29 የዐማራ ተወላጅ የአየር ኃይል አብራሪዎች ሥራ ለቀቁ፦

29 የዐማራ ተወላጅ የአየር ኃይል አብራሪዎች ሥራ ለቀቁ፦

ከባለፈው ዓመት ጀምሮ ሲታመስ የነበረው የደብረ ዘይት፣ የድሬ ደዋና የባሕር ዳር አየር ኃይል 29 አብራሪዎቹን በግዴታ አሰናብቷል፡፡ ዝቅተኛ ልምድና የትምህርት ደረጃ ባለቸው የትግራይ ተወላጆች መታዘዝ የለብንም፤ የበረራ ልምምድ ከትግራይ ተወላህ ውጭ ለሆኑ በቂ ርቀት አይሰጥም፤ እኩል ዜጎች ከሆን እኩል የተጠያቂነትና የባለቤት ስሜት ሊኖረን ሲገባ የሚፈለገው ጎሳ አባለት ባለመሆናችን ብቻ ለአገር የማናስብና የማንታመን መሆናችን የሥራ ሞራላችን አጥፍቶታል ያሉ ከ40 በላይ አብራሪዎች የሥራ መልቀቂያ አስገብተው ነበር፡፡ ሆኖም የአገልግሎት ዘመናችሁ ገና አልሞላም ተብለው ብዙ ቆይተው ነበር፡፡

ባሳለፍነው ሳምንት ግን 29 የዐማራ ተወላጅ ለሆኑ የአየር ኃይል አብራሪዎች 35000 ብር የአገልግሎት የሚል ሳንቲም እየተሰጣቸው ከደብረ ዘይት፣ ከድረ ደዋና ባሕር ዳር አየር ኃይል ምድቦች ከሥራ ተሰናብተዋል፡፡ ሌሎች ከ20 የሚበልጡ አብራሪዎችም የሥራ መልቀቂያ በመጠባበቅ ላይ እንደሆኑ ከደብረ ዘይት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

MulukenTesfaw

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *