በኮምቦልቻ ከተማ አርሷደሮች እየታሠሩ ነው፡፡ << መሬታችንን ከተነጠቅን መሞት ለኛ እረፍት ነው፡፡ >> አርሷደሩ፡፡

በኮምቦልቻ ከተማ አርሷደሮች እየታሠሩ ነው፡፡
<< መሬታችንን ከተነጠቅን መሞት ለኛ እረፍት ነው፡፡ >> አርሷደሩ፡፡
.
በደቡብ ወሎ ዞን ፤ የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር በኢንቨስትመንት ሰበብ አርሷደሩን ማፈናቀል የቆየና ስር የሠደደ የመልካም አስተዳደር ችግር መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡ አርሷደሮች ያለበቂ ካሳ ፣ ቦታቸውን በህገወጥ መንገድ ይቀማሉ ፤ ቅሬታ እንዲያነሱ አይፈቀድም ፤ ቅሬታ ያስነሱ አርሶደሮች ደግሞ በገዛ መሬታቸው ያለአግባብ ይታሰራሉ፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ በዚሁ ከተማ አስተዳደር ቀበሌ 09 ትዩአምባ የሚገኙ አርሷደሮች ፤ << መሬታችንን ለአንድ ካሬ በ6 ብር መንጠቅ አግባብ አይደለም፡፡ ከዚህ ቀደም በ1.46 ብር የተነጠቅነው ይበቃል ፤ ስለዚህ ለባለሀብት መሬት ለመሸጥ ሲባል የሚናጋው የዜጎች ህይወት አይታይም ወይ ? ... >> የመሳሰሉትን ጥያቄ ያነሱ ከ20 በላይ አርሷደሮች መታሠራቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ በኮምቦልቻ ከተማ ኢንቨስትመንትን ከለላ በማድረግ የሚፈፀመው የመሬት ንጥቂያ በሺዎች የሚቆጠሩ አርሷደሮችን ኑሮ አስከፊ ደረጃ ላይ አድርሶታል፡፡ በአርሷደሩ የእርሻ ቦታ ላይ ያላቆመው የመሬት ቅርምት ፤ በመቶ ሚሊየኖች ገንዘብ ፈሶባቸው በመሠራት ላይ ያሉ ፕሮጀክቶችን ቦታ ሳይጠናቀቁ ፤ የዲዛይን ማሻሻያ ሳይደረግባቸው ቆርሶ እስከመሸጥ የደረሰ ህገወጥነት ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡ በከተማዋ መሬት ዋነኛ የሙስናና የመልካም አስተዳደር ችግር ሆኗል፡፡ ከተማዋን የቆረቆሩ ነዋሪዎች ሳይቀሩ በገዛ መሬታቸውና ቤታቸው ላይ ህልውና በማጣት ፤ << ቤቴ ዛሬ ተቀማ ፤ ዛሬ ተወሰደ ፤ መሬቴን ቀሙኝ አልቀሙኝ >> በማለት በስጋት በመኖር ላይ ሲሆኑ የመንግስት ካድሬዎች ቦታቸውን ከመቀማቱ በፊት ፤ ያለፍላጎታቸው ቤት ንብረታቸውን ለመሸጥ እየተገደዱ ይገኛሉ፡፡ በዚህና በኮምቦልቻ ከተማ የመልካም አስተዳደር ችግር ዙሪያ ፤ ልሳነ_አማራ ነዋሪዎችን በማነጋገር ተከታታይ ፅሁፍ ይዛ ትቀርባለች፡፡ ይጠብቁን!!!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *