ትንታጉን ጋዜጠኛ ተመስገን አክባሪ ጀግኖች በሚአደርጉለት ማበረታቻ እያገገመ ነው!

ጀግናን ማክበር ሺ ጀግና ያፈራል
ዳዊት ሰለሞን
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
ትንታጉን ጋዜጠኛ ተመስገንን ወያኔ ጋዜጣው እስኪታተም እየጠበቀች ስታሽግ ስታከስረው ኑራ መጨረሻ ወህኔ አስገብታ አሳር መከራውን አብልታ ወጣት ሁኖ የገባ ልጅ ከሰውነት ዘር አውጥታ …..ሰውነቱን አበሳቁላ ብትለቀውም ጀግናን አክባሪ ጀግኖች በሚአደርጉለት ማበረታቻ እያገገመ ነው!

ይህ ጀግና ወንድማችን ምንም ቀሪ ገንዘብ የለውም በተለያየ ጊዜ አክስረውታል ከዛ ላይ ይህን ያህል ጊዜ ሲታሰር ቤተሰብ ላይ የደረሰ ፋይንይስ መቃወስ ቀላል አይሆንም! ይህን የተረዳው የደቡብ አፍሪካ አገር ወዳድ ህዝብ ተሜን መልሶ ለማቋቋም እና ለ ህክምና የሚሆን ያቅማቸውን መለገስ አሰቡ አስተባብረው ገንዘብ አዋጡ እና 61,400.00 ( ስልሳ አንድ ሺ እእራት መቶ ) ብር ለግሰዋል!

እኛም አምሳ ሎሜ በሚለው መርህ ያቅማችን ብንለግስ አንድ ጀግና ለትግል እንደገና ማብቃት ! ብቻ ሳይሆን ይህን እያዩ ሺ ጀግኖች ይነሳሉ ብየ አስባለሁ ! ጀግናን ማፍራት የሁላችን ሀላፊነት ነው!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *