እዚህ ተደርሷል።

ይህ አይን ያወጣ ባዕድ አምልኮ ነው።

ብርሃን ከጨለማ ጋር ፥ብኤልዜቡል ከክርስቶስ ጋር ምን ያገናኘዋል?

መለስና መስቀል በምን ሂሳብ በምን ስሌት ይገናኛሉ?

የተሰቀለልን መለስ ነውን ?

የሰውን ልጅ ለማዳን የሞተልን መለስ ነውን ?

እርኩሱን…ዘረኛውን….ነብሰ በላውን….ሙሰኛውን…ጎጠኛውን….ተንኮለኛውን…አገር ሸቃጩን…ፀረ-ኢትዮጵያዊውን….መሬት ሸንሻኙን….ህዝብ አተራማሹን….ይህን ቁጥር አንድ አረመኔ ስለምን ከመስቀሉ ጋር በአንድ አደረጋችሁት ?

እናንተ ልበ እውራን በውኑ ይህ በአምላክ ፊት አፀያፊ አይደለምን ?
በውኑ ይህ አምልኮ አይደለምን ?
ይህ በእግዚአብሔር ዘንድ የሚወደድ ነውን ?

ለትውልዱ ምን እያስተላለፋችሁ ነው?
እናንተስ ለነፍሳችሁ ምን እያሰባችሁ ነው?

ይህ አይን ያወጣ ቅብጠታችሁ….ይህ አምላክን የሚገዳደር ድፍረታችሁ….ይህ ከደንዳና ልባችሁ የወጣ ትቢታችሁ….ይህ ከድንገተኛ ጥጋብ የመነጨ ብልግናችሁ……የት እንደሚያደርሳችሁ አስባችሁበታል ?

ለነገሩ እንደ ፈርዖን ልባችሁን ያደነደነው የራሱ ምክንያት ቢኖረው ነው ።ፍርዱን ለእርሱ ትቻለሁ።

ይብላኝላችሁ።  ዮሴፍ ይጥና

በምስሉ ላይ ከትልቅ እድከትንሽ ስትሰግዱ ….ፀሎት እያደረጋችሁ ፎቶ ስትነሱ ጉድ ብለን ነበር።አሁን ደግሞ በክርስቶስ ተክታችሁት ቁጭ አላችሁ።

እ….ግ…ዚ….ዖ !!!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *