የአግ7 የሰሜን ኢትዮጲያ ዕዝ ታጋዬች መስከረም 19 ለ 20 /2010 ከለሊቱ 6:00 እስከ 8:00 በቆየው የተኩስ ልውውጥ የወያኔ ፀረ ሽምቆች በመሮጥና በገደሉ እየተንከባለሉ ወደ ሊቦ ሲሸሹ ፡

#Ethiopia : በደቡብ ጎንደር ሊቦ ከምከም ወረዳ ሊቦ ቀበሌ መሽጎ በነበረው የፀረ ሽምቅ አባላት ላይ የአግ7 የሰሜን ኢትዮጲያ ዕዝ ታጋዬች መስከረም 19 ለ 20 /2010 ከለሊቱ 6:00 እስከ 8:00 በቆየው የተኩስ ልውውጥ የወያኔ ፀረ ሽምቆች በመሮጥና በገደሉ እየተንከባለሉ ወደ ሊቦ ሲሸሹ ፡ በወቅቱ ይህን የወያኔን ፀረ ሽምቅ በዋና አዛዥነት እና በምክትል አዛዥነት ሲመሩት የነበሩ ዋና አዛዥ ማሩ ዋለ እና ምክትሉ ጌትነት ወንድዬ መሽገውበት እና ማዘዣ ጣቢያ አድርገው ይጠቀሙበት የነበረው ሁለት ትልልቅ ክፍሎች ከነ ሙሉ ንብረታቸው እና ዕቃቸው በቦምብ በእሳት ጋይተዋል፡፡ እነዚህ አዛዦች ሆድ አደር በመሆን ለህወሓት አገልጋይ ሆነው የአካባቢውን ህብረተሰብ መኖሪያቤት ፡ አዝመራ ሲያቃጥሉ እና የህዝቡን የቤት እንሰሳ ሲያርድና ሲዘርፉ የነበሩ አረመኔዎች ናቸው፡፡ ይህ ዘመቻ ከአሁን በኃላ ለሆዳቸው በማደር በማንኛውም መልኩ ለህወሓት አገልጋይ በመሆን እየሰሩ በሚገኙ ሁሉ እርምጃውና ጥቃቱ የሚቀጥል መሆኑን እንገልፃለ ፡ ከህዝብ ወጥተው ህዝብን ከአረሚኔዎች በመታደግ ጥቃቱን የፈፀሙ ታጋዬች በሰላም ወደ ቦታቸው ተመልሰዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *