ጌታቸው አሰፊ ርጉም ሰው ነው! ሰውየው እጅግ በጣም ደንቆሮ እና እብሪተኛ መሆኑን የ ዊክሊክ መረጃ አብራርቷል!

ጌታቸው አሰፋ እና አብዲ ሙሀመድ
🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
ጌታቸው አሰፊ ርጉም ሰው ነው! ሰውየው እጅግ በጣም ደንቆሮ እና እብሪተኛ መሆኑን የ ዊክሊክ መረጃ አብራርቷል! አዲስ አበባ ካለው የ አሜሪካ አምባሳደር ጋር ያደረገውን ውይይት በዊክሊክ ላነበበ ሰው የዚህን ሰው እብሪት እና ድንቁርና መገንዘብ ይችላል! በነገራችሁ ላይ ጌታቸው አሰፋ ላይ መለስ ጥርስ ነክሶበት ነበር አንድ ቀን ሊመታው ሲአደባ ሞት ቀደመው! ጌታቸው አሰፋም በሚስቱ በቀሉን ተወጣ! ይህ ሰው እጅግ በጣም በቀል የተጠማ አረመኔ ነው!

ጌታቸው አሰፋ አሁን በ አሸናፊነት ብቅ ብሏል ለጊዜው አዜብ እና አባይ ወልዱ የተሸናፊነት ፅዋን ቢጎናፀፉም ሌሎች እጅ የሰጡ በመጨረሳ ስአት ያጎበደዱ ይኖራሉ! አዘለም አቀፈ የ ጌታቸው አሰፋ የበቀል ሰይፉ ሊበላቸው የተዘጋጁ አሉ!

ባለፈው አመት ገደማ አብዲ ሙሀመድ ጌታቸው አሰፈ ላይ ያለውን ተቃውሞ እና ቅራኔ በድፍረት ሲገልፅ ይህ ሰው ምን አይነት ደፋር ልብ ቢኖረው ነው የሚል አግራሞት ነበረኝ ! ለካስ ነገሩ ሌላ ነው የምስራቅ እዝ የ ጦር ጀኒራሎች አብዲን አይዞህ ስለሚሉት እና የ እነሱም ሙሉ ጥበቃ ስላለው ጌታዋን የተማመነች በግ እንዲሉ ደረቱን ነፍቶ ጌታቸው አሰፋን ያንጏጠው ነበር!

አብዲ ሙሀመድ እንደ ጌታቸው ያለ ጨካኝ እብሪተኛ እና ደንቆሮ ነው! ህውሀት አብዲን በብዙ መልኩ ተጠቅሞበታል! መጀመሪያ በክልሉ ይንቀሳቀስ የነበረውን የ ኦብነግ ሀይል አዳክሞበታል! ኦጋዴን ውስጥ የሚደረገው አፈና ደግሞ ከህውሀት አፈና በ እጅጉ ይበልጣል! አንድ በውጭ ሀገር የሚገኝ የ ኦጋዴን ተወላጅ ከ ኦብነግ ጋ ከታየ ወይም ጅጅጋ ላይ ስለሚደረገው አፈና በፌስቡክ ከፃፈ ወይም አብዲ አሊን ካልደገፈ አገር ቤት የሚገኙ ዘመዶቹ ታስረው እየተደበደቡ ይቅርታ እንዲጠይቅ ይገደዳል ሳይወድ በግድ ለዘመዶቹ ሲል አብዲ ሙሀመድን ይደግፋል! ሰሞኑን በ እስር ቤት የሞተችው አዛውንት ታሪክ ከዚህ ጋ ይገናኛል!

በቂም በቀል ተኮኩቶ ያደገው ጌታቸው አሰፋ ተቀናቃኞቹን ሽባ ካደረገ በሗላ ወደ አብዲ ሙሀመድ ሊዞርበት በማኮብኮብ ላይ ነው ለዚህ ደግሞ ራሱ ህውሀት አዞ ያስፈፀመው የ ኦሮሞወች እልቂት እና መፈናቀል ጥሩ መክሰሻ ሁኗል! መረጃን ከ አለቆቹ ከጀኒራሎች የሚአገኘው አብዲ አሊ ቀኑ እንደዘነበለበት ገብቶታል በወቅቱ ቀንደኛ ተዋናይ የሆኑ አሽከሮቹን እንዲሸሹ ነግሯል ! እሱም ወይ ይሸሻል ወይ ይቀድሙት እና ይያዛል! የ አብዲ አሊ መያዝም ሆነ ሌላ የ ጌታቸው አሰፋን አሸንፎ መውጣት እንጂ የህውሀትን መታደስ አያመለክትም!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *