ዳንኤል ክብረት የማይቀድስ ሆድ አደር የክብር ዲያቆን ነው።

አለምነው መኮንን እና ዳንኤል ክብረት ምንና ምን ናቸው?
*አለምነው መኮንን የብአዴን ፅ/ቤት ኃላፊ
*አማራን ትምክህተኛ ልጋጋም ብሎ ብሎ የተሳደበ በሆዱ የሚያስብ ሆዱ አምላኩ የሆነ ግለሰብ ነው።
ዳንኤል ክብረት የማይቀድስ ሆድ አደር የክብር ዲያቆን ነው። ከወያኔ ጋር የጥቅምና የስጋ ጋብቻ በመፈጸም ለወያኔ ያጎበደደ መንፈሳዊ ካድሬ ነው። በፎቶው ላይ በአንድ ተርታ ከብአዴን ምርጥ ቅልቦች ላይ የመጀመሪያ ወንበር ላይ ከዳንኤል በስተቀኝ ሁለተኛ ወንበር ላይ አብሮት የተቀመጠው አለምነው መኮንን ነው። ሁለቱም የወያኔ ግብረ በሎች አማራን በንግግራቸውና በጽሁፊቻቸው በማወረድና በመዝለፍ አንደበታቸውን ለወያኔ በማከራየት ያሳደፉ ነውረኞች ናቸው። አለምነህ አማራን የሰደበውን እንደገና በመጻፍ ዳግም አኩሪ ታሪክ ያለውን የአማራ ተወላጆችን አልሳደብም። ዳንኤል በብሎጉ የጎንደር ዘመነ መንግስትን በተለይም ስመ ጥሩ ጀግናው አጼ ቴዎድሮስን ከዘለፈው እቀነጭባለሁ። የዳንኤል ሙሉ ዘለፋ እንዳለ በመጻፍ ጀግኖቻችንን እንደ ወያኔው ግብረ በላ ዳንኤል ታሪካቸውን አላሳዳፍም።

የደጃች ……….. ልቅሶ (በወያኔው ግብረ በላ ዳንኤል ክብረት)
«ዐፄ ቴዎድሮስ በበጌምድር ማንም ለሞተ ዘመዱ እንዳያለቅስ የሚል ዐዋጅ ዐውጀው ‹ሰው ሁሉ ዕንባውን ያጠጣ ነበር፡፡› በዚህ መካከል ደጃች ውቤ ሞቱና ለእቴጌ ጥሩ ወርቅ ወደ መቅደላ መርዶ ተላከ፡፡ ዐፄ ቴዎድሮስም ሕዝቡን ‹ለደጃች ውቤ አልቅሱልኝ› ብለው አዘዙ፡፡ ሰውም ሁሉ ዘመዱ ሲሞት የቀረበት ልቅሶ ያን ጊዜ ወጣለት፡፡ ይህንን ያየች የበጌምድር አልቃሽ
የኔታ ደጅ አዝማች ሁልጊዜ ደግነት
ዛሬ እንኳን ለድኻው ዕንባ አስተረፉለት
ብላ ገጠመች ይባላል፡፡
ያን ቀን በበጌምድር ወጥቶ የማያውቅ ሰው አደባባይ ወጥቶ፣ ተለቅሶ የማያልቅ ልቅሶ ተለቀሰ ይባላል፡፡ ከወጣው በጌምድሬ መካከል ደጃች ውቤን የሚያውቃቸው፣ ለደጃች ውቤም ያለቀሰላቸው ጥቂት ነው አሉ፡፡ አብዛኛው ሰው ያለቀሰው ከዚህ በፊት ለሞተውና ተከልክሎ ሳያለቅስለት ለቀረው ዘመዱ ነበር፡፡ በየማርገጃው የወረደው ሙሾ ደጃች ውቤን ከሚያስታውስ ይልቅ ቴዎድሮስን የሚወቅሰው ይበዛ ነበር አሉ፡፡ በዚህ የተነሣ የደጃች ውቤ ልቅሶ በድምቀቱ ተወዳዳሪ አጥቶ ይኖራል፡፡
ምክንያትና ሰበብ ይለያያሉ፡፡ ምክንያት የአንድ ነገር መነሻ ሥር መሠረቱ፣ ቫይረሱና ጀርሙ፣ መንሥኤውና መብቀያው ነው፡፡ ሰበብ ግን ያ በአንዳች ምክንያት ሲበቅል፣ሲያድግ፣ ሲጎነቁል፣ ሲከካ፣ ሲቦካ የኖረ ጉዳይ የሚገለጥበት ምቹ አጋጣሚ ነው፡፡ ‹እንኳን እናቱ ሞታ እንዲያውም አልቅስ አልቅስ ሲለው› የኖረ ሰው ‹ዋይ› ብሎ የሚወጣለት ቀን፡፡ የበጌምድርን ሰው በነቂስ ወጥቶ እንዲያለቅስ ያደረገው ምክንያት የደጃች ውቤ መሞት አልነበረም፡፡ የቴዎድሮስ አስተዳደራዊ በደል እንጂ፡፡ ዐፄ ቴዎድሮስ ሞጣ ሄደው ሬሳ በሬሳ አድርገውት ሲመጡ
ሞጣ ቀራንዮ ምነው አይታረስ
በሬሳ ላይ መጣሁ ከዚያ እስከዚህ ድረስ
ተብሎ ተለቅሷል፡፡ ንጉሥ ግን አልሰሙም፡፡
ሸዋ ወርደው የሰውን እጅ እየቆረጡ ገደል ሲከቱትም
ዐፄ ቴዎድሮስ እጅግ ተዋረዱ
የሸዋን ሰው ሁሉ እጅ ነሥተው ሄዱ ተባለ፡፡ ንጉሥ ግን አልሰሙም፡፡
ጎጃም አገው ምድር ሄደው የደጃች ጓሉን ሠራዊት ገጥመው ድል ካደረጉ በኋላ የተማረከውን ስምንት ሺ ሠራዊት እንደ ከብት አሳርደው ባደሩ ጊዜ
አንጥረኛው ብዙ ከንጉሡ ቤት
ባል አልቦ አደረጉት ይኼን ሁሉ ሴት
ተብሎ ተለቀሰ፡፡ ንጉሥ ግን አልሰሙም፡፡
ከጣና ምጽርሐ ደሴት ተነሥተው የደንቢያንና የበጌምድርን ሰው በየቤቱ እያስገቡ እሳት ባነደዱት ጊዜ፤ የበጌምድር አልቃሽ
እግዜርና ንጉሥ ተጣልተው ቁመው
ቅዱስ ሚካኤልን ዳኛ አስቀምጠው
እግዜር በግራ ነው ንጉሡ በቀኝ
በል ፍጅና ስጠኝ ሲሉ ሰማሁኝ፤ ብላ አለቀሰች ፡፡ ንጉሥ ግን አልሰሙም፡፡
የጎጃምም አልቃሽ ሜጫን በዘረፉት ጊዜ
ልብሴንም ገፈፈው ለበሰው እርዘኛ
በሬዬንም ነዳው አረደው ነፍጠኛ
እህሌንም ዘረፈው በላው ቀለበኛ
ንጉሥ የቀረዎ ጥቂት አማርኛ
ምነው ሆድ አይዘርፉ አርፌ እንድተኛ፡፡ አለች አሉ፡፡ ንጉሥ ግን አልሰሙም፡፡
ይህ ሁሉ ብሶት በሕዝቡ ውስጥ ታምቆ ይኖር ነበር፡፡ ብሶቱም እንደ ሙዳየ ምጽዋት በየቀኑ እየተጠራቀመ፣ እንደ ፍግ እሳት ውስጡን እየፋመ፣ እያብተከተከው ኖሯል፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲህ እንደዛሬ ሰላማዊ ሰልፍ፣ ጋዜጣ፣ ሬዲዮ፣ ፌስ ቡክና ሚዲያ ከመምጣቱ በፊት የብሶቱ ማውጫ፣ የሐሳቡም መግለጫ የልቅሶ ላይ ሙሾ ነበር፡፡ ቴዎድሮስ ይባስ ብለው የከለከሉት እርሱን ነው፡፡ ማንም ልቅሶ እንዳይቆም፣ ማንም ሙሾ እንዳያወርድ አወጁ፡፡ ‹የሚያስቆጣ ነገር ነግሮ አትቆጣ ይለኛል› እንደሚባለው፡፡
ሰውን ከብሶቱ በላይ ሁለት ነገር ይጎዳዋል፡፡ ብሶት ሰሚና ብሶት ማሰማት ሲከለከል፡፡ – – -» እነ ቴዴ አፍሮ እና ሌሎች ስመ ጥር አርቲስቶች የዘመሩላቸውን ጀግና ዳንኤል መይሳውን ለዚህ ትውልድ በዚህ መልክ በማስተዋወቅ በመጀመሪያ አማርኛው ተናጋሪ ክፍል እንዲለያይ አልፎም የአማራው ታሪክ የሚያሳድፍ ሆዱ አምላኩ የሆነ ግለሰብ ነው። ለዚህም ነው ዳንኤል ከዚህ ግለሰብ ጋር በአንድ ተርታ የተቀመጠው። በአንጻሩ የህዝብ ልጅ የሆነው ወንድማችን ሀብታሙ አያሌው አለምነው መኮንን ላደረገው የድፍረት ንግግር በመቃወም በባህር ዳር ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ አካሂዶ ነበር። ዳንኤል አሁን ወደ ሜልበርን ይህን ሁሉ ነውር ፈጽሞ ወደ አውስትራልያ ሊሂድ ነው፤ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን እንዴት ይሆን የሚቀበሉት? https://youtu.be/UE-fjSyj2QQ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *