አቶ አብዲ ሙሃመድ ከአገር እንዳይወጡ መታገዳቸው እየተሰማ ነው።

መረጃ
ጅጅጋ ዛሬ ጸጥ ብላለች። የመከላከያ አባላት በብዛት ይታያሉ። አቶ አብዲ ሙሃመድ ከአገር እንዳይወጡ መታገዳቸው እየተሰማ ነው። በቁም እስር ላይ ናቸው የሚል ወሬም በከተማው በብዛት እየተናፈሰ ነው። ሌሎች ባለስልጣኖች መደናገጣቸውም እየተነገረ ነው። ህወሃት በአቶ አብዲ ጉዳይ ላይ ከሁለት ተከፍሎ ቆይቷል። አንደኛው ቡድን ፕሬዚዳንቱን በማሰር የህወሃትን ገጽታ መልሶ መገንባት ይቻላል የሚል ሃሳብ አቅርቦ ነበር።

ኢሳት ፕሬዚዳንቱ በቁም እስር ላይ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማሰባሰብ ጥረት በማድረግ ላይ ነው። በጅጅጋ የምትገኙ ኢትዮጵያውያን በከተማው ያለውን እንቅስቃሴ በተመለከተ ተጨማሪ መረጃዎችን እንድትልኩን በአክብሮት እንጠይቃለን።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *