ጎንደር ላይ የወያኔ አመራሮች አስቸኳይ ስብሰባ ተቀምጠዋል::

የህወሓት ፍላጎትና ዕቅድ ከሸፈ፡፡

#Ethiopia : በሰሜን ጎንደር ዞን በምዕራብ ወረዳዎች ለዘመናት አብረው እየኖሩ የሚገኙትን የአማራን እና የቅማንትን ህዝቦች ለማጋጨት ያደረገው እንቅስቃሴ በሁለቱ ህዝቦች በሳል አስተሳሰብ ሊከሽፍ ችሏል፡፡ በመሆኑም በቋራ ወረዳ ኮዛ ቀበሌ በተባለው ቅማንቶች አንመርጥም ብለው ወጥተዋል መጀመሪያም ተገደን ነው ካርድ የወሰድነው በማለታቸው ምርጫው በታቀደው መሰረት ሳይካሄድ ቀርቷል በሌሎች ቀበሌዎችም በጭልጋ ወረዳ ነጋዴ ባህር ኳሊበር ሎሜዬ እንዲሁም በመተማ ወረዳ መቃ ሽንፋ ጉባይ ላንጫ ቱመት በመሳሰሉት ቀበሌዎች እየተደረገ ያለው ምርጫ የቅማንት ተወላጆች መምረጥ አልፈለጉም:: በመሆኑም ህወሓት ዕቅድ መክሸፉን ሲረዳ የተወሰኑ ኮሜቴ ነን የሚሉ የቅማንትን ህዝብ የማይወክሉ ለሆዳቸው ያደሩ በመሰብሰብ ምርጫውን አደናቅፎ ግጭት ለመቀስቀስ ከጭልጋ ወረዳ ነጋዴባህርና ኳሪበር ሎሜዬ ቀበሌዎች የቅማንት ተወላጅ የሆኑ ሴቶችን እና ህፃናትን በመኪና በመጫን በማስወጣት ላይ ይገኛል:: ጎንደር ላይ የወያኔ አመራሮች አስቸኳይ ስብሰባ ተቀምጠዋል:: ያለውን ሁኔታ እየተከታተልን እንገልፃለን፡፡ ናትናዬል መኮንን

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *