ዳንኤል ክብረትን “ዲይቆን” ? …..ማነው ? ምን ተልኮ አለው?

ዳንኤል ክብረትን “ዲይቆን” ? …..ማነው ? ምን ተልኮ አለው?
??❤️??????????❤️

ክቡራን ወዳጆቼ ሰሞኑን አንድ የታቀደ ዘመቻ እንዳለ አፈትልኮ የወጣ መረጃ የፌስቡክ መንደርን ማስጨነቅ ጀምሯል! መረጃው እንደሚለው ወያኔ በውጭ ሀገር የሚገኘውን የኦርቶዶክስ ቤ/ክርስትያን ማተራመስ አቅዷል ለዚህም ደግሞ ለክፉ ቀን ያስቀመጠውን አማቹን ዳንኤል ክብረትን አሰማርቷል! በነገራችሁ ላይ ዳንእኤል ከ ማህበረ ቅዱሳን ከተባረረ አመታት ተቆጥረዋል!

ዛሬ ስለዚህ ግሩም ፀሀፊ ለመፈተሽ ፈለግሁ እና ! ይህ ድንቅ ፀሀፊ/ሰባኪ/ የ ማህበራዊ ጉዳይ ተንታኝ…..ብዙ እልፍ አድናቂ ስላሉት ስመ ገናና ሰው ለመፈተሽ ብሞክር ዱላውም ውርጅብኙም እርግማኑም …,ከባድ ስለሚሆንብኝ ባይሆን እንደሱ ስመ ገናና የ ሀገር አድባር ሽማግሌ ከ አምስት አመት በፊት ስለ ዳንኤል ክብረት የፃፉትን ብጋብዛቸው ይሻላል አልኩና ይህን የ ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያምን ፅሁፍ ጀባ ልላችሁ ወደድኩ! ረዥም ነው ግን የሰንበት ቀን ስለሆነ ያውም በሰንበት ስለ ሀይማኖት ጉዳይ ማንበብ መልካምም ስለሚሆን በዛ ላይ ቤተክርስትያንንም ሆነ ሀገርን ማዳን የሚገባ ነገር በመሆኑ ታነቡት ዘንድ ምኞቴ ነው ! የ ፕሮፌሰሩ ትችት መነሻ ‘ መክሸፍ እንደ ኢትዮዽያ ታሪክ” የተሰኘውን መፅሀፍ ዳንኤል አጣጥሎ መፃፉ ነበር ! ግድ የላችሁም ….አንቡት ! ባታነቡትም ላይክ እና ሼር አርጉት ሌላ ቤተክርስትያንን መታደግ የሚችል ሰው ሊአነበው ይችላል! ኤርሚያስ ለገሰም በግድምድሞሽ ዳንኤል የወያኔ ካድሪ መሆኑን ጠቆም አርጏል! ይህን የሚአደርገው ግን ገንዘብ ፈልጎ ነው ወይስ እንደ ጎሳየ ተስፋየ የትግራይ ተወላጇ ባለቤቱ አስገድዳው የታወቀ ነገር የለም በነገራችን ላይ ትግሬ አግብቶ የወያኔ ምርኮኛ ያልሆነ በውርርድ አንድ ሰው ይገኝ ይሆን ? በቅርብ የምናውቀውን ቀነኒሳ በቀለን ጨምሮ ማለቴ ነው!

መክሸፍ እንደ ዳንኤል ክብረት …….መስፍን ወ/ማርያም
??????????
አቶ ዳንኤል ለመናገርና ለመጻፍ ያለው ፍጥነት በሚናገርባቸው ጉዳዮች ላይ ካለው እውቀት ጋር አይመጣጠንም፤ እንዲያውም ያውቃል እንዲባል የሚጽፍ አንጂ አውቆ የሚጽፍ አይመስልም፤ አቶ ዳንኤል ሳላውቀው በጻፈው ላይ አስተያየት ስሰጥ ይህ ሁለተኛዬ ነው፤ ከዚህ በፊት በአንድ ጋዜጣ ላይ በጣም የታወቀውን የአየርላንድ ችጋር በ150 ዓመታት ያህል አቅርቦት በማየቴ አስተያየት ሰጥቼበት ነበር፤ ዛሬ ደግሞ ስለመክሸፍ እንደኢትዮጵያ ታሪክ በጻፈው ላይ አጭር አስተያየት ልስጥ፤ እንዲያው እንትንን እንትን ካላሉት ገብቶ ይፈተፍታል የሚባለውን በመከተል እንጂ ትርፍ ይኖረዋል ብዬ አልገምትም፤ ከደርግ ዘመን ጀምሮ የተለያዩ ካድሬዎች ደብተራዎችም ጭምር ማነብነብን እንደተናጋሪነት ሠልጥነውበታል፤ ስለዚህም ሰውም ማነብነባቸውን እንደእውቀት እየወሰደው ይወናበዳልና በጊዜው መልስ መስጠት ግዴታ ይመስለኛል፤ የሰው ልጅ በምን ይታፈራል? በወንበር፤ በወንበር አይደለም በከንፈር፤ ይባላል፡፡

ነገር ሳላበዛ ጥቂት ነጥቦችን በማንሣት የአቶ ዳንኤልን የማንበብ ችሎታና የተንኮል ክህነት ብቻ ለአንባቢዎች ላሳይ፤ ስለአስተያየቱ አስተያየት መስጠት አስፈላጊ አይደለም፡፡

አንደኛ፣ ደጋግሜ እንብቤዋለሁ ይላል፤ ይህንን ባይነግረን ጥሩ ነበር፤ በመናገሩ ብቻ እንዳናምነው ማስረጃ ይሰጠናል፤ ያላነበበውን ደጋግሜ አንብቤዋለሁ ማለት ያስፈለገበት አስገዳጅ ምክንያት ምንድን ነው? አውቃለሁ ብሎ በመነሣት ለማሞኘት ወይም ለማታለል ካልሆነ በቀር ሌላ ምክንያት ያለ አይመስለኝም፤ እንደአቶ ዳንኤል ያለውን ለማስጠንቀቅ ደጋግሜ አነበብሁት በሚለው መጽሐፍ ውስጥ ‹‹የዩኒቨርሲቲን ዓለም የማያውቁ ሰዎች ሌላ ትርጉም በመስጠት እንዳይሳሳቱ ማስጠንቀቅ ያስፈልጋል፤ በአካል በዩኒቨርሲቲ ውስጥ ሆነው ልባቸው ከደብተራ ተንኮል ላልጸዳም ቀናውን የእውነት መንገድ እንዲያመለክታቸው እመኛለሁ፤›› የሚል ተጽፎ ነበር፤ ይህንን አቶ ዳንኤል አላነበበውም፤ ካነበበውም አልገባውም፡፡

ሁለተኛ፤ ‹‹ለመሆኑ ታሪክ ይከሽፋል? የክሽፈት ታሪክ ሊኖር ይችላል እንጂ የከሸፈ ታሪክ ሊኖር ይችላል? የስኬት ታሪክ ይኖራል እንጂ የተሳካ ታሪክ ይኖራል? አንድን ታሪክ ከሽፏል ወይም ተሳክቷል የሚያሰኘው ምን ምን ሲሆን ነው? … በመጽሐፉ የምናጣው ታላቁ ነገር ይሄ ነው፤›› በዚህ ትርጉም የማይሰጥ የቃላት ድርደራ ላይ ምንም አስተያየት መስጠት አይጠበቅብኝም፤ ይቀጥልና ‹‹.. የታሪክን ክሽፈትና ስኬት መበየኛ ነገሮችን አስቀድመው በማሳየት አንድ ታሪክ ከሸፈ ወይም ተሳካ የሚያሰኙትን መመዘኛዎች …›› ይላል አቶ ዳንኤል፤ ካላነበበው ‹ደጋግሜ አንብቤዋለሁ› በማለት ብቻ ጭንቅላቱ ውስጥ አይታተምለትም፤ የሚከተለው እንደሚነበብ ሆኖ የተጻፈ ነበር፤ ‹‹መክሸፍ የምለው አንድ የተጀመረ ነገር ሳይጠናቀቅ ወይም ሳይሳካ እንቅፋት ገጥሞት መቀጠል ሳይችል ዓላማው ሲደናቀፍና በፊት ከነበረበት ምንም ያህል ወደፊት ሳይራመድ መቅረቱን ነው፤›› ይህ ተጽፎአል! አላነበበውም፤ ካነበበውም አልገባውም፡፡

ሦስተኛ፤ ‹‹ታሪክ ጸሐፊዎቹን ከታሪኩ ጋር አብሮ መውቀጥ ከተልባ ጋር የተገኘህ ሰሊጥ ዓይነት ይሆናል››! ይላል፤ ይህ ሰው አንብቤአለሁ፤ አውቃለሁ፤ ሲል በመሃይም ድፍረት ነው፤ የሚከተለው ተጽፎአል፤ ‹‹አንድ ሰው በአገርና በሕዝብ ጉዳይ ላይ ከጻፈ ‹‹ማንም ዜጋ በጉዳዩ ላይ የመሳተፍና ሀሰቡን በሙሉ ነጻነት የመስጠት መብት አለው፤ አለዚያ በየጓዳችን በሐሜት ብቻ እየተዘላዘልን እውነትን አንጥሮ በአደባባይ የማውጣቱን ዘዴ ሳንማር ሌላ ሦስት ሺህ ዓመታት እንቀጥላለን፤›› ይህንን አላነበበውም፤ ካነበበውም አልገባውም፡፡

አራተኛ፤ በራሱ ላይ ሲፈርድ ቶሎ ሳይጽፍ መቆየቱን ለማስረዳት ምናልባት ከእሱ የተሻለ ሰው ቢጽፍ፣ ምናልባት ፕሮፌሰር ባሕሩ ቢጽፍ፣ ምናልባት የታሪክ ሊቃውንትቱ ተማሪዎች ቢጽፉ፣ ምናልባት የታሪክ ክፍሉ ቢጽፍ በማለት ጠብቆ እንደነበረ ይገልጻል፤ እነዚህ ሁሉ የሱን ምኞት እሱ በፈለገው ፍጥነት ሳያሙዋሉለት ቀሩና እነፕሮፌሰር ባሕሩን ላጨበት ሥራ ራሱን አቀረበ፤ የሱ ድፍረት የሌሎቹን እውቀት የሚበልጥ ለማስመሰል ጻፈ፤ ድፍረቱን ልናደንቅለት ይገባል፤ በማያውቁት ጉዳይ ደረትን ገልብጦ በሙሉ እምነት ማነብነብ የካድሬዎች ባሕርይ ሆኖ በቤተ እግዚአብሔርም ገብቶአል፡፡

አምስተኛ፤ አቶ ዳንኤል ከአዋቂነት ወደመንፈሳዊነት ይሸጋገርና ‹‹አንድን አካል መልስ ለመስጠት በማይችልበት ጊዜና ሁኔታ መሄስና መውቀስ ከሞራል አንጻር ፍትሐዊ አይሆንም፤ የሀገሬ ሰው ‹ሙት ወቃሽ አትሁን››› እዚህ ደግሞ ጭራሽ ሊወጣበት ከማይችለው የአለማወቅ ማጥ ውስጥ በድፍረት ገባ! ‹‹ሞራል›› ስለሚለው ነገር ምንም እንደማያውቅ ሳያውቅ አወጀ፤ ድፍረት ብቻውን በምንም መንገድ እውቀት አይሆንም፤ ለመራቀቅ ፈልጎ ራሱን በአለማወቅ አዘቅት ውስጥ ከተተ፡፡

ስድስተኛ፤ በጽሑፉ መደምደሚያ ላይ የደብተራ ተንኮል አፈትልኮ ይወጣል፤ መንግሥቱ ኃይለ ማርያምን ያነሣና በደብተራ ተንኮል አንዱን ‹‹ዶክተር›› የሚለውን መልክ የሌለውና ስም የሌለው የደብተራ ምሥጢር ያደርግና፤ ‹‹እኒህ የኢትዮጵያ ጥናት ተቋም ዶክተር ወደመንግሥቱ ኃይለ ማርያም ዘንድ በማን በኩል እንደሄዱ ፕሮፌሰር መስፍን ያውቃሉ፤›› ብሎ ይለጥፍብኛል፤ እግዚአብሔር ያሳያችሁ ስሙን ያልጠቀሰውንና የማላውቀውን ሰው የእኔን ስም ጠርቶ እንደማውቀው አድርጎ ሌላ ስሙን ያልጠቀሰውንና እኔ የማላውቀው ‹‹ዶክተር›› ወደመንግሥቱ ያቀረበ እያለ ውሸት ሲያጠነጥንና ሲፈትል ጊዜ ያጠፋበት ምክንያት አልገባኝም፤ ተንኮሉ እዚህ ላይ አያበቃም፤ ታደሰ ታምራትን ‹‹መንግሥቱ ከመሸኘቱ በፊት ግን ‹ከዶክተር እገሌ ጋር ቅሬታ አላችሁ መሰል፤ አንዳንድ ነገር ነግሮኝ ነበር፤ እዚያው ተነጋግራችሁ ፍቱት፤ አላቸው፤›› ይልና የመጨረሻዋን የደብተራ ተንኮል ጣል አድርጎ ይደመድማል፤ ‹‹አሁን እዚህ መጽሐፍ ላይ ቤተ መንግሥቱን አየሁት፡፡›› ምን እንዳየ፣ የት እንዳየ፣ ምንና ምን እንደተገናኘ የደብተራ ምስጢር ነው፤ ያቀረበውን ሁሉ የማን ባለሙዋል ሆኖ ያገኘው እንደሆነም አይናገርም፤ እንዲህ ያለ ሞላጫነት! ስለእውቀት ከተጻፈ መጽሐፍ ተነሥቶ ወደመንግሥቱ ኃይለ ማርያም ጓዳ ገብቶ፣ ስሙ የማይጠራ ዶክተርን መነሻ አድርጎ፣ ይህን ሁሉ እኔ እንደማውቅ ተናግሮ በድንቁርና ምርጊት ይደፍነዋል! እንዲህ ያለ ሰው ስለእውቀት ለማውራት ለምን ይነሣል? ከበሽታ በቀር ምን ሌላ ይገፋፋዋል? ከዳዊት ሰለሞን

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *