ባህርዳር የሚገኘው የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽ/ቤት በሰው ብዛትና በስልክ ጥሪዎች ተጨናንቋል!

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ)
*******************************
ባህርዳር የሚገኘው የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽ/ቤት በሰው ብዛትና በስልክ ጥሪዎች ተጨናንቋል!
********************************
ዛሬ ጥቅምት 08/2010 ከወትሮው ለየት ባለ መልኩ አባይ ማዶ የሚገኘው የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽ/ቤት የአለምነው መኮንን ቢሮ በሰዎች ብዛትና በስልክ ጥሪዎች እጅግ ተጨናንቆ ይገኛል ፡፡ ወደ አለምነው መኮንን ቢሮ ለመግባት ወረፋ የያዙ የድርጅቱ ከፍተኛ ፣ መካከለኛ እና ዝቅተኛ አመራሮች የሚገኙበት ሲሆን እንዲሁም ነባር የብአዴን ታጋዬችና የአካል ጉዳቶኞችም ወረፋ /ተሰልፈው/ ታይተዋል ፡፡ ምክንያቱም የድርጅቱ መስራችና ላለፉት 27 ዓመታት በመንግስት ከፍተኛ ስልጣን ላይ የሚገኘው በረከት ስምኦን መልቀቂያ መጠየቅ በምሽቱ ዜና ላይ መንግስት ይፋ ማውጣቱ ነው ፡ እነዚህ በድንጋጤ የተሞሉት የድርጅቱ አባሎች እንዴት መልቀቂያ ጠየቀ? ለምን በባህርዳር በነበረው ኮንፈረንስ ይሄን አላቀረበም? ምክንያቱ ለምን ግልፅ አይደረግም ? ድርጅታችን ከታህድሶ በኃላ አይደለም ለኛ አባሎቹ ለህዝብም ግልፅ እንሆናለን በአልንበት ወቅት አንድ ከፍተኛ የድርጅቱ ማዕከላዊ ኮሚቴና የመንግስት ባለስልጣን መልቀቂያ ሲጠይቅ እንዴት አይነገርም ለውይይትና ለመነጋገር አይቀርብም ? በማህበራዊ ድህረ ገፅ አይተን ስንጠይቅ ይህ የግንቦት 7 ወሬና የኢሳቶች ውሸት ነው ፡ የፀረ- ሰላሞች ምኞት ነው ወዘተ ትሉን አላቹሁ እንዴት በግልፅ አልተነገረም ? የሚሉ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ለአለምነው መኮንን ጥያቄ ያቀረቡ ሲሆን አለምነውም ሲመልስላቸው ” አንድ ሰው መልቀቂያ ጠየቀ ተብሎ ይሄን ያክል ውዥንብርና ሁከት ምን አመጣው ለወሬ ይሄን ያክል ከምንተራመስ ለስራ እደዚህ ብንሆን እንዴት ጥሩ ነበር ? በረከት መልቀቂያ ያቀረበው የመንግስት ስልጣኑን በተመለከተ በመሆኑ ይሄ እኛን አይመለከትም እስከአሁን ከድርጅቱ ለመልቀቅ ጥያቄ አላቀረበም ያኔ ወደ እኛ ጥያቄውን ሲያቀርብ መልስ እንሰጥበታለን ” የሚል ምላሽ ሲሰጣቸው ጠያቂዎች እጅጉን በመልሱ እደተበሳጬ በተለይ ነባር ታጋዬች የሚባሉትና የአካል ጉዳተኞች /በጦርነት አካላቸውን የተጎዱ/ እስከ መሳደብ ደርሰዋል በተለይም ይህ ድርጅት እስከ አሁን የቆመው ከበረሀ ታግለው በመጡ ሰዎች እንጅ ከትግሉ አጥቢያ በኃላ በገባቹሁት አይደለም ብለው እስከ መናገር የደረሱ ሲሆን ካቢኔዎች ደግም ከመስከረም 10-14 ቀን 2010 ዓ/ም ድረስ በባህርዳር በተደረገው የከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች ኮንፈረንስ ላይ በረከት አንተ (አለምነው) ላይ ከፍተኛ ትችት እና አስተያየት ስለሰጠህ ለጠየቅንህ ጥያቄ የንቀትና የጥላቻ ምላሽ ሰጠኸን” በማለት ተናግረዋል ፡ ይህ በንዲህ እንዳለ በዛሬው ቀን ወደ አለምነው መኮነን ቤሮ የሄዱት የድርጅቱ አባላት የሆኑ ብቻ ሳይሆኑ “ልማታዊ ባለሀብቶች” ተሰልፈው ታይተዋል ለአብነት ያህልም የሆም ላንድ ሙሌጌታ ፡ አበበ ይማም ፡ የግራንድ ሆቴል ባለቤት ነኝ የምትለው ወ/ሮ ትልቅ ሰው ገዳሙ ፡ በከተማው ባላሀብቶችን እና ባለስልጣናትን በማገናኘት የሚታወቀው የበምነት ሥጋና ሪስቶራንት ባለቤት በቀለ ይገኙበታል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *