ኢህአዴግ ሆኗል ተብሎ ተወርቶብኝ ነበር ፤ በነገራችን ለይ ኢህአዴግ መሆን ሃጢያት አይደለም ስውሩ ወያኔ ልደቱ

አቶ ልደቱ ትላንት እና ዛሬ
“”””””””””””””””””””””””””””””””””””””
ሰዎች ስለ ግል ህይወታቸው ያሻቸውን ሲናገሩ ጉዳዩ የእነሱ ብቻ ይሆናል። በአገር ጉዳይ መናገር ሲጀመሩ ግን ጉዳዩ የአገር ጉዳይ ነው ፤ አገር ደግሞ የጋራ ነው ፤ ስለሆነም ደግፈንም ይሁን ተቃውመን በተባለው ጉዳይ ለይ መናገር እንችላለን ።
1/ ከሰሞኑ JTV ለይ እንግዳ ሆነው የቀረቡት አቶ ልደቱ እንዲ አሉ ” ኢህአዴግ ሆኗል ተብሎ ተወርቶብኝ ነበር ፤ በነገራችን ለይ ኢህአዴግ መሆን ሃጢያት አይደለም ። ኢህአዴግ እኮ ከ5 እና ከ6 ሚሊዬን አባላት ያሉት ድርጅት ነው ።” አቶ ልደቱን በርግጥ ኢህአዴግ ከላይ ያሉትን ያህል አባላት አሉት ? ብለን መሞገቱን እንተወውና ከአመታት በፊት VOA ለይ ሲጠየቁ እንዲህ ማለታቸውን እናስታውሳቸው “ኢህአዴግ እኮ በህዝብ አንቅሮ አክ ተብሎ የተተፋ ድርጅት ነው!! እኔ እንዴት የዚህ ድርጅ አባል እሆናለሁ? ”
2/ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የአስችኳይ ጊዜ አዋጅ እስከማሳወጅ የደረሰውን የህዝብ የለውጥ እንቅስቃሴ ፥ ሰውየው ሲገልፁት” ኢህአዴግ 100% አሸነፍኩ በማለቱና ህዝቡ ድምፁን የሚያሰማለት የፓርላማ ተወካይ ስሌለው ህዝቡ ድምፁን በአመፅና ድንጋይ በመወርወር መግለፅ ጀመረ ፤ ከዚህ በፊት እኔን ጨምሮ አንድም ሁለትም ድምፁን የሚያሰሙለት ሰዎች ፓርላማ ውስጥ በመኖራቸው ይህ አመፅ አልነበረም ። ” ብለውን አረፉና ዛሬም እውነተኛ ማንነታቸው አስመሰከሩ ።
3/ አብዛኛው ህዝብ እርስዎን የሚወድ ነው የሚጠላ ? ተብለው ለተጠየቁት ሲመለሸሱ አብዛኛው ሰው በአሉባልታ የተነሳ እሳቸውን የሚጠላ እንደሆነ ገልፀው ” በተለይ ሶሻል ሚዲያ ለይ እኔን የሚወድ ሰው ያለ አይመስልም ” ሲሉ ስለራሳቸው ምስክርነት ሰጠው ለእኛ ህዝብ እንደማይሰሳትና ፥ እርሳቸውንም ህዝብ ተገቢው ቦታቸው ለይ እዳሰቀመጣቸው በንግግራቸው በእጅ አዙር አረጋግጠዋል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *