ጀግናው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ተፈታ! ጊዜ ለኩሉ የሚል መፅሃፍ አሳትሟል! ጥቅምት 5 2010

ጀግናው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ተፈታ!
ጊዜ ለኩሉ የሚል መፅሃፍ አሳትሟል!
ጥቅምት 5 2010

ሰውነቱን አጎሳቁለው ለ3 አመት አንገላትተው ቢያስሩትም መንፈሱ ይበልጥ ጠንክሮ ነው የወጣ። ፀጉሩ ሽበት በሽበት ሆኗል(በውስጤ እልህና እንባ ተናነቀኝ)። ሰውነቱ በጣም እንዳንገላቱት ያስታውቃል። መንፈሰ ጠንካራው አይበገሬው ተሜ ግን የመንፈሱ ጥንካሬ አሁንም ከፊቱ ላይ ይነበባል። በአሳሪወቹ እጅ እያለ እንኳ ትግል ያላቆመው ትንታጉ የኢትዮጵያ ውድ ልጅ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ባዶ እጁን አልወጣም። ለሁሉም ጌዜ አለው የሚል መፅሃፍ ለህዝብ አበርክቷል። እጃችን እስክትገባም ቸኩለናል! አወ ለሁሉም ጊዜ አለው። አሁን ጊዜው ተመስገን ለሚዘምርላት ለኢትዮጵያ ስለመሆኑ የለውጡ አየር እያወጀ ነው! በልጅ ናፍቆት ለ3 አመታት የተንገላቱት እናቱ እንኳን ደስ አለወት። ይህን ጀግና የወለደው ማህፀኖት የተባረከ ነው። እንደ ስምህ ምግባርህ ያማረው ወንድም ታሪኩ ደሳለኝ የወንድም ጠበቃነትን አስተምረሃልና እንኳን ደስ አለህ እናመሰግናለን። ተሜ ናፍቀህናል! ዳመናውን ገልጠህ የተስፋዋን ምድር ትንሳኤ አብስረን!
ሙሉነህ ዮሃንስ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *