ኦሪት ዘ ህወሓት . በመጀመሪያ ህወሓት ነበር። ህወሓትም በደደቢት በበረሃ ይኖር

ኦሪት ዘ ህወሓት .
በመጀመሪያ ህወሓት ነበር። ህወሓትም በደደቢት በበረሃ ይኖር
ነበር። ህወሓትም እንዲህ አለ። “በአምሣያችን ኦህዴድን እና
ብአዴንን እንፍጠር”! ህወሓትም ኦህዴድን እና ብአዴንን
ከኢህአፖ የበረሃ ቅሪቶች አበጃቸው። በአፍንጫቸውም
የህወሃትን ማንፌሥቶ እፍ አለባቸው። ህወሃትም እንዲህ
አላቸው! “እነሆ የሚቃወሙትን ግደሉ፣ የሚታሠረውንም እሠሩ፣
የሚዘረፈውንም ሁሉ ዝረፋ፣ ተቆርሦ የሚሠጠውንም መሬት
ሳትሰስቱ ስጡ፣ በዚያ በነገሳቹበት ያለውን ሁሉ እንደኔ ሆናቹ
ግዙ፣ ሁሉን ታደርጉ ዘንድ ይቻላቹዋልና። እንደቃሉም ሆነ
በሺዋች የሚቆጠሩም ሞቱ የቀሩት በየእስርቤቱ እንዲሰቃዩም
ሆነ ..መሬትም ንብረትም ተዘረፈ…ህወሀትም ይህን ባየ ግዜ
ደስ አለው በልቡም ሀሴትን አደረ አንድ ነገር ግን ፈጽሞ
እንዳታደርጉ አላቸው። ይኸውም ህወሃት ለምን የበላይነቱን ያዘ
ብላቹ እንዳትጠይቁ። ይህን በጠየቃቹ ጊዜ የሞት ሞትን
ትሞታላቹ” አላቸው።
.
እነሱም የፈጣሪያቸውን ትዕዛዝ አንዲትም እንኳን ሣይሸራርፍ
እንደተባለው ሲያደርጉ እንሆ 26 አመታትን ኖሩ። ህወሃትም
ኦህዴድን እና ብአዴንን በመፍጠሩ አንዳች አልተጸጸተም።
እነሱም እንዳታደርጉ የተባለውን የስልጣን እና የህይወት ዛፍ
አንዲትም እንኳን ቅርንጫፍ አልነኩምና። አሁን ግን አፈነገጡ
እርሱም በመፍጠራቸዉ ተጸጸተ… ፈራ, ደነገጠም, ….
ይቀጥላል …

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *