ኮበሌወች ውርደትን ባርነትን ስደትን እንጅ ሞትን አይፈሩም ለሀገር በክብር ለመሞት ቆርጠው ተነስተዋል::

🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
ኮበሌወች መጡላችሁ
💚💛❤️🔥💚💛❤️
ኮበሌ ማለት ምንድን ነው ለምትሉ አንባቢወች! ኮበሌ ማለት አፍለኛ ጎረምሳ ! እሳት የላሰ እሳት የጎረሰ ወጣት የነብር እጣት የሚባለው ነው! ኮበሌ የኦሮሞ ቄሮወችን የሚቀራረብ ትርጉም አለው!

ኮበሌወች ከታሪካዊዋ ከተማ ጎንደር መነሻቸውን አድርገው በ ሁሉም የ አማራ ክልል እና ሌሎች ከተሞች ለማሳረግ አልመዋል ! እውነቱን ለመናገር የቄሮወች የትግል ስልት እንዳነሳሳቸው እና እነሱም ከቄሮውች ተሞክሮ ቀስመው የራሳቸውንም ነገር ጨምረው ከተቋቋሙ ቆየት ብለዋል!

ኮበሌወች በ እናት ሀገራቸው ኢትዮዽያ እና በባንዴራቸው አይደራደሩም ! ኮበሌወች ማንንም አይነቅፍም ወይም ማንንም አይጣሉም ኮበሌወች ከ አማራ ኮረብቶች ላይ ወጥተው ጅራፋቸውን እያጮሁ ነው! ኮበሌወች መሰደድ እና ለ አረብ ባርነት መሸጥን ተፀይፈው በሀገራቸው ምድር ነፃነታቸውን ለማስከበር ቆርጠው ተነስተዋል ከ ቄሮወችም ጋ እየተነጋገሩ የ ትግል ተሞክሮ እየቀሰሙ እንደሆነ ሰምቻለሁ!

ኮበሌወች ውርደትን ባርነትን ስደትን እንጅ ሞትን አይፈሩም ለሀገር በክብር ለመሞት ቆርጠው ተነስተዋል:: ኮበሌወች የ እኛን ድጋፍ በጣም ይፈልጋሉ ! ኮበሌወች ስራቸውም መሰረታቸውም ኢትዮጵያን ነው ! ኮበሌወች ኮምፒተር ጀርባ ቁጭ ብለው የሚጎፈሉ አይደሉም ! ኮበሌወች መሬወች ናቸው! ሁሌም እንዲህ ይላል —

🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
ትመር እንደሆነ ምረር እንደ ቅል
አልመር ብሎ ነው ዱባ ሚቀቀል
🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥

ኮበሌወች በሞታቸው ሀገራቸውን ነፃ ሊያወጡ ቆርጠው ተነስተዋል ! የ እማራ ወጣቶች ህብረት
-ኮበሌወች ተነስ ወጣት የ ነብር እጣት ተቀላቀለን የሚል ጥሪ ለ አማራ ወጣቶች አስተላልፈዋል!
💚💛❤️🔥🔥🔥💚💛❤️
ኮበሌወች መጡ
እሳት ልሰው እሳት ጎርሰው
💚💛❤️🔥🔥💚💛❤️
ማሳሰቢያ
እኔ የኮበሌወች አባል አይደለሁም! ኮበሌወች እሳት ጎርሶ እሳት ልሶ ለመሞት እና ለመግደል የተዘጋጀ እንጂ እንደ እኔ ከ ኮምፒተር ጀርባ የሚፎክር አይፈልጉም!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *