አስደንጋጭ አደጋ ጎንደር ላይ ደረሰ መስከረም 30 2010

አስደንጋጭ አደጋ ጎንደር ላይ ደረሰ
መስከረም 30 2010

በመገንባት ላይ ያለ የጎንደር ዮኒቨርስቲ/ማራኪ ካምፓስ ህንፃ ተደርምሶ እጅግ በጣም ብዙ ሠራተኞች በዛሬው ማክሰኛ እለት ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ ለመወጣጫ የተገጣጠሙት የእንጨት ርብርብ በመደርመሳቸው በስራ ላይ ያሉ ወገኖች ከ6 እስከ 9 ፎቅ ከሚደርሰው ህንፃ ላይ ለመውደቅ ተዳርገዋል። ብዙወች ለሞትና ለከባድ ጉዳት መዳረጋቸው ከቦታው ተነግሮናል። የጉዳቱ ሰለባወች ብዙወቹ የቀን ሰራተኞች ናቸው። ቸቸላ ሆስፒታል በህዝብ ተጨናንቋል። ጥበቃዎች አናስገባም ብለዋል፡፡

የህንፃ ተቋራጩ አፍሮ ጽዬን ኮንስትራክሽን ሲሆን ባለቤቱም ሲሳይ የሚባል የትግራይ ባለሃብት መሆኑን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ጎንደር ያሉ የንግድና የመንገድ እንዲሁም የህንፃ ስራወች ለትግራይ ተወላጆች ልዩ ቅድሚያ እንደሚሰጥባቸው ከአሁን በፊትም ከነማስረጃው ዘግበንባቸዋል።በህዝባችን ላይ ስለደረሰው ጉዳት በጣም እያዘንን ለተጎዱት አፋጣኝ ህክምና እንዲያገኙ ወገንተኝነቱ የተሰማቸው የህክምና ባለሞያወችን ትጋት ይሻል። ስለ ህንፃ ተቋራጩና ስለ ደረሰው ጉዳት ዝርዝር ሁኔታ እያጣራን ነው።
፦፦፦፦፦፦
ዘግይቶ የደረሰን ተጨማሪ መረጃ
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ቴወድሮስ ካምፓስ ውስጥ ባለስምንት ፎቅ ህንፃ ስራ ላይ ስለ ደረሰው አደጋ አዲስ መረጃ ከተቋሙ ሰራተኞች ደርሶናል። ለልስን ስራ መወጣጫ የሰሩት እንጨት ተደርምሶ 13 ሰዎች ወድቀው ነበር። በሰዉ ከፍተኛ እርብርብ የወጡ ሲሆን 1ሴት ወድያው ስትሞት 1ወንድ የቀዶ ጥገና ቢደረግለተም መትረፍ አልቻለም። 11ሰዎች ግን ህክምና እየተደረገላቸው ነው ተብሏል። የህንፃ ተቋራጩ Unity Engineering ነው የሚል አዲስ መረጃም ደርሶናል። ማጣራቱን እንቀጥላለን።
AsnakewAbebe

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *