ትግራይ ብትገነጠል ምን እንዳይቀርብን !

የትግራይ መገንጠል ጥቅሙ ብዙ ነው

ሕወሓት የትግራይን ሕዝብ ስለመገንጠል ማወያየቱ መልካም ይመስለኛል፡፡ ትግራይ ከኢትዮጵያ ብትገነጠል ጥቅሙ ለሁሉም ነው፡፡ ዋነኛው ኢትዮጵያ ላይ ያንዣበበው የእርስ በእርስ ጦርነት ዋነኛ ተጠቂ ከመሆን ይተርፋሉ፤ ለቀሪው የኢትዮጵያ ክፍል ደግሞ ታላቅ እፎይታን ይሰጣል፡፡
ዛሬ ትግራይ ብትገነጠል ስፓኞች ካታሎኒያን እንደሚማጸኑት አብረን እንኑር ብሎ የሚማጸን አካል እንደማይኖር ግልጽ ነው፤ ከተቻለም የሕወሓቶች ትእቢት እስኪበርድ የተከዜን ወንዝ ተከትለን የማያገናኝ ታላቅ ግንብ በመገንባት እንተባበራለን፡፡ በአጪሩ ቆዩ አብረን እንኑር የሚል አካል ስለማይኖር ፍቺው ሰላማዊ ይሆናል ማለት ነው፡፡
እስካሁን ከሚቆጩኝ ነገሮች አንዱ ኤርትራን ላለማስገንጠል የጠፋውን የሰው ሕይወት ሳስብ ነው፤ አርትራን ላለማስገንጠል ያለቀው የኢትዮጵያ ወታደር በስህተት ነው ያለቀው፡፡ ኤርትራ ላይ በመቶ ሽዎች የሚቆጠር ጀግና እሳት ውስጥ ከመጨመር ለጁቡቲ ነጻነት አለመስጠት እጅግ የተሻለ ነበር፡፡ በዚያ ላይ የወሎ አሰብ የራሳችን ነበር፡፡ ደርግ በቀይ ሽብር ከጨረሰው ሕዝብ በላይ ትግራይንና ኤርትራን ላለማስገንጠል ያባከነው የአገር ገንዘብና የሰው ሕይወት የበለጠ ጥፋተኛ ያደርገዋል፡፡
በመጨረሻ ሕወሓቶች ትግራይን ለመገንጠል የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ብቸኛ የምደግፍላቸው ነገር እንደሆነ ላሳውቅ እወዳለሁ፡፡

ሙሉቀን ተስፋው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *