አንተ ቀልደኛ ነህ፥ ፎግረህ ምትበላ

አንተ ቀልደኛ ነህ፥ ፎግረህ ምትበላ
እኔ ለፍቶ አዳሪ፥ የለቴን እንጀራ
ተሸክሜ ምዞር፥ ከሸንኮራ ጋራ።
አንተ ለለት ጉርስህ፥ ለሰው ሳቅ ለመፍጠር
ሸንኮራ እንደንቁላል፥ በጣይ ስትመረምር
በጆችህ በያዝከው፥ በቁራጩ መሀል
ወለላ አየሸጠ፥ በደረቀ ከንፈር
በሽብሽብ ግንባሬ፥ እየው የፊቴን ጣር
የሚታይ የለውም፥ ከባዶ ሆድ በቀር።

ቀልድ እንጀራ ሲሆን፥ በፌዘኞች ዓለም
አንዱ ጎርሶ ያድራል፥ በሌላኛው ህመም።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *