናል ። ወይም ከፍቷል ። ወይም ሊከፍት አስቧል ። ወይም ደግሞ።እስቲ እናንተ የምትጠረጥሩትን ጥርጣሬ ጠርጥራችሁ አካፍሉን ። ወይ ሀገሬ ኢትዮጵያ ! ወይ ዘመነ ህወሓት ። መቸም የማታሳየን ጉድ የለም ።

ዘመድኩን በቀለ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *