አቶ ለማ መገርሳ ፈተናህ አሁን ነው

ይድረስ ለአቶ ለማ መገርሳ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት።

አቶ ለማ መገርሳ ፈተናህ አሁን ነው ።

ከሰሞኑ የምትናገራቸው የአንድነት ኢትዮጵያን እንገንባ ጥላቻን በመተው ፍቅርን ለአዲሱ ትውልድ እናስረክብ ስትል ሁላችንም ይህ ሰው ለወደፊት ለኢትዮጵያ ይጠቅማል ብለን አንጨብጭበናል ።

አሁን ግን ያን የሚያምርና አስደናቂ ንግግሮችህን ፈተና ላይ እየጣለህ ነው ።
የሰሞኑ የአማራ እልቂት በአንዳንድ ፅሁፎች ስመለከት ይህ የህውሓት ሴራ ነው ኦሮሞና አማራ አንድ እንዳይሆን የሚሉ አሉ ።

እኔ ግን ለአቶ ለማ መገርሳ የምለው ከእነሱ የተለዬ ነው ።
ህውሓት አደረገው ብዬ የምጠረጥረው በትግራይ ክልል ሲሆን ብቻ ነው ።
አሁን ግን ወደድክም ጠላህም ይህ አማራን ያነጣጠረ ግድያ የተካሄደው በአንተ ክልል ውስጥ ነው ለዚህ ተጠያቂው ደግሞ አንተ ነህ ።

ከሰሞኑ በአንተ ክልል ተደብቀው ሳይሆን በአደባባይ ገጀራ ይዘው በመውጣት ኦሮሞ የእኛ ናት እናንተ መጤዎች ናችሁ የምኒሊክ ሰፋሪ ናችሁ እያሉ ነው ሱቃቸውን ቤታቸውን በማቃጠል እንደ አይሲስ ያረዷቸው
አሁን አማራዎች በየጫካው ተደብቀው ነው ያሉት ።

አቶ ለማ መገርሳ የአማራ ህዝብ ከአንተ የሚጠብቀው 4 ነገር አለ ።

1 — አሁን በአስቸኳይ አማራዎች ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ ከአሁን በኋላ እንደዚህ አይነት ነገር እንዳይፈጠር የማድረግ አላፊነቱ አለብህ ።

2 — ንብረታቸው ለወደመ የኦሮሞ አስተዳደር ካሳውን በመክፈል እንደገና እንዲቋቋሙ አድርግ ።

3 — በአጠቃላይ በግድያውና ንብረት በማውደም የተሳተፉትን በአስቸኳይ ለፍርድ እንዲቀርቡ አድርግ ።

4 — ከዚህ እልቂት በእስተጀርባ ማን እንዳለ ለምን ይህን እንዳደረጉት ለኢትዮጵያ ህዝብ አሳውቅ ።

በመጨረሻም ባለፈው ኢትዮጵን በአንድ ላይ እንገንባ ብለህ እንዳልከው ።
ኢትዮጵያ ያሉ ህዝቦች ሁሉ ከፈለጉት ክልል ሂደው የመኖር የመስራት መብት አላቸው ለዚህም ነው ኢትዮጵያ ለሁሉም የተባለችው ።
ከኦሮሞ ክልል የሚኖሩ አማራዎች መጤዎች ወይም የምኒሊክ ሰፋሪዎች ተብለው በገጀራ ከተመቱ ግን አንተ ያልካት ኢትዮጵያ የለችም ማለት ነው ።
አቶ ለማ መገርሳ ፈተናህ አሁን ነው ። ከ ጌቱ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *