ስደተኛው ሰላይ

ስደተኛው ሰላይ

ግርማይ በርሄ ነዋሪነቱ, Oslo, Norway
ሙያ: የህዋሃት ሰላይና ካድሬ
ከ10 አመት በፊት ግርማይ በርሄ Girmay Berhe ውሸቱን ህዋሃት በጋዜጠኝነቴ አሰቃየኝ ብሎ ወደ ኖርዌይ እንደ ስደተኛ የመጣ ጊዜ የህዋሃት አባልና ካድሬ ነበረ። ግርማይ በርሄ ኢትዮጵያ ነፃ ጋዜጠኛ ሆኜ ስ ሰራ የእስራትና የግርፋት ስቃይ ደርሶብኛል በማለት አርጋዊ በርሄ (የሪፖርተር ጋዜጣ ባለቤት) የፃፈለትን በማህተምና ፊርማ ያጌጠ የምስክር ወረቀት አሳይቷቸው የኖርዌይ መንግስትን በማሳመን መኖሪያ ፈቃድ አገኘ። በ2005 ያራ በመባል የሚታወቀው የኖርዌይ ኩባንያ መለስ ዜናዊን ምርጥ መሪ ብሎ ለመሸለም ዋና ከተማው ኦስሎ ጋብዞት ሲመጣ መለስን የሚቃወመውን ሰልፍ በመፈክር የሚመራው ግርማይ በርሄ ነበረ። ግርማይ በርሄ የዋህ የኖርዌይ ተቃዋሚዎችን እኔን ተከተሉኝ እያላቸው እውነትኛ ተቃዋሚ መስሏቸው ከኋላው እየተከተሉት ጉሮሯቸው እስኪዘጋ እሱ የሚለውን መፈክር እያስተጋቡ ሲጮሁ መለስ ሽልማቱን ወስዶ ይጠብቀው የነበረው አንድ ሺህ እንቁላል ሳይወረወርበት ተቃዋሚዎቹን ሰልፈኞች ፊት ለፊት ሳያገኝ በጓሮ በር አምልጦ እንዲወጣ በማስደረግ ግርማይ በርሄ መለስ ዜናዊን ከውርደት ያዳነ ሰው ነው። ከምርጫ በኋላ ኖርዌይ መኖሪያ ፈቃድ ሲያገኝ የተቃዋሚዎችን ስምና አድራሻ እየመዘገበ ለወያኔ ኤምባሲ አሳልፎ መስጠትን ስራዬ ብሎ ከያዘው ሰንብቷል።
ግርማይ በርሄ የሟቹ ኢያሱ በርሄ ወንድም ሲሆነ ሁለቱ ወንድማማቾች ግን እንደጠላት ነበር የሚተያዩት ምክንያቱ ደግሞ ግርማይ የተወለደው ከአቦይ በርሄ ገረድ ስለነበረ ዘራፊው ወንድሙ ኢያሱ በርሄ ምንም ሳያወርሰው የቀረው ብቸኛው የአቦይ በርሄ ልጅ ነው። በአሁኑ ወቅት ግርማይ በርሄ ስደተኞችን በመሰለልና በሰው ሰው ሃገር የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፎች እንዳይካሄዱ ለመበተን ሰላማዊ ሰልፎችን በመከልከል ወያኔ ላይ ምንም አይነት ህዝባዊ ተቃውሞና ስብሰባዎች እንዳይካሄዱ የማድረግ ዋና ሃላፊነት የተሰጠው የህዋሃት ካድሬ ነው። ነፃ ጋዜጠኛና የእውነት ስደተኛ መሆኑን ተቃዋሚዎችን አሳምኖ የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ማህበር ሳይቀር አምኖት በስደት ላይ ከሚገኙ ጋዜጠኞች ተርታ ውስጥ አስገብቶታል። የስደተኛ ጋዜጠኛ የሆነው ድህረ ገጽ ethioforum እንኳን ሳይቀር ተጭበርብሮ ግርማይ በርሄን በወያኔ ለስደት ከተዳረጉት ጋዜጠኞች አንዱ በማድረግ በተራ ቁጥር 63 ላይ በማስፈር ግርማይ በርሄ የፖለቲካ ጥገኝነት እንዲያገኝ ረድቶታል።ሊንኩን ይመልከቱ http://ethioforum.org/journalist-witnesses-government%E2%80%99s-brutality/

ግርማይ በርሄ እነ ተመስገን ደሳለኝ፣ ጌታቸው ሸፈራው፣ ዉብሸት ታዬ ዞን 9 ወዘተ በታሰሩ ጊዜ ለነጻ ፕሬስ መጠናከር ለዴሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ መጎልበት ፍላጎቱ ቢኖራቸው ኖሮ መንግስት አያስራቸው ነበረ የታሰሩት ሽብርተኞች ስለሆኑ ብቻ ነው ብሎ ለኖርዌይ መንግስት ሳይቀር ደብዳቤ ጽፎ ለማስተባበል የሞከረ አጭበረባሪ የውሸት ስደተኛ ነው። በተለይ ኖርዌይ የተወረረችው በአድርባዮችና የወያኔ ሰላዮች ነው። አሁን ግን ሁሉንም በስምና ፎቷቸው እያወጣን እናጋልጣቸዋለን። ዲያስፖራዎች እንደነዚህ አይነቶቹን በምቾት እየኖሩ በህዝብ ደም የሚቀልዱትን የሐሰት ስደተኞችና ሰላዮች በማጋለጥ ሁላችንም ብንዘምትባቸው መልካም ይሆናል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *