ኦሮሚያ ክልል አዲስ አበባ ዙሪያ አለም ገና ወለቴ በአማራ ተወላጅ ወገኖች ላይ የሕይወትና የንብረት ጉዳት እንደደረሰባቸው

ሰበር ዜና!”
በኦሮሚያ ክልል አዲስ አበባ ዙሪያ አለም ገና ወለቴ በአማራ ተወላጅ ወገኖች ላይ የሕይወትና የንብረት ጉዳት እንደደረሰባቸው ከአካባቢው በደረሰን መረጃ ለማወቅ ተችሏል፡፡ በአለም ገና ዙሪያ ለዘመናት የኖሩ አማሮች ዛሬ ለሊት ጨለማን ተገን ተደርጎ የመኖሪያ ቤታቸውን በር እየተሰበረ ወደውስጥ ዘልቆ በመግባት በዱላ መጨፍጨፋቸው ከተጎጂዎች ለማወቅ ተችሏል፡፡ ከመሬታችን ልቀቁ በሚሉ ኃይሎች አቶ ሙልጌታ ተሰማ የተባሉ የአማራ ተወላጅ በሕይወት እንዳይተርፉ ተደርገው በመደብደብ የሞት ሰላባ ሆነዋል በርካቶች ቆስለው ወደ ሆስፒታል ገብተዋል፡፡ ይህ አሳፋሪ ድርጊት ሰፊውን የኦሮሞ ህዝብ አይወክልም በአማራ ጠል ዘረኛ አገዛዝ ሆን ተብሎ የተሸረበ እልቂት መሆኑ ይታወቅ፡፡ ከስንታየው ቸኮል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *