የኢትዮጵያ ሕዝብ ስለተትረፈረፈ የኤሌክትሪክ ኃይል ምርት በዜና ሲነገር ይሰማል እንጂ የቤቱን አምፖል የሚያበራለት ኃይል የሚመጣለት በቀን ከ 3 ሰዓት አይበልጥም!! ዘመቻ

#ETHIOPIA | የውሀና የኤሌክሪክ መብራት አገልግሎት ሂሳብ ያለመክፈል ዘመቻ

የአገልግሎት ሂሳብ መጠየቅ ያለበት የተሟላ አገልግሎት ከተሰጠ በኋላ ብቻ ነው። ለግማሽ ወይም ለኩርማን አገልግሎት ሂሳብ አይጠየቅም። የተሟላ አገልግሎት ሳይሰጥ ሂሳብ መጠየቅ ነውር ነው፤ ህገ-ወጥ ነው፤ ዘረፋ ነው።

የኢትዮጵያ ሕዝብ ስለተትረፈረፈ የኤሌክትሪክ ኃይል ምርት በዜና ሲነገር ይሰማል እንጂ የቤቱን አምፖል የሚያበራለት ኃይል የሚመጣለት በቀን ከ 3 ሰዓት አይበልጥም። መብራት ሲመጣና ሲሄድ ለሚቃጠለው ንብረት የኢትዮጵያ የኤሌክሪክ መብራት ኃይል ባለሥልጣን ካሳ ከፍሎ አያውቅም። የአገልግሎት ሰጪው መሥሪይ ቤት ከተገልጋዮቹ ጋር ውል የገባው ሃያ አራት የመብራት ኃይል ሊያቀርብ እንጂ ሲያመቸው ሊያቀርብ ሳያመቸው ሊያቋርጥ አይደለም። አገልግሎት ሰጪው ውል በማፍረሱ ለተገልጋዮች ካሳ ሊከፍል ይገባ ነበር፤ ይህ አልሆነም። ይህ ሳይፈፀም ሂሳብ መጠየቅ ኢፍትሃዊ አሠራር ነው። ስለዚህ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ሂሳብ አንከፍልም ማለት ተገቢ ነው።

የመጠጥ ውሀ አቅርቦት ደግሞ ከኤክትሪክ ኃይል አቅርቦት የባሰ ነው። በሳምንት አንድ ቀን ለሚመጣ የቧንቧ ውሀ የአገልግሎት ሂሳብ መቀበል ነውር ነው። ውሀ በማይኖርበት ጊዜ በቧንባ መስመር ላይ በሚደርስ ዝገት ምክንያት ለሚደርስ የጤና መታወክ እና በውሀ እጦት ለሚደርሰው ጉዳት የውሀ አቅራቢው መሥሪያ ቤት ካሳ መክፈል ይኖርበታል። እነሱ ሂሳብ ስለመጨመር ሲያስቡ እኛ የምናስበው ስለጉዳት ካሳ ነው። ይህ ተግባራዊ እስከሚሆን ድረስ የውሃ አገልግሎት ሂሳብ አንከፍልም ማለት ተገቢ ነው።

በ2009 ዓም የተጀመረው ግብር ያለመክፈል ዘመቻ ዘንድሮ አድማሱን እንዲያሰፋ ከሚደረገው ጥረት በተጨማሪ የዉና የኤሌክትሪክ መብራት አገልግሎት ሂሳብ ያለመክፈል ዘመቻ ለመጀመር ጊዜው ያስገድዳል።

ላልተሰጠ አገልግሎት ሂሳብ የምንከፍልበት ምክንያት የለም ! አገልግሎቶች ይሟሉ፤ ለደረሱብን ጉዳቶ ካሳ ይከፈለን !!!

በውሀና በመብራት ኃይል የአገልግሎት ሂሳብ ላይ ዘመቻ ይጀመር!!!

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!!

© Patriotic Ginbot 7: Dept of Civic Disobedience

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *