ወያኔ ቆስላ ሊሆን ይችላል ግን ጨርሳ የ አልጋ ቁራኛ አልሆነችም …ደክማ ሊሆን ይችላል ግን ሽባ አልሆነችም

ከፈንጠዝያው ባሻገር
🌹🌹🌹🔥🌹🌹🌹

ከ ትቂት ወራት በፊት ትቂቶች ፈራ ተባ እያለ ሳንወድ በግድ ልባችን እየሸፈተ ወደ ለማ አድናቂነት ዘው ብሎ ሲገባ…ብዙወች አሽሟጠጡን …ሳቁብን ….ተከራከሩን ..

መሬት የረገጠው እውነታ እየደገፈን ሌሎች አክቲቪስቶች እየተቀላቀሉን ከ እንቦጭ እሰከ ባህርዳሩ የፍቅር ድግስ እያጀቡን….ተጉዘን ተጉዘን ….ዛሬ ላይ ደርሰናል…አሁን ነገሩ ለሁሉም ይፋ ሁኖ ከ ደጉ እና ለማ ጀምሮ እስከ ጮፌ ዶንሳ የቀበሌ ካድሪወች ድረስ የ ኦሮማራን ጥዑመ ዜማ እያንቆረቆሩት ነው…

ከያኒው ቴዲ ፍቅር ያሸንፋል ብሎ ሲዘፍን ከዘፈኑ ጣዕም እና …ከ ሀሳቡ ፅድቅነት ውጭ ፍቅር የ 27 አመቱን የጥል ግድግዳ ደርምሶ ያሸንፋል ብሎ ያሰበ ቢኖር እሱ በ እውነት ነብይ ነው…

አሁን ስለ አማራ እና ኦሮሞ ፍቅር ማዜም እና መቀኘት ከብዙ ሺህ ቅኝቶች ውስጥ ሚጢጥየ ጭማሪ ካልሆነ በስተቀር …ብዙም ድንቅ ነገር አይሆንም .ጫልቱ እና ከበቡሽ ሄለን እና ሰሚራ አብረው እየዘመሩት ነውና🙂!

የ እኔ ፅሁፍ ዓላማ…ከዚህ ፌሽታ ማዶ ምን ይጠብቀናል? ምንስ ተደግሶልናል ? ይህን ደስታ እንዳይነጥቁን ምን ማድረግ አለብን ? የሚለውን ቆም ብለን እንድናስብ ለመጋበዝ ነው…

ወያኔ ቆስላ ሊሆን ይችላል ግን ጨርሳ የ አልጋ ቁራኛ አልሆነችም …ደክማ ሊሆን ይችላል ግን ሽባ አልሆነችም ስለዚህ …የቆሰለ ውሻ አደገኛ ስለሆነ ሁላችንም በ ጥንቃቄ እንጏዝ …ወይኔ እንዲህ ሊአደርግ ይችላል ይህን ይፈጥራል እያልኩ …እንደ ደህንነት አማካሪ ያለሙያየ አልዘባርቅም …እንደ አንድ ለሀገሩ የሚጨነቅ ኢትዮጵያዊ ከፈንጠዝያው ባሻግር የሚኖረውን ቁመን እንድናስብ መጠቆም ስለፈለግሁ ይህን አልኩ… ከዳዊት ሰለሞን

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *