ያንተ ትምህርት የአፈር ትምህርት” እስቄል ጋቢሳ “.

#Ethiopia”ያንተ ትምህርት የአፈር ትምህርት”
እናቴ
እናቴ አንድን ሠው ተምሮአል ከኔ የተሻለ ያስባል ብላ አክብራ ቦታ ሰጥታው እያለ ሠውየው ከግምቱአ ወርዶ ስታገኘው ” ያንተ ትምህርት ያፈር ትምህርት ትላለች” አሁንም ታድያ እኚህ በዕውቀታቸው የበቁ ናቸው የሚባሉ ፕሮፌሰርም በሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን ያውም በምዕራባውያን አገር ላይ
እየኖሩ : በስደት ያስጠለለቻቸው አገር እዛሬ ላይ ለመድረስ ያለፈችበትን ውጣ ውረድና
የፈጀባትን ግዜ ጠንቅቀው እያወቁ : ዕትብታቸው ለተቀበረባት አገርና ኢትዮጵያዊነትን ቢፀየፉትም: እወክለዋለሁ ለሚሉት የኦሮሞ ብሔረሰብ ( ውክልናው አልተረጋገጠም ) እስከዛሬ እየሰበኩት ያለው በሬ ወለደ ዘባተሎ የጥላቻ ታሪክ ሳያንሳቸው
ዛሬ ደሞ በሌላ መልክ ተነስተው ስንት መረጃ ላላቸው ነጮች ፍፁም ከዕውነት የራቀ ሌላ የታሪክ ጥላሸት ይዘው በዚህ በፈረደበት አማራ ላይ እንደገና ተነስተዋል :: ምክንያቱም ላለፉት 26 ዓመት ሞቶ አላልቅ አላቸዋ::
ፕሮፌሰር የታሪክ መምህር ናቸው በዚያ ይተዳደራሉ ሆኖም ግን ከሙያቸው ስነ ምግባር (Ethics ) ውጭ ባገኙት መድረክ ላይ በውስጣቸው ተሸክመው የኖሩትን የተሳሳተና የበሰበሰ የጥላቻ መርዝ መሰረት አድርገው ቢያቀረሹ ዛሬ ያደመጡአቸው ነገ ዕውነቱን ሲረዱት የሚያፍሩት እራሳቸው ናቸው::
በዚህ የመረጃ ዘመን ማንም ማንንም አይሸውድም::
ፕሮፌሰር ከእንግዲህ በቀራቸው ዕድሜ
ሊቀርቡ የሚችሉት ወደ መቃብር እንጂ ወደ ሌላ ትርፍ ህይወት አይመስለኝም : ታድያ በዚህ በቀራቸው ግዜ ቢያንስ ስለልጆቻቸው ሲሉ ዕውነትን ለአንዲት ጀንበር እንኩአ ለምን ተናግረው እንደማያልፉ አላውቅም::
የፕሮፌሰር ሕዝቅኤል ትምህርት ዕውነትም እናቴ እንዳለችው ” የአፈር ትምህርት ” ነው::
ጎሣዬ ተዘራ.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *