ትልቁ ዋርካ ወደቀ

ትልቁ ዋርካ ወደቀ

🔥🔥🔥🔥🔥🔥
ሲያልቅ አያምር ይሉሀል ይህ ነው! አባቴ መርጌታ ሰለሞን ቀፀላ እግዚአብሄር ሲጣላ ድላ አይቆርጥም ይሉ ነበር ነብሳቸውን በገነት ያኑርልኝ! የ ህውሀት ቀንደኛው ሰው ባልጠበቅነው መንገድ መታሰር ከፍተኛ የሆነ የ ኢኮኖሚም ቀውስ እና መመሰቃቀል ያስከትላል! ይህ ደግሞ እየተቀጣጠለ ካለው ወያኔ ላይ ከተለኮሰው ሰደድ እሳት ላይ ቤንዝል እንደማርከፍከፍ ይቆጠራል!

ይህ ሁኔታ የ 66ን አብዮት እየመሰለኝ ነው! ነገሮች ከቁጥጥር ውጭ እየወጡ ይመስላል! ለ ነገሩ ህውሀት እኮ በደዌ መጠቃት የጀመረችው መለስ ከሞተ በሗላ ነው! በ 1980ወች መጀመሪያ ገደማ አላሙዲን እና ህውሀት አብረው ብቅ አሉ! አብረውም ሊወድቁ ነው መሰል!! ታስታውሱ ከሆነ ትልቁን የሜድሮክ ወርቅ ኩባንያ ህውሀት ለ አላሙዲ በ 75 ሚሊየን ብር ብቻ ነው የሸጠለት! የህዝብን ሀብት ላለፉት ሀያ ስድስት አመታት ግጦ አልፎ አልፎ ደግሞ ጥቃቅን ፍርፋሪ ለ አርቲስቶች ይወረውራል!

የ ወያኔው ቴሌቪዢን ስለ ሌሎች መታሰር ሲዘግብ ስለ አላሙዲን መታሰር ምንም አላለም! በዚህ ዜና ሀዘን የሚቀመጡ እልፍ ናቸው! አላሙዲን ተቀድመው እንጂ እስሩ ሲከናወን ኢትዮጵያ ቢኖሩ ወያኔ አሳልፋ አትሰጣቸውም ነበር! እንግዲህ የሚሆነውን እንከታተል ! ወያኔ እንደቆማጣ ገላ ቀስ በቀስ ፍርክስክስ እያለች መሆኑን ልብ ያለው ልብ ይበል!

አላሙዲን በስር በስዕሉ ያሉትን ኩባንያወች ሁሉ ባለ ሀብት ነው! የ ጣና ገዳሞች በደም በተጨማለቀ ገንዘብ የ ሀይቁ ፈውስ ይቅርብን ያሉ ይመስላል ለጣና ማጨጃ ማሽን ሳይገዙ ሸቤ ገቡ
ከዳዊት ሰለሞን

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *