ኦህዴድ ቁጭ ብሎ የቁማር መጫወቻ ከመሆን ስብሰባውን ረግጦ መውጣት ይጠበቅበታል!

የ ኢሀዴግ ስብሰባ !
🔥🔥🔥🔥🔥🔥

ኢሀዴጎች ለስብሰባ ተቀምጠዋል! ለጊዜው ተቋርጦ የነበረው ስብሰባ ቀጥሏል! አሁን ያለው የ ኢሀዴግ ስራ አስፈፃሚ አወካከል ለህውሀት ባደላ መልኩ የተዋቀረ ስብስብ ነው 5 ሚሊየን የማይሞላ ህዝብ እወክላለሁ የሚል ወያኔ ከ ሶስት እጥፍ በላይ የሚወክሉትን ብአዴን ኦህዴድ እና ደህዴን ጋር እኩል 9 አባላትን ይዞ የቀረበው ህውሀት በበላይነት የሚመራው ኢሀአዴግ ተሰብስቦ የሚረባ ነገር ይወስናል ብሎ መጠበቅ የዋህነት ነው!

ኦህዴድ ሙሉ በሙሉ ህውሀትን ተቃውሞ እንደሚወጣ ቢጠበቅም ከ ብአዴን እንደዛ አይነት አቋም ስለማይጠበቅ ኦህዴድ በድምፅ መሸነፉ አይቀርም! እርግጥ ነው ከ ኦህዴድ ጋ የሚቆሙ ትቂት ብአዴኖች ቢኖሩም እንደ እነ አለምነው እና ደመቀ መኮነን አይነት ገልቱወች ከ ህውሀት ሀሳብ ይወጣሉ ብሎ ማሰብ ራስን ማሞኘት ነው! የ ሀይለማርያም ደሳለኝ ደኢህዴን ከ ህውሀት ሀሳብ አንዲት ኢንች ፈቀቅ አይልም!

ደግነቱ በ አባላት ጉዳይ የሚወስነው ኢሀዴግ ሳይሆን ድርጅቶች በመሆናቸው ለማ ይታሰር ወይም ዶር አብይ ይታሰር ብሎ መወሰን ኢሀዴግ አይችልም እንጂ ቢችል ይወስን ነበር! ይህ የ ኢሀዴግ ስብሰባ ሊአደርግ የሚችለው! ምንድን ነው ?እርግጥ ነው የ ኢሀዴግ ስብሰባ ውሳኔ የሚተገበረው በ ፓርላማ ነው ፓርላማው ውስጥ የ አማራ እና የ ኦሮሞ ወንበር ከግማሽ በላይ ስለሆነ የ ኢሀዴግ ውሳኔ ተግባር ላይ ለማዋል የሚቻል አይደለም ቢሆንም የሚከቱሉት ነገሮች ላይ ሊወስን ይችል ይሆናል!

1. የ ክልል መንግስታት ስልጣን የሚሸራረፍበትን
ሁኔታ መወሰን

2. የተለመደውን የ ፌደራል ጣልቃ ገብነት የበለጠ ማስፋት

3. የ ክልል ሚዲያወችን አፍ ማዘጋት

4. የ ክልል ፓሊሶችን አቅም ማሳጣት

5. ኦህዴድ እና ብአዴን ውስጣችሁን ፈትሹ የ ችግሩ መንስኤ እናንተ ናችሁ ብሎ ማሸማቀቅ እና ለመሰነጣጠቅ መሞከር

ኦህዴድ ቁጭ ብሎ የቁማር መጫወቻ ከመሆን ስብሰባውን ረግጦ መውጣት ይጠበቅበታል! ስብሰባውን ረግጦ ወጣ ማለት ኢሀዴግ ፈረሰ ነው! ከባድ ውሳኔ ቢሆንም በወያኔ ሰይፍ ከመበላት የሚድነው በዚህ መንገድ ብቻ ነው!

ወያኔ ይውደም ! ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር

ዳዊት ሰለሞን

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *