የበረከት ስምዖን [ መብራቱ ገ/ ሂወት] የክህደት ጨዋታ – [ሊቁ እጂጉ]

የበረከት ስምዖን [ መብራቱ ገ/ ሂወት] የክህደት ጨዋታ – [ሊቁ እጂጉ]

ይህችን አጭር ማስታወሻ ለመጻፍ የተነሣሁት ከውስጥም ከቅርብ ሆናችሁ በዝርዝር የምታውቁትን የኢትዮጵያ ሕዝብ ቀንደኛ ጠላት እየነቀሳችሁ ለወገናችሁ እንድታጋልጡ ለማሳሰብ ነው።

ሕወሓት(ወያኔ) ብዙ ተንኮለኞችና ጨካኞች የተሰባሰቡበት ለመሆኑ ከደደቢት ጀምሮ በሚፈጽሟቸው አረመኒያዊ የክህደት ተግባራት ይታወቃሉ።

በወያኔ ውስጥ ካሉ የጥፋት ጠበብቶች መካከል መሰሪ ተንኮለኛውና ጨካኙ በእናትና አባቱ ኤርትራዊ ሆኖ ጎንደር ያደገው በረከት ስምዖን(መብራቱ ገብረ ሕይወት) ነው።

በረከት መጀመሪያ ኢሕአፓ ውስጥ ሆኖ ብዙ የነቁ ኢትዮጵያውያን/ትን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ የጨረሰና ያስጨረሰ ለመሆኑ አብረውት የነበሩ ይናገራሉ።

ኢሕአፓን ለቆ ወያኔ ውስጥ ከገባ በኋላ ከሌላው ምስጥ ዘመዱ መለሰ ዜናዊና ስብሓት ነጋ ጋር ተጣብቆ ኢትዮጵያዊነትን በሚያንፀባርቁ የድርጅቱ አባላትና በታወቁ ሰዎች ላይ ብዙ ተንኮሎችን በመጠምጠም እየነቃቀለ ድርጅቱን በፀረ-ኢትዮጵያ ሰዎች አጠናክሮ ለኤርትራ መገንጠል ከፍተኛ አስተዋጽዖ አድርጓል።

ብአዴንን እርሱና መለሰ ዜናዊ በሚፈልጉት መንገድ ጠፍጥፈው አደራጅተው በረከት አለዘሩ የአማራ ሕዝብ ወኪል ሆኖ በአማራው ሕዝብ ላይ በኢኮኖሚ፣ በሥነ-ልቦና፣ በትምህርት፣ በጤና፣ በሕይወትም ላይ ከፍተኛ በደል ሲፈጽሙ ቆይተዋል።

የጥፋት ጓዱ መለሰ ዜናዊ ሲሞት በረከት የሠራቸውን ክፋቶች ስለሚያውቅና ለራሱም ወያኔን ስለሰጋ ከመጀመሪያው የመለመላቸውን የብአዴን የዋሃን በፀረ-ወያኔነት ቀስቅሶ ለልዩ ልዩ የዴሞክራሲ ጥያቄዎች በማነሣሳት ለራሱ መጠጊያ የሚሆን ዋሻ አመቻቸ። በዚህ ሁኔታ ማለትም ብአዴንን ቀስቅሶ በሕወሓትና በብአዴን መካከል መቃቃር ፈጥሮ ከለያየ በኋላ ወደ ሕወሓት ተመልሶ ራሱ የፈጠረውን ችግር እንደሌለበት ሆኖ በሁለቱ ድርጅቶች ለተፈጠረው ችግር መፍትሔ ማግኘት ይቻላል በማለት ገዱ አንዳርጋቸውን አስገድዶ ሕዝቡ ያላወቀውንና ምክር ቤቱም ያለተወያየበትን የአማራ መሬት ፈርሞ ለወያኔ እንዲያስረክብ አደረገ። ከዚያም ከነ አዲሱ ለገሠ ጋር ሆኖ የብአዴንን አመራሮችና ካድሬዎች በተጠያቂነት መሰዋዕት በማድረግ ሪፖርት ለወያኔ አቅርቦ ብዙዎችን ለሥራ መልቀቅና ለክስ አዘጋጅቷቸዋል። በዚህ ሁኔታ ብአዴን ሲተረማመስ ደግሞ በአማራው ሕዝብ ላይ የትግሬ ወያኔያዊ ወታደር አዝምቶበታል። አሁን ደግሞ ቀስቅሶ ያሳመጻቸውን ቀና የብአዴን ሰዎች በመክዳት ወያኔን ዋሻ አደረገ ማለት ነው።

ሌላው በአንድ ተሳስቦና ተዋልዶ በፍቅር የኖረውን ሕዝብ በቅማንት ማንነት ጥያቄ አስነስቶ ከታየ በኋላ በአቶ መለሰ ዜናዊ አንደበት “እናንተ አማራ ሆናችኋል የተለየ የሚያደርጋችሁ ሁኔታ የለም ተብሎ ተዘግቶ ነበር። እንደገና ከእነ አምባሳደር ዘመነ ካሠኝና ሌሎች አድርባዮች ጋር በማሴር ካድሬዎችን እየመለመለ ማስልጠኛ አስግብቶ አጠናክሮ ጥያቄው እንዲነሣ አደረገ። በሌላ አቅጣጫ ደግሞ በአማራ ክልላዊ መንግሥት ኋላ ሆኖ የቅማንት ክልል ሊሆን የሚገባው ብሎ 42 ቀበሌዎችን ያለምንም ሪፈረንደም አሰጥቶ በፌድራል ምክር ቤት ፀደቀ። ግን ብጥብጡ እንዲቀጥል ስለሚፈልግ የቅማንት ተወካይ ነን የሚሉት ይህን እንዳይቀበሉና ጥያቄያቸውን እንዲቀጥሉ አድርጎ ይኸው ሕዝቡንም የክልላዊ መንግሥቱንም እያበጣበጠ ሰላም እንዲጠፋ የእርስ በርስ ግጭቶች እንዲስፋፉ እያደረገ ነው። በአጠቃላይ በረከት ስምዖን 100% በሆነ የክህደት መንገድ ያሳደገውን ሕዝብና አምነው የተጠጉትን የብአዴን ሰዎች ለፍጅትና ለእርድ አዘጋጅቷቸዋል ማለት ነው። ከዚህ በኋላ በሚቀጥለው በረከት ስምዖን ማንንና ማንን እንደሚያጋጭ ጊዜ የሚገልጠው ይሆናል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *