እኒህ የ እድሜ ባለፀጋ ከ ሀምሳ አመት በላይ የ ትልቁን የትምህርት ማዕረግ የያዙ አንጋፋ ሙሁር የሰሞኑ መነጋገሪያ አጀንዳ ሁነዋል

ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም
💚💛❤️🔥🔥💚💛❤️
እኒህ የ እድሜ ባለፀጋ ከ ሀምሳ አመት በላይ የ ትልቁን የትምህርት ማዕረግ የያዙ አንጋፋ ሙሁር የሰሞኑ መነጋገሪያ አጀንዳ ሁነዋል ! ይህ ነገር ከዋነኛው የትግል አጀንዳ ያዘናጋል በሚል ስሸሸው ብኖርም ነገሩ እየጦዘ ከዋናው አጀንዳችን እያስወጣን ስለሆነ አንድ ነገር ማለት አለብኝ ብየ አሰብኩ::

1. ከ 60ወች ባለስልጣን ግድያ ጋር
🔥🔥🔥
ይህ ነገር አዲስ አይደለም ገነት የምትባል ፀሀፊ ኮ/ል መንግስቱን ዝምባቢዊ ሂዳ አናግራ በፃፈችው መፅሀፍ መንጌ ለ እሳቸው ያለውን ጥላቻ እና በ ዛ ወቅት አጣሪ ኮሚሽን ሁነው ተመድበው ሲሰሩ ነገሩን እንዲአፈጥኑት ስንወተውታቸው መሳሪያው በ እጃችሁ ነው ለምን ትጨቀጭቁናላችሁ አሉን ብሏል:: እውን ይህን ብለዋል አላሉም የሚጣራ ሁኖ ቢሉስ በዚህ ቃል ምክኒያት 60ወቹን አዛውንት ገድለዋል ከሆነ መከራከሪያው ይህ ተራ እና የማይረባ ነገር ነው:: የደርግ ድርጊት ተቀባይነት የሌለው ዘግናኝ ድርጊት ነው:: አዛውንቶቹን ደርግ የገደለበት ሂደትም ከዚህ ጋ እንደማይገናኝ በወቅቱ የነበሩ ሰወች በቃልም በፅሁፍም አስረድተዋል::

2. አማራ የለም ብለዋል
🔥🔥🔥🔥
ይህን ነገር ከ 27 አመት በፊት ከመለስ ጋር በቴሌቪዥን በተደረግ ውይይት ይሁን ክርክር ተናግረዋል :: ይህን የተናገሩት የወቅቱን ስነልቦና በመገናዘብ እንጂ ከጥናት እና ምርምር የተገኘ ባለመሆኑ እንደተሳሳቱ ሀቅ ነው! አማራ የሚባል ነገድ ከ ሽህ አመታት በፊት እንደነበረ በጥናት የተረጋገጠ በመሆኑ በዚህ ጉዳይ ብዙ ማለት አልሻም! አማራ አለ ነበረ: ወደፊትም ይኖራል!

3. በላይ ዘለቀ ኦሮሞ ነው
🔥🔥🔥
ይህን የ ሀሳብ ሙግት የት እንዳገኙት አላውቅም ሀቁ ግን በላይ ዘለቀ በ ግማሽ ወገኑጎጃሜ በግማሹ ወሎየ ነው! ተወልዶ ያደገው እና መርቶ ጣልያንን ያርበደበደው ጎጃም ውስጥ ነው ስለዚህ በላይ ዘለቀ ጎጃሜ አማራ ነው::

4. ዘራቸው ትግሬ ነው
🔥🔥🔥
ይህ ደግሞ ፍፁም ሀሰት እና ከባለቤቱ ያወቀ ቡዳ ነው ያሰኛል ! እሳቸው ራሳቸው እንደተናገሩት አባት እና እናታቸው ከወሎ መጥተው አዲስ አበባ ውስጥ ተወልደዋል :: ዘራቸው ከወሎ ይመዘዛል ስለዚህ በጥላቻ ተነሳስተን የሌለ ነገር ማውራት ስህተት ነው!

መደምደሚያ
🔥🔥🔥🔥
እኔ የ ፕ/ር መስፍን አምላኪም ጭፍን ደጋፊም አይደለሁም:: የምደግፈውን የትግል መስመርም አይደግፉም በ ኢትዮጵያዊነታቸው እና በ እድሜ ልክ የሰባዊ መብት ተሟጋችነታቸው አደንቃቸዋለሁ! እኒህ የ እድሜ ባለፀጋ እና አንጋፋ ሙሁር የፃፉአቸውን መፅሀፍ በማንበብ መማር ስንችል እሳቸውን እንደ አንድ የገዢው ፓርቲ ባለስልጣን መንቀፍ እና ሌት ተቀን ማውገዝ ተገቢም ገንቢም አይደለም! ጎበዝ ስንት የሚሰራ ስራ እያለ በ እሳቸው ዙርያ እየተነታረክን የትግል ጊዜን ማጥፋት ዝም ብሎ ረካሽ ታዋቂነት እና የውሸት የ አማራ ተቆርቋሪነት የመነጨ ነው እንጂ ፕ/ር መስፍን በ አማራነቱ አሳር መከራውን ለሚያየው አማራ ጠላትም ፀርም አይደሉም ከዳዊት ሰለሞን!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *