ጥብቅ ሰበር መረጃ!

ጥብቅ ሰበር መረጃ!
ጭንቅ ውስጥ የገባው ህወሃት ብአዴንን እያባበለ መሆኑ ታወቀ! ወልቃይትን ቢሆን እንመልሳለን እያሉ ነው!
ህዝባችን በምንም መደለያ እንዳይዘናጋ አደራ ተላልፏል!
ጥቅምት 8 2010

ብአዴንን ከኦህዴድ ለመነጠል በሚስጥር ስብሰባ ይዘዋል። መቀሌ ላይ ስብሰባ የሰነበተው ወያኔ በአንጃ በመከፋፈሉ መስማማት አልቻሉም። በአድዋ የበላይነት ላይ ያለው ቅሬታ አድጎ ተፎካካሪ አንጃ ፈጥሯል። ህዝባዊ ተቃውሞውንም በምን መልኩ እንፍታው በሚለው መስማማት አልቻሉም ተብሏል። የህወሃት ስምምነት ማጣትና በአንጃ መከፋፈል እየከፋ ከመምጣቱም በላይ ኦህዴድና ብአዴንን ማዘዝ ከማይችሉበት ደረጃ መድረሳቸውን የመረጃ ምንጫችን አክሎ ገልጿል። ህወሃት የምታሽከረክረው ኢህአዴግ ያለ አዛዥ እየተወዛወዘ ነው። ወጀብ በዝቶበታል። እየተንገዳገደ ነው። ህዝቡ ደግሞ ለለውጥ ቁርጠኛ ሆኗል።
AsnakewAbebe

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *