ከአክሱም ዩኒቨርሲቲ የተፈናቀሉ ተማሪዎች ጎንደር ገቡ! ህዳር 12 2010

ከአክሱም ዩኒቨርሲቲ የተፈናቀሉ ተማሪዎች ጎንደር ገቡ!
ህዳር 12 2010

ከአክሱም ዩኒቨርስቲ 42 ተማሪዎች ለደህንነታቸው ዋስትና አጥተው ወደ ጎንደር መጥተዋል። ለጊዜው የት ከተማ እንዳሉ ከመግለፅ ተቆጥበናል። በህዝብ ድጋፍ ጊዜያዊ ማረፊያ ተዘጋጅቶላቸው በሰላም አድረዋል። ተማሪዎቹ አብዛኛውን የአማራ ብሄር ተወላጆች ቢሆኑም ኦሮሞወችና የሌሎች ብሄር ተወላጆች አብረው መምጣታቸው ታውቋል። ልክ ባለፈው ዙር ከአዲግራት ዩኒቨርሲቲ ሸሽተው እንደመጡት እነዚህ ተማሪዎችም ወደየቤተሰቦቻቸው መኪና ተዘጋጅቶ እንዲመለሱ ህዝብ እየተባበራቸው መሆኑ ተነግሯል። ምስጋና ለጎንደር ህዝብ።
AsnakewAbebe

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *