የትግራይ መገንጠል አጀንዳ ላይ ውይይት ማድረጉንና ሕዝቡን ስለ ትግራይ መገንጠል እያወያየ መሆኑ ተገለጸ።


Hiber Radio: የሕወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ ሰሞኑን ትግራይን
ለመገንጠል መምከሩ ተገለጸ፣ በሕዝባዊ ተቃዎሞዎች ላይ
ሕወሓት የላካቸው የደህነት አባላት ጥፋትና ሕዝብ ከሕዝብ
የማጋጨት ስራ እየሰሩ ነው
(ህብር ሬዲዮ -ላስ ቬጋስ) ሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ
(ሕወሓት) በአገሪቱ እየተስፋፋ የመጣው ሕዝባዊ ተቃውሞ
ማየልን ተከትሎ በትግራይ መቀሌ ላይ ሰሞኑን የማዕካላዊ
ኮሜቴ በስብሰባዎ ዛሬ ድረስ በድርጅቱ ፕሮግራም የሚጘነውን
የትግራይ መገንጠል አጀንዳ ላይ ውይይት ማድረጉንና ሕዝቡን
ስለ ትግራይ መገንጠል እያወያየ መሆኑ ተገለጸ።
የአረና የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አምዶም ገ/ስላሴ እንደገለጸው
ሰሞኑን የሕወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አጀንዳ አድርጎ
የተወያየበትን የትግራይ መገንጠል ጉዳይ ሕዝቡን ትግራይ
ብትገነጠል ምን ይመስላችሁዋል ? እያሉ ወረዳና ቀበሌ ድረስ
ባለው መዋቅር ወርዶ እየተጠየቀ መሆኑን ይፋ አድርጓል።
ሕወሓት ከ42 ዓመት በፊት ሲመሰረት በ6 ወር ውስጥ
የትግራይ ትግሪኝ ሪፐብሊክ እመሰርታለሁ ማለቱን አስታውሶ ዛሬ
ከ42 ዓመት በሁዋላ አጀንዳው ለምን ተነሳ ሲል ይጠይቃል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የሕወሓት አገዛዝ አገሪቱ ላይ ያሰፈነው
በአንድ ብሄር የበላይነት የሚመራ የገዢ ቡድን በጉልበት
መግዛት የማይችልበት ደረጃ ሲደረርስ የአገቱን አንጡራ ሀብት
ሲዘርፍ ከኖረው የቀረውን አሟጦ፣ህዝብን ከሕዝብ ለ26 ዓመት
ሲያስፋፋ በኖረው የዘር ፖለቲካ አጋጭቶ፣ አገሪቱን በታትኖ
ትግራይን ለመገንጠል ወደ መጨረሻው ደረጃ እየተቃረበ
መሆኑን ጃዋር መሐመድን ጨምሮ የተለያዩ አክቲቪስቶችና
የተቃዋሚ መሪዎች ለህብር በቅርቡ በሰጡት ቃለ መጠይቅ
በጥያቄ ቀርቦላቸው መመለሳቸው አይዘነጋም።
በቅርቡ በሶማሌና በኦሮሚያ መካከል ዘርን መሰረት አድርጎ
የሶማሌ ልዩ ሀይልን ተጠቅሞ በንጹሃን ላይ የከፈተው ጦርነት
ከ200 መቶ በላኢ ንጹሃን ሲገዱ ከ140 ሺህ በላይ የኦሮሞ
ብሄር ተወላጆችበዘራቸው ምክንያት ሲፈናቁ የህወሓትን
የተልዕኮ የዘር ግጭት ለማስነሳት የሚሰሩት የሶማሌው ክልል
ፕሬስዳንት አብዲ ኢሌ ቃል አቀባይ 350 ሶማሌዎች
መፈናቀላቸውን መጥቀሳቸው ይታወሳል።
ስልጣን ወይም ሞት ብሎ የተነሳው ሕወሓት ለ26 ዓመትት
አማራና ኦሮሞን ለማጋጨትና እርስ በእርስ በጥርጣሬ
እንዲተያዩ ለማድረግ የሰራው ሴራ ሁሉ እየከሸፈ መሔድ
ተቃውሞውን ተከትሎ በደህነት አባሎቹ አንዱ አንዱ ላይ ጥቃት
እንደወሰደ ለማድረግ እና የህዝብ እልቂት ለመጋበዝ የተለያዩ
እንቅስቃሴዎችን እያደረገ ይገኛል።
ጋዜጠኛ ሙሉቀን ተስፋው ከሰሜን ሸዋ ያገኘውን መረጃ ጠቅሶ
እንደዘገበው ትላንት ጥቅምት 9 ቀን 20110 ዓ. ም በሰሜን
ሸዋ ዴራ ላይ አማራና ኦሮሞውን ለማጋጨት የሕወሓት
ተላላኪዎች <<አማሮች ሊወሯችሁ መጡ>> ብለው
እስከመቀስቀስ ቢሄዱም ሁለቱም ወንድማማች ሕዝቦች
ከጥዋቱ ጀምሮ በመራህቤቴ እና በዴራ ለሕዝባዊ ተቃውሞ
አደባባይ የወጡ ሲሆን በአገዛዙ ታጣቂዎች በተተኮሰ ጥይት
ሶስት ንጹሃን ተገለው አራት ቆስለዋል።
የትላንቱን ተቃውሞ ተከትሎ በጥይት ከተመቱት 7 ሰዎች ሁለቱ
ወዲያው ሲሞቱ አንዱ መራህቤቴ ሆስፒታል ከደረሰ በሁዋላ
ሕይወቱ ማለፉን እና ቀሪዎቹ የቆሰሉት አራት ሰልፈኞች በሪፈራል
ወደ ደብረ ብርሃን ሆስፒታል መወሰዳቸው ታውቋል።
የአገዛዙ ኃይሎች ከቱቲ የመጡ አማሮች ኦሮሞዎችን ሊያጠፉ
ነው ብለው ቢሰብኩም ‹‹ሁላችንም አንድ ነን›› በሚል
ከመራህቤቴ፣ ብቸናና ዴራ የተሰባሰቡ ዐማሮችና ኦሮሞዎች
ዛሬም ከአገዛዙ ኃይሎች ጋር ሲጋፈጡ መዋላቸውን ከቦታው
ያገኘነውን መረጃ የጠቀሰው ይሄው ዘገባ አመልክቶ በአሁኑ
ወቅት የመራህቤቴ ከተማ ከፍተኛ ቁጥር ያለው በአጋዚ ወታደር
መከበቡም ተመልክቷል።
በተያያዘ ዜና ተስፋ የቆረጠውን በሕዝቡ ላይ ተጨማሪ ጥፋት
ለማምጣት የሚሰራው የትግራይ ነጻውጪው ግንባር-ሕወሓት
በኦሮሚያ ክልል ሰሞኑን የተነሳውን ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ወደ
አልተፈለገ አቅጣጫ ለመምራት በተቀነባበረ ሁኔታ የደህነት
አባላቱን ሰርገው እያስገቡ መሆኑን ትላንት በጫንጮና
ደብረጉራቻ ቄሮ መስለው መኪኖችን እና ቤቶችን ያቃጠሉት
የወያኔ ተላላኪ ወታደሮችና ደህንነቶች በኦሮሞ ቄሮ አባላት
ተጋልጠው ለኦሮሚያ ፖሊስ ተላልፈው መሰጠታቸውን ዘሐበሻ
አስቀድሞ መዘገቡ ይታወሳል።
ከአዲስ አበባ 45 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ጫንጮ
ከተማ እና ከአዲስ አበባ 156 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ
በምትገኘው ገብረጉራቻ ከተማ በኦሮሚያ ቄሮ (ወጣቶች) ስም
የሕዝብን ቤትና ንብረት ያቃጠሉት የሕወሓት ደህንነቶች እና
ወታደሮች መሆናቸው ተጋለጦ በሕዝቡ ግፊት በቁጥጥር ስር
ውለዋል።
የኦሮሞ ቄሬዎች ሰላማዊ ትግል እያካሄዱ ባሉበት በአሁኑ ወቅት
ወትሮም ሰላማዊ ትግሉን የንብረት ማውደም አስመስሎ
ማቅረብ የሚፈልገው ሕወሓት መራሹ መንግስት ወደ ጫንጮ
እና ደብረ ጉራቻ ከተማ ከደቡብ ክልል በተለይም የወላይታ
ተወላጅ ወታደሮችና የደህንነት አባላትን በመላክ ከአማራ ክልል
የሚመጡ መኪኖችን እና በነዚህ ሁለት ከተሞች የሚኖሩ
የአማራና የሌሎች ብሄር ተወላጅ ቤቶችና ንብረቶች እንዲቃጠል
አስደርጓል ያሉት የአካባቢው ምንጮች ቄሮ በመምሰል ድርጊቱን
የፈጸሙ የሕወሓት ተላላኪዎች በኦሮሚያ ፖሊስ ቁጥጥር ስር
መዋላቸው ታውቋል::
ከአካባቢውን እማኞች አንዱ ባለፉት ቀናት ከ አማራ ክልል
የሚመጡ ተሳፋሪዎች ላይ ምንም የደረሰ ጉዳት የለም።
እንደውም ከ አማራ ክልል የሚመጡ ተሳፋሪዎች ከ ኦሮሞ
ወገኖች ጋር ሆነው ከመኪናም እየወረዱ ‘down down
Woyan’: bye Bye Woyane’: ሲሉ እኔ ብዙ አይቻለሁ፣ ያንን
ሳይ አለቀስኩ፣እንዴት ደስ ይላል መሰላች ሁ። የሚገርመው
ደግሞ ከ አማራ ክልል የሚመጡ ተጓዦች የሚችሉትን ያህል
ሁሉም ባሶች ውስጥ ያሉ ተሳፋሪዎች የሚች ሉትን ያህል
በሶማሌ ግጭት ለተፈናቀሉት ገንዘብ በፌስታል እየሰበሰቡ
ያዋጡ በብዛት አይቻለሁ። ኦሮሞና አማራ ለዘላለም
ትብብራቸው ይቀጥላል ሲሉ መግለጻቸው የተዘገበ ሲሆን
የሕወሓት ሕዝብን ከሕዝብ የማጋጨት ሴራ በኦሮሞና በአማራ
የማያበቃ በመሆኑ ተቃውሞ በሚካሄድባቸው ቦታዎች ሁሉ
ሕዝቡ ሰርጎ ገብ የህወሓት ተልዕኮ ተሰጥቷቸው
የሚንቀሳቀሱትን ሊያጋልጥ እንደሚገባ ይሄ ድርጊት ያሳያል
የሚል አስተያየት እየተሰጠ ይገኛል።
የአካባቢው ምንጮች ለዘሐበሻ እንደጠቆሙት ሕወሃት በዚህ
ብቻ ሳያበቃ ከአዲስ አበባ ወደ ተለያየ የአማራ ክልል ከተሞች
የሚሄዱ የመንገደኞችና የዕቃ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ላይ
ራሱ አደጋ ጥሎ የሽብር ድርጊት ሊፈጽም ይችላል የሚል
ጥርጣሬ እያየለ የመታ ሲሆን ሕዝቡ እንዲያውቀው መረጃው
እንዲደርስ ተማጽኖ አቅርበዋል።
ሕወሓት በአሁኑ ወቅት ሁለት የጥፋት ስትራቴጂ በአገሪቱ ላይ
እየተከተለ ስልጣኑን ለማስጠበቅ እሞከረ ነው የሚሉ ሁለት
የጎሉ አስተያየቶች በአደባባይ መደመጥ ጀምረዋል። በአንድ
በኩል ራሱ በመላው አገሪቱ የህዝቡን ብሶት ተከትሎ ፍጹም
አለመረጋጋት እንዲፈጠር ሰሞኑን የደህነት አባላቱን አስርጎ
ሊፈጥር እንደፈለገው ሰፊ ጥፋት በማድረስ ሰላማዊ
ተቃውሞዎችን ወደ እርስ በእርስ መጠፋፋት በመቀየር ራሱ
ሰላም አስከባሪ መስሎ መውጣት ይህ ካልተሳካ አሁን ራሱ
በበላይነት የሚጨፍርበትን አደጋ ላይ የወደቀ ስርዓት ላይ
መፈንቅለ መንግስት ማካሄድና ፈተና የሆኑበትን የክልል
አስተዳደሮች ማፍረስና ካዛለቀው ስልጣኑን ይዞ መቀጠል ሲሆን
ሁለተኛው አማራጭ ይህ ካልሆነ ከ42 ኣመት በሁዋላ
ሲሰራበት የነበረውን አገሪቱን ዘርፎና አደህይቶ የተለየ ድጋፍ
ሲያደርግላት የቆየውን ትግራይ መገንጠልና ሌላውን እርስ
በእርስ ማጫረስ በመሆኑ ለውጥ ፈላጊ ሀይሎች በሁሉም
መስክ መተባበርና ወሳኝ የሆነ እርምጃ መውሰድ አለባቸው
የሚል ተደጋግሞ ጥሪ እየቀረበ ይገኛል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *