የሚያየው እና የሚሰማው የወያኔ ግፍ እዚህ የሚያረገው ተሳትፎ አላረካ ብሎት ነው ወደ ኦርትራ ያመራው ።

| በምስሉ ላይ የምትመለከቱት አርበኛ ታጋይ ተስፋ ላቀው በቅፅል ስሙ ተከዜ ከአሜሪካዋ ከተማ ሲያትል የሞቀ ቤቱን እና ኑሮውን ጥሎ ኤርትራ በረሃ በመውረድ የተሰዋ ጀግና።

ዛሬ የሲያትል አርበኞች ግንቦት 7 አባላት ትልቅ ሀዘን ላይ ነው ያሳለፍነው የወንድማችን እና የትግል አጋራችን የሆነው አርበኛ ተስፋ ላቀው ከትግል ሜዳው የተመለሱ ወገኖቻችን መሰዋቱን ሲያረዱን የተሰማንን ሀዘን በቃላት መግለፅ እጅግ ከባድ ነበር ።

አርበኛ ታጋይ ተስፋ ላቀው /ተከዜ/ እጅግ በጣም መልካም አስተዋይ እንዲሁም በድርጅታችን ውስጥ በምንም አይነት ተሳትፎ ቀድሞ የሚገኝ ከምነግራችው በላይ የሚገርም ትህትና ያለው ትክክለኛ አገር ወዳድ ስለ ኢትዮጵያ ህዝብ አጥብቆ የሚቆረቆር ውድ የኢትዮጵያ ልጅ ነው ።

የሚያየው እና የሚሰማው የወያኔ ግፍ እዚህ የሚያረገው ተሳትፎ አላረካ ብሎት ነው ወደ ኦርትራ ያመራው ።

ከመሰዋቱም በፊት ብዙ ግዴታዎችን ከአጋር የትግል ወንድሞቹ ጋር ግብ የመታ ጅግና የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጇ ነው እና በህይወት ባይኖርም ከልባችን ተቀምጦ ይኖራል።

ይህንን ሁሉ መከራ የሚያስከፍለን ይህንን ወራዳ ሰው በላ አገዛዝ እስከ መጨረሻው እንፋለመዋለን !

ከሞቀ ቤቱ ሁሉን ነገር ትቶ ከአሜሪካ ከሲያትል ከተማ ለኢትዮጵያን ነፃነት ኤርትራ በርሀ ወርዶ የተሰዋ የህዝብ ልጅ ነው ይህንን እያየን እንኳን አሁንም በዘር መርዝ ተተብትበን በወሬ ህዝብ የምናደነቁር እውነት የወያኔ ቅጥር ካልሆንን መሬት የወረደውን ትግል ጥግ ማድረስ አለብን ይህንን የማናረግ ከሆነ ግን የዚህ ሁሉ ህዝብ ደም ተጠያቂ እንደምንሆን እንዳንዘነጋ።
ወንድሜ ተስፋ ላቀው አስረስ / ተከዜ / ነብስህን በገነት ያኑርልን ሁሌም በነፃነት ፈላጊው የኢትዮጵያ ህዝብ ልብ ውስጥ ነክ ለቤተቦቹም መፅናናትን እንመኛለን።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *