ጎበዝ የያዝነው እኮ ትግል ነው ! የ ሰው ህይወት የሚከፈልበት ትግል! ይህ ትግል ብዙ ወገኖችን አስገብሮናል!

ብርሀኑ ነጋ——– ሲፈተሽ
??❤️?????❤️
ስለዚህ አርስት ለመፃፍ ስነሳ ከራሴ ጋር ተሟግቻለሁ!! መቼም ሰማይ አይታረስም ንጉስ አይከሰስም በሚባልበት ማህበረሰብ ውስጥ እያለሁ ይህን ለሰማይ እና ለምድር የሚከብድ ስብዕና ያለውን ሰው ለመፈተሽ ስነሳ ምን ያህል ውርጅብኝ እንደማስተናግድ ከወዳሁ ይተየኛል!!

ጎበዝ የያዝነው እኮ ትግል ነው ! የ ሰው ህይወት የሚከፈልበት ትግል! ይህ ትግል ብዙ ወገኖችን አስገብሮናል! የቅርቦችን ለማስታወስ ያክል መሳፍንት ጥጋቡ (ገብርየ) አበራ ጎባው …ሌሎች በስም የማናውቃቸው ታጋዮች ተሰውተውበታል! አንዳርጋቸው ፅጌን ጨምሮ ስንት እና ስንት ሰወች ጥፍራቸውን እየተነቀሉ! በዘይት የተቀቅሉበት የውስጥ ገላቸው እስኪገለበጥ የተገረፉበት ትግል ነው! ይህ ትግል መራራ እጅግ መራራ ነው!!! ስለዚህ ይህ መራራ እልህ አስጨራሽ ትግል ሚሊዮኖች በፀሎት በገንዘብ በህይወት የሚደግፉት የህዝብ ትግል ነው!

ወያኔ ከጥንሱ ጀምሮ ይህን ትግል ጠምዶ የያዘው የመሪወችን ቆራጥነት እና የማያወላዳ የትግል ፅናትን በመገንዘብ እንጅ በሰራዊቱ ብዛት ወይም ባለው የመሳርያ ክምችት አይደለም!

ይህ ወያኔን ያንቀጠቀጡ እና ያናወጡ መሪወች እንደ እናት ጡት ሁለት ናቸው አንደኛው እስር ቤት የሚማቅቀው እእንዳርጋቸው ፅጌ ሌለኛው ብርሀኑ ነጋ!!!

እኔ የግለሰብም የ ድርጅትም አምላኪ አይደለሁም ሁለቱንም ሰወች በአካል አላውቃቸውም ! እኔን ከነመፈጠሬም አያውቁኝም! ሁለቱ ከልብ መሪወች ናቸው! ሁለቱም የተሰጣቸው የተለያየ መክሊት ነበር ! ሁለቱ በ አንድ ላይ ግን ሙሉ ይሆናሉ! አሁን አንድ አካል ብቻ ንቅናቄውን እየመራው ይገኛል!

ብርሀኑ ነጋ !ይቅርታ ማዕረጉን እየደረደርኩ አላሰለቻችሁም ብየ እንጅ አርበኛ ታጋይ ብርሀኑ ነጋ የሚለውን ማዕረግ አላምንበት ሁኘ አይደለም!! ይህ ሰው በተፈጥሮ ደመ መራር ይመስለኛል ብዙ ቀንደኛ ጠላቶች በግለሰብ ደረጃ አፍርቷል ! ከ እነኝህ መካከል ልደቱ አያሌው ዋነኛው ሲሆን ሌሎችም ብዙ አሉ! እነዚህ ጠላቶቹ በየግዜው የሚፈበርኩት ስም እና ጥላሸት ብዙ ነው! ዋና ዋናወችን በዚህ ፅሁፌ ልዳስሳቸው!

1. ፀረ አማራ !
———–
መቼም በ እሱ ደረጃ ከልጅነቱ ጀምሮ እስከ አሁኑ እድሜው ድረስ ለነፃነት ያቀነቀነ! እህቶቹ በልጅነታቸው በመስዋዕትነት ሲወድቁ የታዘበ ታጋይ ለአንድ እሱ ሲታገልላት ለኖረችው ሀገር መሰረት የሆነን የህብረተሰብ ክፍል ይጠላል ብሎ ማሰብ ከባድ ነው! እስኪ እሱ ላይ የተለጠፈውን ጥላቻ ለጊዜው ተውት እና እንደሰው ልጅ አስቡት ከሰማንያ በመቶ በላይ አማራ የሆኑበትን ንቅናቄ እየመራ እነ ገብርየን የመሰሉ የ አማራ ልጆች ለህይወታቸው ሳይሳሱ እየወደቁ ያየ ሰው እንዴት እነ ገብርየ የወጡበትን ማህበረሰብ ይጠላል! ?
እነ አንዳርጋቸው እነ ነአምን እነ ገበየሁ አባጎራው እነ አሰፋ ማሩ የወጡበትን ማህበረሰብ እንዴት ይጠላል ተብሎስ ይታሰባል ? ይህ ሰው የተለየ ፍጡር ካልሆነ በስተቀር አማራን የሚጠላበት ምንም ምክኒያት የለውም! የወጣበት የጉራጌ ማህበረሰብም ሳይቀር የ አማራ ተለጣፊ ይባላል እንጅ አማራን የሚጠላ አይደልም ስለዚህ ፀረ አማራነትን ከየት ያመጣዋል?

2. በ ህዝቡ ገንዘብ ይነግዳል!
——-//-////——–///
ሲያሙት ያማል ይላል አባቴ እንዲህ አይነት ያልሆነ ሀሜት ሲገጥመው! እስኪ ማን ይሙት በሙሉ ፕሮፌሰር ማዕረግ ዩኒቨርስቲ የሚአስተምር ! ባለቤቱ የራሷ የህክምና ማዕከል ያላት ዘር አዛርቱ የሞላው የተረፈው ባለፀጋ ስንት ጉሮሮ ደርቆ የሚገኝ ብር በልጦበት በህዝብ ገንዘብ ሲነግድ? ይህ ሰው እኮ ወደ ትግሉ በመግባቱ ምክኒያት የተዘረፈበት ንብረት ብቻ እኛ እስካሁን ካዋጣነው ገንዘብ የብዙ እጥፍ ይሆናል!

ለማንኛውም ወገን ይህን የመሰለ መሪ አይዞህ እያልን እየደገፍን እውቀቱን እና ዝናውን መጠቀም ሲገባን ባልሆነ በተልካሻ ነገር መወጋጋት ለ እሱም ለዚች ምስኪን ሀገርም አይጠቅምም !ህሌናችን እንፈትሽ እና ራሳችን እንመርምር እላለሁ ወንድማችሁ! ዳዊት ሰለሞን

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *