በኤሊባቡር ከ20 በላይ ዐማሮች በአንድ ቀን ብቻ በገጀራ ተጨፍጭፈው ተገድለዋል፤

እጅግ በጣም አስደንጋጭና የጭካኔ ዜና ከሙሉቀን ተስፋው :-

” በኤሊባቡር ከ20 በላይ ዐማሮች በአንድ ቀን ብቻ በገጀራ ተጨፍጭፈው ተገድለዋል፤

በኤሉ አባ ቦራ (ኤሊባቡር) ዞን ደጋና ጮራ ወረዳዎች የዐማራ ተወላጆች ተለይተው እየተጠቁ እንደሆኑ የተጎጅ ቤተሰቦች ትናንት ጥቅምት 11 ቀን 2010 ዓ.ም. በስልክ አረጋግጠዋል፡፡ መንግሥትን በመቃወም የተጀመረው የተቃውሞ ሰልፍ ዐማሮችን በጅምላ መግደልና ቤትና ንብረታቸውን ወደ ማውደም መዞሩን የሚግልጹት ተጎጂዎች ትናንት ብቻ በአንድ ቀን ከ10 በላይ ሰዎች በገጀራ ተጨፍጭፈው ተገድለዋል፡፡
የዐማራ ተወላጆች ቤትና ንብረት እየወደ እንደሆነ የሚናገሩት በተለይ በደጋ ወረዳ ጎሮ፣ ሰፌና ደፎ ቀበሌዎች የዐማራ ቤትና ንብረት ሙሉ በሙሉ ወድሟል፤ በዐሥር ሺህዎች የሚቆጠሩ ዐማሮችም በጫካ ተዘርተው እንደሚገኙ ገልጸውልናል፡፡ የኦሮሚያ ፖሊስ ዩኒፎርም የለበሱ ሰዎች የግድያው ዋና ተሰላፊ እንደነበሩም አክለው ገልጸዋል፡፡
ለጊዜው በጎሮ ቀበሌ የተገደሉ 6 ያክል ሰዎች ስም ዝርዝር የደረሰን ሲሆን የተቆራረጡ የዐማራ አስከሬኖች ሁሉ በጮራ ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ ተከማችቶ እንደሚገኝም ተገልጧል፡፡ ትናንት ከተገደሉ ሰዎች መካከል
1. አቶ ክንዱ
2. አቶ ምስጋናው የዚህ ግለሰብ ገዳይ የክልሉ ልዩ ኃይል ፖሊስ አባል ነው፤
3. አቶ ሙላት
4. አቶ ባቡ
5. አቶ ይማም
6. ሼህ ሁሴን ናቸው፡፡
በኤሌባቡር ጫካዎች ተዝርተው የሚገኙ ዐማሮች የድረሱልን ጥሪም አስተላልፈዋል፡፡”

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *