የደንበጫ ወረዳ መሣሪያ መካዝን ተሰብሮ ተዘረፈ

ሰበር ዜና፤ የደንበጫ ወረዳ መሣሪያ መካዝን ተሰብሮ ተዘረፈ!

በምዕራብ ጎጃም ዞን የደንበጫ ወረዳ የሚሊሻ ጽ/ቤት የመሣሪያ መካዝን ትናንት ሌሊት ተሰብሮ 22 ክላሽንኮፍ መሣሪያዎች ተዘርፈዋል፡፡ የወረዳው አመራሮች በዚህ ምክንያት ከሁለት ተባድነው እየተገማገሙ ነው፡፡ በማንና እንዴት እንደተዘረፈ በውል ያልታወቀው ይኼው መካዝን ከሚሊሻ ጽ/ቤትና ከፖሊስ አባላት መካከል የተወሰኑ እንደታሠሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

በሌላ በኩል በእንጅባራ ከተማ የፌደራል ፖሊስ አባላት ስብሰባ ላይ መሆናቸውን ተከትሎ የመከላከያ ሠራዊት ከተማዋን እያሸበራት ነው ብለውናል ምንጮቻችን፡፡ የፌደራል ፖሊስ በእንጅባራ ከተማ ስብሰባ ማድረጉ ያልተለመደ ከመሆኑም ባሻገር በመከላከያ ሠራዊት ጥበቃ መደረጉ ያልተለመደ ነገር ነው እንደ መረጃዎቻችን፡፡

MulukenTesfaw

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *